የኢትዮጵያ ጦር ከላይሊበላ ወደ ሰቆጣ እየገሰገሰ ነው፤ ትህነግ ” ወደ መቀለ እንዳይገቡ አስጥሉኝ” አለ

“የነቀለና መተማመኛ ምሽጉ የተሰበረበትን፣ በሽንፈት እግሩ የተነቀለን ሃይል እየተከታተሉ ድልን በድል ማጀብ ነው” እንደሚገባ ወታደራዊ ባለሙያዎች አስተያየት እየሰጡ ባለበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ሃይሎች ታሪካዊዋንና ቅዱሷን ላሊበላን መቆጣተሩን መንግስት ይፋ አድርጓል። ወደ ሰቆጣ እየገሰገሰ እንደሆነም ተመልክቷል። ትህነግ ” የድረሱልኝ ” ጥሪ ማቅረቡ ተሰማ።

የጋሸናን ግንባር ምሽጎች ሰብረው የአሸባሪውን አከርካሪ የሰበሩት የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ታሪካዊቷን የላስታ ላይሊበላ ከተማንና የላይሊበላን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን መቆጣጠሩን ይፋ ያደረገው የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ነው።

በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙባትን የላይሊበላ ከተማንና ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያውን ለመቆጣጠር የተቻለው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሪነት በየግንባሩ የተጀመረው ማጥቃት ውጤት ለማስመዝገብ በመቻሉ እንደሆነ፣ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ የላስታ ላሊበላን አካባቢ በማጽዳት የሰቆጣ ከተማን ለመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሡ ነው ብሏል።

“ራሳቸውን በጠላት እንዳላስደፈሩት የግዳንና የራያ ወረዳዎች ሁሉ ቀሪዎቹ በወረራ ሥር የሚነገኙ የዋግ ሕምራ፣ የሰሜንና የደቡብ ወሎ ሕዝብ፣ ከጀግኖቹ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ጠላትን እንዲደመስስና ነጻነቱን እንዲያስከብር መንግሥት ጥሪ ያቀርባል” ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።

በሌላ ዜና አሸባሪው ህወሓት ለተባበሩት መንግስት ድርጅት፣ ለአሜሪካ ለአውሮፓ ህብረት፣ ለአረብ ሊግ “የድረሱልኝ”ደብዳቤ መፃፉን አልጀዚራ አረብኛ መዘገቡን ሱሌማን አብደላ ዘገባውን ወደ አማርኛ መልሶ ካሰራጨው ዜና ለመረዳት ተችሏሎ። ህወሓት ለአሜሪካና ለአውሮፓ ህብረት፣ እንዲሁም ለተመድና የአረብ ሊግ አገራት በላከው ደብዳቤ የኢትዮጵያ መንግስት ለአስቸኳይ ድርድር እንዲቀመጥና፣ ወደ ትግራይ ክልል እንዳይገባ ጫና እንዲያደርጉለት መጠየቁን ሚስጢር ሰማሁ ሲል አልጀዜራ አመልክቷል።

“አልጀዚራ ከአንድ የአሜሪካ ዲፕሎማት አገኘሁት” ባለው መረጃ “የህወሓት ሚስጥራዊ ደብዳቤ ላይ የአረብ ሊግን ጨምሮ የአውሮፓ ህብረት አሜሪካና ተመድ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጠንካራ አቋም ይዘው ጫና እንዲያደርጉለት ተማፅኗል” የሚል ዘገባ ሰርቷል።

ከኢትዮጵያ መንግስት በተጨማሪ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ ኢራን፣ ቱርክና ሩሲያ ለኢትዮጵያ መንግስት የሚያደርጉት ወታራዊ ድጋፍ እንዲያቆሙ ደብዳቤ የላከላቸው አገሮች እና ተቋሞች ጫና እንዲያደርጉለት መጠየቁንም ዘገባው ያስረዳል።

See also  ከሃገር ለመውጣት የሞከሩ 60 ወጣቶች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ

Leave a Reply