እስካሁን ባለዉ ሁኔታ አገራችንም ሆነ የአማራ ህዝብ ለጦርነት እየተዘጋጁ እንጅ ጦርነቱን በሙሉ አቅማቸዉ አልጀመሩትም። ይህ የሆነበት ምክንያትም የጠላት አሰላለፍ ፍፁም ባልታሰበ መንገድ ጦርነቱን ህዝባዊ ስላደረገዉ አገራችንም ሆነ አማራ በተመሳሳይ መልኩ መዘጋጀት ስለነበረባቸዉ ነዉ። አሁን እንደ ሀገርም ሆነ እንደ አማራ የእዉነተኛዉ ጦርነት ዋዜማ ላይ እየደረስን ይመስላል።
ይሄን ጦርነት እንደ ሀገር በአስተማማኝና በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ያለዉን ስራ እየተመለከትን ነዉ። እንደ አማራም ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ ጦርነቱን ህዝባዊ ለማድረግ እየተሞከረ ነዉ። የሚቀር ነገር ቢኖርም እስካሁን ባለዉ ሁኔታ እየታዩ ያሉ ለዉጦች ቀላል ግምት የሚሰጣቸዉ አይደሉም። በተለይም ጠላት በወረራ በያዛቸዉ አካባቢወች ያደረሳቸዉ ሁለንተናዊ ዉድመቶች ጦርነቱን ህዝባዊ ለማድረግ በአያሌዉ አግዟል። በተለይም ካሁን በሁዋላ እኔ “ጠቤ ከዶ/ር አብይ እንጅ ከናንተ ጋር አይደለም” የምትለዉ የትህነግ ማደናገርያ ለደቂቃወችም አትሰራም።
ሌላዉ ከአማራ አንፃር የተፈጠረዉ አቅም የዛሬ ሳምንትና በዛሬዉ እለት የተመረቀዉ ልዩ ሀይላችን ነዉ። ይህ ሀይል አሁን ያለዉን ወታደራዊ አቅም በትልቁ እንደሚያሳድገዉ ይጠበቃል።
ሌላዉና ጥሩዉ ነገር በአጅሬና ጃኖራ ያለዉ ፋኖ በዛሬዉ ዕለት ከሆነ ቦታ ላይ ተገናኝቶ የደረሰበት ዉሳኔ ነዉ። ይህ ሀይል ከሚመለከታቸዉ አካላት አስፈላጊዉ ድጋፍ ከተደረገለት አንድ ግንባር እንደሚዘጋ ይጠበቃል። በነገራችን ላይ አባ ድፈን መሳፍንትም በዚህ መድረክ ተገኝቶ የሚለዉን ብሏል። በትህነጋዊያን የተወራበት ሞቷል ወሬም ሀሰት መሆኑን በወቅቱ ስልኩን አፈላልገን ለሆነ ቴሌቪዥን ጣብያ እንዲያናግሩት ሁኔታወችን አመቻችተን ነበር። ሆኖም በኔት ወርክ ምክንያት ያገኙት አልመስለኝም። ለሁሉም ይህ የፋኖወች መድረክ እንዲፈጠር ሀሳብ ላካፈልከኝና እዉን እንዲሆን ላደረጋችሁት የቀድሞዉ ሰ/ጎንደር አሰተዳዳሪና ባልደረቦቹ ምስጋና ይገባችሁዋል።
በመጨረሻም እዉነተኛዉ ጦርነት ገና አልተጀመረምና ወጣቶቻችን አሁንም መከላከያን በገፍ ተቀላቀሉ(መከላከያ በቃኝ እስከሚል ድረስ)። መከላከያ የመጨረሻዉ የህልዉናችን ምሽጋችን ስለመሆኑ ይሰመርበት። ወጣቶቻችን ከመከላከያ በተጨማሪ የልዩ ሀይላችንንም በስፋት ተቀላቀሉ።
ጦርነቱ ገና አልተጀመረም!
የትግላችንን መዳረሻ እንዳንዘነጋ!
የገባንበት ጦርነት መዳረሻዉ የኢትዮጵያን ህልዉና በአስተማማኝ ሁኔታ ማረጋገጥ ነዉ። ይህ ሲሆን የአማራም ሆነ የመላ አገራችን ህዝቦች ህልዉና እዛዉ ሳለ ይረጋገጣል። የኢትዮጵያ ህዝቦች ህልዉና ከኢትዮጵያ ህልዉና መረጋገጥ ዉጭ አይታሰብም።
የገባንበት ጦርነት የህልዉና እንደመሆኑ ትግሉ ቀላል አይሆንም። ዉስብስብ፣ፈታኝ፣መስዋትነትን የሚጠይቅ ነዉ። ምን አልባትም ጦርነቱን በሚፈለገዉ መጠንና ፍጥነት ህዝባዊ ካላደረግነዉ ጊዜም ሊወስድ ይችላል።
በአጠቃላይ የዚህ ጦርነት ግብ በአገራችን ላይ የህልዉና አደጋ የደቀነዉን ሀይል በአስተማማኝ ሁኔታ በማሸነፍ የኢትዮጵያን ህልዉና በአስተማማኝ ሁኔታ ማረጋገጥ እንጅ የሆነ ከተማ ወይም ኮረብታ በመያዝ ሊለካ አይገባም። ይህም ሲሆነሰ የዚህን ጦርነት ግብ ለማሳካት የግድ ትግራይ ድረስ መዝመት ላያስፈልግ ይችላል። የጦርነቱን ግብ ደ/ጎንደር፤ሰ/ጎንደር፤ዋግ ወይም ሰ/ወሎ ላይ ማሳካት ይቻላል።
በሌላ አባባል የትህነግን ወራሪ ሀይል ከደ/ጎንደር፤ስ/ጎንደር፤ዋግ ወይም ሰሜን ወሎ አሰወጣነዉ ማለት በዚህ ጦርነት ኢትዮጵያ አሸነፈች፣ የጦርነቱ ግብም ተሳካ ማለት አይደለም። በዚህ ጦርነት ኢትዮጵያ አሸነፈች ፣የጦርነቱ ግብም ተሰካ የምንለዉ ትህነግ ተዋጊና ተላላኪ አልባ ሁኖ ከቀረ ብቻ ነዉ፤ያኔ ኢትዮጵያ አሸንፋለች የጦርነቱ ግብም ተሳካ ብለን አፋችንን ሞልተን እንናገራለን። አሁን የሚገኙት መለስተኛ የአዉደ ዉጊያ ድሎች ወደ ዋናዉ ድል መዳረሻ መንገዶዶች እንጅ በራሳቸዉ ግቦች አይደሉም። ስለሆነም በነዚህ መለስተኛ ድሎች ሳንዝናና እና ሳንዘናጋ ለበለጠ መራራ ትግልና ጣፋጭ ድል መዘጋጀት ያስፈልጋል።
ይልቁንስ የአማራ ወጣት ምንም አይነትት ቅድመ ሁኔታ ሳተነሳ መከላከያ ሀይላችንን/ልዩ ሀይሉን ተቀላቀል።
Chuchu Alebachew