በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች አሸባሪዎቹ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግና ሸኔ የፈጸሙትን የሰብአዊ ጥሰት ወንጀሎችና የንብረት ውድመት የሚያሳይ የፎቶ ሰነድ ይፋ ተደረገ።

አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን አሸባሪዎቹ ሕወሓትና ሸኔ የፈጸሟቸውን ዘግናኝና አሰቃቂ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የመሰረተ ልማትና ንብረት ውድመቶች እንዲሁም ወንጀሎችን በፎቶ ማስረጃነት የሚያሳይ https://nomore-ethiopia.org/ የተባለ ድረገጽ ይፋ አድርገዋል።

ድረገጹ ስያሜውን ያገኘው በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የተለያዩ ግንዛቤዎችንና ለውጦችን የፈጠረውን የበቃ ወይም #nomore  እንቅስቃሴን ተከትሎ ሲሆን ንቅናቄው አፍሪካውያንና ሌሎችንም ያነሳሳ እንደሆነ ተመልክቷል።ንቅናቄው ምንም አይነት የጸጥታ ችግር ሳይፈጠር ሁሉንም ባስገረመ መልኩ የተከናወነ መሆኑን አውስቷል።

ይህንንም ተከትሎ የአንዳንድ ምዕራባውያንና የዘመናዊ ቅኝ ገዢዎችን አጀንዳ የሚያስፈጽሙትን ሕወሓትና ሸኔ የሽብር ቡድኖችን ተግባር በዚሁ የንቅናቄ መንገድ ማስተላለፍ አስፈልጓል ብሏል። በዚህም አሸባሪዎቹ ሕወሓትና ሸኔ በ17 ከተሞች ያደረሱትን የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ እጅግ ዘግናኝና አስከፊ ወንጀሎች እንዲሁም የመሰረተ ልማትና የተቋማትን ውድመት የሚያሳይ የፎቶ ሰነድ በድረገጹ https://nomore-ethiopia.org/ ይፋ መደረጉን ከኢዜአ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡


Leave a Reply