የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ መስጫ አማራጭ ይፋ ሆነ

ኅብረተሰቡ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ የሚሰጡበት አማራጮች ይፋ ሆነዋል፡፡በዚህም ዕጩ ኮሚሽነሮችን

• በቀጥታ ስልክ 0111300340 ወይም 9988

• በፋክስ ቁጥር 0111233007

• በኢ-ሜል dialoguecommission@gmail.com

• በinfo@hopr.gov.et ወይም

• በአካል ጥቆማ መስጠት እንደሚችል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

በኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጁ አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 1 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የዕጩ ኮሚሽን አባላትን ከሕዝብ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶችና ከሲቪል ማኅበራት እንደሚቀበል ተደንግጓል፡፡በአዋጁ አንቀጽ 13 መሰረት ለኮሚሽነርነት የሚያበቁ መስፈርቶችም፡-

1/ ዜግነት ኢትዮጵያዊ፣

2/ ሁሉንም ሃይማኖቶች፣ የተለያዩ ብሔሮችን፣ ብሔረሰቦችን እና ሕዝቦችን በእኩል ዓይን ማየት

3/ የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ፣

4/ ለአገራዊ መግባባት ጉልህ አስተዋፅዖ ሊያበረክት የሚችል፣

5/ መልካም ሥነ-ምግባርና ስብዕና ያለው፣

6/ በሕዝብ ዘንድ ዓመኔታ ያለው፣

7/ በከባድ ወንጀል ተከሶ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያልተላለፈበት፣

8/ የኮሚሽኑን ሥራ በአግባቡ ለመሥራት የሚያስችል የተሟላ ብቃት ያለው፣

9/ ሙሉ ጊዜውን ለኮሚሽኑ ስራ ለማዋል ፍቃደኛ የሆነ የሚሉት መሆናቸውን ምክር ቤቱ አስታውቋል።


Leave a Reply