በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የተመራ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የልዑካን ቡድን ከጅቡቲ ፕሬዝዳንት እስማዔል ዑመር ጉሌህ ጋር ተወያየ።
በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ እንዲሁም የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ተመስገን ጥሩነህን ያካተተ የመንግስት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከጅቡቲው ፕሬዝዳንት ክቡር እስማዔል ኡመር ጌሌህ ጋር ተገናኝተው በወቅታዊ አካባቢያዊና በሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱም የሁለቱ አገራት ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ታሪካዊ፣ የማይለዋወጥና በማናቸውም የውጭ ኃይል ተፅዕኖ የማይናወጥ መሆኑ ተነስቷል።
የህዘብ ለህዝብ ትሥሥራቸውም በባህልና ቋንቋ ጭምር የተሳሰረና በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑም ተገልጿል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ለፕሬዝዳንቱ ማብራሪያ የሰጠ ሲሆን÷ በመንግስት በኩል በአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ የሚፈጠሩ ችግሮችን በመቋቋም የአገሪቱን ሰላም ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን አብራርቷል።
በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በተለይም በትግራይ ክልል የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ፣ ሰብዓዊ ድጋፎችንም አጠናክሮ የማስቀጠልና መደበኛ የትምህርትና የግብርና ሥራዎችም እንዲጀመሩ የተደረገበት አግባብ መኖሩም ነው የተገለጸው፡፡
የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማዔል ኡመር ጌሌህ በበኩላቸው÷በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል ያለው ግንኙነት ከመቼውም ጊዜ በላይ የተጠናከረ መሆኑን ገልጸዋል።
የሁለቱ ሀገራት ግንኙነትም ታሪካዊ፣ ጠንካራና በማናቸውም የውጭ ተፅዕኖ የማይናወጥ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡
ጅቡቲ ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሮቿን ለመፍታት እያደረገች ያለውን ጥረት አድንቀው÷ የሁለቱ አገራት ትስስር ጠንካራ እንደሆነና መለያየት በማይችል መልኩ የተሳሰረ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በአንዱ አገር ውስጥ የሚፈጠር ችግር ሌላውም ላይ ተፅዕኖን እንደሚያሳድር ፕሬዝዳንቱ በውይይቱ ወቅት አንስተዋል ፡፡
በመሆኑም ትሥሥሩን ይበልጥ ለማጠናከር ጅቡቲ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆኗን ለልዑካን ቡድኑ አረጋግጠዋል፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ኢታማጆር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ከጅቡቲው አቻቸው ጄኔራል ዘካሪያ ጋር ተገናኝተው በሁለቱ የመከላከያ ኃይሎች መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ተወያተዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል ያለው የህዝብ ለህዝብና የመንግስታቱ ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን አንስተው ይህንኑ ግንኙነት በወታደራዊ መስክም ማስቀጠል እንደሚገባ ተወያዮቹ አንስተዋል፡፡
በዚሁ መሠረት በወታደራዊ መስክ የመረጃ ልውውጥ፣ የትምህርትና ስልጠና ትብብር እንዲሁም የልምድ ልውውጦችን ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በሁለቱ አገራት የጋራ ድንበርና የኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደርን ሰላማዊ ቀጠና ከማድረግ አኳያም በትብብር እንደሚሠሩ የተወያዩ ሲሆን በዓመት አንድ ጊዜ የሚካሄድ የጋር ሁለትዮሽ ውይይቶችንም አጠናክረው ለማስቀጠል ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ጅቡቲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ተበዳዮችን ለመካስ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል፡፡… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን