– 240 ሺህ ሚደርሱ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ
በሚቀጥሉት ሁለት ወራት በአገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የሚያስችል ንቅናቄ ሊካሄድ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስቴርን የ2015 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል።
በሪፖርታቸው ትምህርት ቤቶችን በማሻሻል የመማር ማስተማር ሒደቱ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን የማስተካከል ስራዎች ይከናወናሉ ብለዋል።
በመሆኑም በሚቀጥሉት ሁለት ወራት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የሚያስችል የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ትብብር የሚጠይቅ አገራዊ የሕዝብ ንቅናቄ የሚደረግ መሆኑን ገልፀዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ 47 ሺህ አጠቃላይ ትምህርት የሚሰጡ የትምህርት ተቋማት መኖራቸውን ጠቅሰው ያሉበትን ደረጃ በሚመለከት ቀደም ብሎ ጥናት መደረጉን ተናግረዋል።
በዚህም በርካታ ትምህርት ቤቶች የሚጠበቀውን ደረጃ የማያሟሉ መሆናቸው ተረጋግጧል ያሉት ሚኒስትሩ በተባበረ አቅም የትምህርት ቤቶቹን ደረጃ ማሻሻል ያስፈልጋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሟላት ሕብረተሰቡን በማስተባበር በተሰበሰው 11 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር 8 ሺህ 702 ትምህርት ቤቶች ተጠግነው አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን ገልጸዋል።
ዘንድሮ 240 ሺህ ሚደርሱ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ ፡- ትምህርት ሚኒስቴር
240 ሺህ ለሚደርሱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በበይነ-መረብ የመውጫ ፈተና ለመሥጠት መዘጋጀቱን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ኘሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንደገለጹት ÷ በ2015 ዓ.ም በመጀመሪያ ዲግሪ ኘሮግራም ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመሥጠት ብሉ -ኘሪንት ተዘጋጅቷል፡፡
የመውጫ ፈተና የክፍያ ተመን ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱንም ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት አብራርተዋል፡፡
የመውጫ ፈተና ስትራቴጂ ማስፈፀሚያ መመሪያ እና የድርጊት መርሐ-ግብር ዝግጅት መጠናቀቁንም ጠቁመዋል፡፡
በመውጫ ፈተና የሚካተቱ የትምህርት ዓይነቶች ተለይተው በቅድመ-ምረቃ በሚሰጡ በሁሉም የትምህርት መስኮች የፈተና ንድፍ ማሳያ መዘጋጀቱን ማስረዳታቸውን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
OBN
- ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበችአሜሪካ ተቀምጠው የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር እንድታደርግ የፌደራል ፖሊስ መጠየቁ ተገለጸ። በጀርመን በተመሳሳይ ስራ መጀመሩ የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጠየቀች፤ ኤምባሲው ንግግር መደረጉን አስታውቋል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ… Read more: ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበች
- ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷልፈቃድ ሳይኖራቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው ሃሰተኛና የፈጠራ ወሬ ሲያሰራጩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች መያዛቸው ተገለጸ። ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት በህዝብ ጥቆማ እንደሆነ ተመልክቷል። ሐሰተኛ እና አፀያፊ የፈጠራ ታሪክ… Read more: ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷል
- “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረበሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት። ከአርቡ ዓለም፣ ከአውሮፓ፣ ከአፍሪቃ፣ ሩሲያና አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ አካላት የሚዳክሩበት በዚህ ጦርነት የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ መገኘቱ ይፋ መሆኑን ተከትሎ አማራ ክልል… Read more: “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ
- Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?Mercenaries from Ethiopia’s Tigray People’s Liberation Front are fighting alongside Sudanese army regulars against fighters of the Rapid Support Forces (RSF), the paramilitary group is claiming. The RSF which has been battling soldiers of the… Read more: Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?
- Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAFSudanese warring party Rapid Support Forces has officially accused the Tigray People’s Liberation Front Fighters of fighting in Sudan in support of the Sudanese Armed Forces (SAF). Civil war broke out in Sudan in April… Read more: Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAF