ተመድ በመቐለ 570,000 ሊትር ነዳጅ መዘረፉን ገለፀ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች በሰጡት መግለጫ ዛሬ ነሀሴ 18 ቀን 2014 ዓ/ም ጥዋት በትግራይ ክልል መዲና ፤ መቐለ ከተማ የሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) መጋዘን መዘረፉን ገልፀዋል።

ዱጃሪች ፤ ” ዛሬ ጥዋት የትግራይ ኃይሎች መቐለ በሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን በኃይል በመግባት 12 የነዳጅ ታንከር 570,000 ሊትር ነዳጅ ውስደዋል ” ሲሉ አሳውቀዋል።

በቦታው ላይ የነበረው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ቡድን ዘረፋውን ለመከላከል ጥረት ቢያደርግም እንዳልተሳካለት ተናግረዋል።

የተዘረፈው ነዳጅ ለሰብዓዊ ድጋፍ ፣ ምግብ፣ ማዳበሪያና ሌሎች አስቸኳይ ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ የሚውል ነበር ያሉት ዱጃሪች ” ነዳጁ በመዘረፉ በመላው ሰሜን ኢትዮጵያ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ለመድረስ የሚሰራው የሰብዓዊው ድጋፍ ስራ ላይ ተፅኖ ይኖረዋል ” ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሰብዓዊ ስራ ሊውል የነበረው ነዳጅ ላይ የተፈፀመውን ዝርፊያ አጥብቆ እንደሚያወግዝ ገልፀዋል።

ViA @tikvahethiopia

See also  የተበተነው የትህነግ ሰራዊት ወደ ወደ ተንቤንና አቢ አዲ ዳግም የመሰባሰብ እቅድ እንዳለው ተሰማ፤ የመከላከያ አባላት "ትንኮሳ ሰለቸን" ይላሉ

Leave a Reply