የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሀገራት ኢኮኖሚ ላይ እያደረሰ ያለውን ጫና ለመቀነስ እና ወረርሽኙን ለመግታት እንዲሆን የአለም ባንክ በቅርቡ በተለይ ለታዳጊ ሀገራት የማገገሚያ ድጋፍ ማድረጉ አይዘነጋም።
ከዚህ ውስጥም ኢትዮጵያ ወደ 207 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ ከባንኩ አግኝታለች። ይህንን የአለም ባንክ የኮቪድ 19 ማገገሚያ የድጋፍ ገንዘብ ኢትዮጵያ ለክትባት ግዥ ልታውለው እንቅስቃሴ መጀመሯን ዋዜማ ከመንግስታዊ ምንጮች ስምታለች።
በዚህም መሰረት ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ከተሰኘው ከታዋቂው የአሜሪካ የመድሃኒት አምራች ኩባንያ የኮቪድ 19 ክትባት ለመግዛት ውል እንደፈፀመችም ተነግሯል።
ኢትዮጵያ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኮቪድ 19 ክትባትን ለመግዛት የፈፀመችው ውል 3 ሚሊየን ለሚጠጋ የክትባት ጠብታ (Dose) ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ወደ 4 ሚሊየን የሚጠጋ የአስትራ ዜኒካ ክትባትንም በግዥ ለማስገባት አስፈላጊው ሁሉ እንደተፈፀመ ከጤና ሚኒስቴር ምንጮች ስምተናል።
ኢትዮጵያ ኮቫክስ ከተሰኘው የኮቪድ 19 ክትባትን ለታዳጊ ሀገራት ለማዳረስ በተቋቋመው ጥምረት አማካኝነት በዚሁ አመት መጋቢት ወር ላይ ወደ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ጠብታ (Dose) የአስትራ ዜኒካ ክትባት ተረክባ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ስታዳርስ መቆየቷ ይታወቃል።
ሁለተኛውን ዙር ክትባት ለማዳረስ የሚያስችል የአስትራ ዜኒካ ክትባት በተለይ 391 ሺህ የአስትራ ዜኒካ ክትባትን ሀገሪቱ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከኮቫክስ ጥምረት ትረከባለች ተብሎም እየተጠበቀ ነው። ክትባቱ ምናልባትም በቀጣዮቹ አምስት ቀናት ኢትዮጵያ እንደሚገባም ይጠበቃል።
ከዚህ በተጨማሪም ከነሃሴ እስከ መስከረም ወር ድረስ 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ጠብታ የአሰትራ ዜኒካ ክትባትን ለመረከብ እየተዘጋጀች የምትገኘው ኢትዮጵያ ሰሞኑን ከሚገባው ወደ 400 ሺህ ጠብታ ከሚጠጋው ክትባት ጋር በድምሩ ወደ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ጠብታ ክትባትን እንደምታገኝ ይጠበቃል።
ይህ ደግሞ በመጀመሪያው ዙር የአስተራ ዜኒካ ክትባት የከተበቻቸውን እና አዲስ የሚከተቡ ዜጎቿን በሙሉ ሁለተኛ ዙር የአስትራ ዜኒካ ክትባት ለማዳረስ እንደሚያስችላትም ዋዜማ ራዲዮ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።
- ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበችአሜሪካ ተቀምጠው የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር እንድታደርግ የፌደራል ፖሊስ መጠየቁ ተገለጸ። በጀርመን በተመሳሳይ ስራ… Read more: ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበች
- ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷልፈቃድ ሳይኖራቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው ሃሰተኛና የፈጠራ ወሬ… Read more: ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷል
- “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረበሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት። ከአርቡ ዓለም፣ ከአውሮፓ፣ ከአፍሪቃ፣ ሩሲያና አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ… Read more: “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ
- Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?Mercenaries from Ethiopia’s Tigray People’s Liberation Front are fighting alongside Sudanese army regulars against fighters of the Rapid… Read more: Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?
- Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAFSudanese warring party Rapid Support Forces has officially accused the Tigray People’s Liberation Front Fighters of fighting in… Read more: Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAF