የሞተች ልጇን ይቅር እንድትል የተጠየቀችው እናት አሻፈረኝ አለች!

ይኽ የኾነው በሳዑዲ ነው። እናት ልጇ በዕድሜ የሚበልጣትን ሰው መርጣ በማግባቷ የተጠነሰሰ ቅሬታ ነው። እናት ለልጄ ይኾናል የምትለውን ሰው አዘጋጅታ ልትድር የነበረ ቢኾንም ልጅ ግን በገዛ ፈቀዷ ይኾነኛል ካለችው ሰው ጋር ትዳር ለመመሥረት ወስና ነበር። በዚህ ምክንያት እናት ልጇን ዓይንሽን ለአፈር በማለት ዘመናት ተቆጥረዋል።

በነዚህ ረዥም የቁርሾ ዘመናት ልጅ በተደጋጋሚ እናቷ ዘንድ እየሔደች በመጠየቅና አውፉታዋን ለማግኘት ብዙ ጥረት ከማድረግ አልቦዘነችም። ተስፋ ሳትቆርጥ ቶሎ ቶሎ እየሔደች ለቅሶ ባጀበው ተማፅኖ ይቅርታን ብትለምንም እናት ወይ ፍንክች! የልጅቷ ባለቤት ሳይቀር ነገሩን ለማርገብ በትዳር ውስጥ ያፈሯቸውን ልጆች እያስከተሉ ቢሔዱም የእናትን ልብ ማራራት አልቻሉም።

ነገሮች በዚህ ድባብ ውስጥ እያሉ ይቅርታ የተነፈገችው ልጅ በብርቱ ካንሰር ዱኒያን ለመሰናበት ተገደደች። ከብዙ ስቃይ በኋላ ሕይወቷ አለፈ። የልጅቷ መሞት የእናትን ልብ ያርዳል ተብሎ ቢጠበቅም ነገሩ የተገላቢጦሽ ኾነ። “ሞታም አልምራትም” ያለችው እናት ብዙዎችን አስደንግጣለች።

በብዙ ሽምግልና እና በቅርብ ሰዎች ብትለመንም ይቅርታ እንደማታደርግ አሳውቃለች። በሥፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ነገሩን “ልብ ሰባሪ” ሲሉ ገልፀውታል። “እናት ልጇን አልምርም ስትል ማየት ይከብዳል” ይላሉ።

በነገሩ ግራ የተጋቡት ቀባሪዎች አስከሬኗን ወደ እናቷ ቤት ወስደው ልቧን ለማራራት ቢሞክሩም ሳይሳካ ቀርቷል። በሕይወት ሳለች የእናቷን ይቅርታ ለማግኘት ስትጥር የኖረችው ሴት ከተሰበረው ልቧ ጋር ተቀብራለች።

© መረጃውን ያገኘነው ከአል-አረቢያ ነወ Via Ahemed

See also  "ተሳበ ተበተነ ተመታ" ትህነግ ቆቦን በመያዙ ለምን አልፈነደቀም? መከላከያ በሌላ ግንባር እያጠቃ ነው

Leave a Reply