ቀንና ታሪክን ታካ ቻይና በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጣላቃ ግብነት ተቃወመች

 ቻይና የአለምአቀፍ ድንጋጌዎች ጠበቃ፤ ዓለም አቀፍ ፍትሃዊነትን እና ፍትህን በማስጠበቅ ረገድ ቁልፍ ሚና ተጫውታለች ሲሉ ፕሬዚደንት ሺ ዢንፒንግ ገለጹ፡፡ቤጂንግ በተባበሩት መንግስታት የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ሕጋዊ መቀመጫ የተመለሰችበትን 50ኛ ዓመት አከበረች፡፡

በመርሃግብሩ የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግን ጨምሮ÷ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፣ የዲፕሎማቲክ መልዕክተኞች እና በቻይና የሚገኙ የአለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ መንግስት ለተባበሩት መንግስታት የቻይና ብቸኛ ህጋዊ ወኪል መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዚደንቱ÷ ይህም ለቻይና ህዝብ ድል መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

ለ50 ዓመታት የቻይና ሕዝብ የማይታክት መንፈስ እያሳየ በተለዋዋጭ ሁኔታዎች ውስጥ ሆኖም÷ የቻይና ልማት በትክክለኛው አቅጣጫ ላይ በመቆየቱ በሀገራቸውና በሰው ልጅ ልማት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መጻፉን አንስተዋል፡፡

የቻይናንና የኢትዮጵያን ወዳጅነት ጠቁመው÷ ለተባበሩት መንግስታት ውሳኔ 2758 ድምጽ ከሰጡ ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗንም አስታውሰዋል፡፡ሁለቱ አገራት በአለም አቀፍ ግንኙነት ላይ ተመሳሳይ ፍልስፍና የሚጋሩ እና ሁለቱም ነፃ የውጭ ፖሊሲን የሚደግፉ እና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወሙ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ እርስ በርስ በመረዳዳትና በመደጋገፍ ሁለቱ አገራት በአለም አቀፍ እና በክልል ደረጃዎች በቅርበት ሲሠሩ መቆየታቸውን ጠቁመው÷በሰብአዊ መብቶች ሽፋን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ የሚገቡ የውጭ ኃይሎችን ትቃወማለች ብለዋል፡፡

ቻይና የአለምአቀፍ ድንጋጌዎች ጠበቃ ነች ያሉት ሺ÷ ዓለም አቀፍ ፍትሃዊነትን እና ፍትህን በማስጠበቅ ረገድ ቁልፍ ሚና ተጫውታለች ብለዋል፡፡በኢትዮጵያ ከቻይና ኢምባሲ ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው÷ በተባበሩት መንግስታት ውስጥ የቻይና ድምጽ ሁል ጊዜ ለታዳጊው ዓለም መሆኑንም ፕሬዚደንት ሺ መናገራቸውን የመንግስት መገናኛዎች ዘግበዋል።

DONATE US – ቢረዱን አስፍተን ለመስራት አቅም ይፈጥሩልናል

About topzena1 2657 Articles
A journalist

Be the first to comment

Leave a Reply