“የምንዛሬ ለውጥ ሊደረግ ነው በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሁሉ ሀሰት ነው ” አቶ ማሞ ምህረቱ

በኢትዮጵያ ” የገንዘብ ምንዛሬ ተመን ማስተካከያ ሊደረግ ነው ” በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሀሰት ነው ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሳውቋል።

የባንኩ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ማብራሪያ ፥ ” እስከዛሬ ድረስ / እስካሁን ድረስ በአንድ ጊዜ የሚደረግ የብር የምንዛሬ ተመን ለውጥ / one time devaluation / ለማድረግ የተደረገ ውይይትም፣ የተወሰነ ውሳኔ ፈፅሞ የለም ” ብለዋል።

የብር የምንዛሬ ለውጥን / devaluation በተመለከተ የተደረገ ውይይት ወይም የተወሰነ ውሳኔ የለም ያሉት አቶ ማሞ ዜጎች በተረጋጋ ሁኔታ በገበያ ስርዓቱ እንዲጠቀሙ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

አቶ ማሞ ምህረቱ ፥ ” በማህበረሰቡ ውስጥ በማህበራዊ ሚዲያ መንግሥት የብር የውጭ ምንዛሬን ለውጥ በማድረግ devaluation ሊያደርግ ነው የሚል ብዙ ወሬ አለ ፤ ይሄን ተከትሎ ገበያ ውስጥ ስካር በሚባል ሁኔታ ሰዎች አንዳንዴ እቃ ይይዛሉ፤ አንደንዴ ደግሞ መሰረታዊ በሚባሉት እቃዎች ላይ አላስፈላጊ የሆነ ዋጋ ይጨምራሉ ከዛም አልፎ የኢኮኖሚ ጥቅም በሌለው ጉዳይ ላይ ያላቸውን ገንዘብ ኢንቨስት ያደርጋሉ ይሄ ፈፅሞ ትክልል ያልሆነና ሊስተካከል የሚገባው ጉዳይ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

ከሰሞኑን በተለይ በመዲናዋ መንግሥት የብር የውጭ ምንዛሬን ለውጥ በማድረግ devaluation ሊያደርግ ነው በዚህም መሰረታዊ እና ሌሎች ቁሶች ዋጋ ሊጨምር ይችላል የሚል ወሬ በስፋት እየተሰራጨ ነበር።
Via Tikvahethiopia

See also  ዕርዳታ - ኢትዮጵያ ጊዜ እየተጠበቀ የምትደቆስበት የስንዴ ፖለቲካ

Leave a Reply