በኮምቦልቻ ከተማ በ16 ዋና ዋና መግቢያና መውጫ በሮች በርካታ ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል


– ወሎ ዩንቨርስቲ ግቢ ውስጥ ገብተው የተገኙ የህወሃት ዘራፊዎች በአየር ወለዶች ተለቀሙ

በኮምቦልቻ ከተማ በ16 ዋና ዋና መግቢያ እና መውጫ በሮች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የ02 የሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት ሃላፊ ኢንስፔክተር ሰብስቤ ኪዳነማርያም ገለጹ።

ኢንስፔክተሩ በሥፍራው ለሚገኙት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች እንደገለጹት፣ በከተማዋ በ16 ዋና ዋና በሮች ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ነው። በዚህም በውል ያልታወቁ በርካታ ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል።

ኢንስፔክተር በከተማዋ ከ25 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ተጠልለው እንደሚገኙ ጠቁመው፤ በተፈናቃይ ስም የአሸባሪ ቡድኑ ሰርጐ ገቦች እንዳይገቡ ፍተሻ እየደረገ ነው ብለዋል።

ህዝቡ በወሬ ሳይሸበር አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅ ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪዎች መደበኛ የሆነ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎቻቸውን እያከናወኑ መሆኑን ዘጋቢዎቻችን በከተማዋ ባደረጉት ቅኝት ተመልከተዋል።

ወሎ ዩ ንቨርስቲ ግቢ ውስጥ ገብተው የተገኙ የህወሃት ዘራፊዎች በአየር ወለዶች እየተለቀሙ ነው የደሴ ከተማ አሁንም በተለመደ እንቅስቃሴዋ ላይ ትገኛለች፡፡

አሸባሪው የትህነግ ቡድን ዛሬም በሐሰት ፕሮፖጋንዳው የደሴ ከተማ ነዋሪዎችን በወሬ ለመፍታት ቢሞክርም አልተሳካለትም፡፡

በከተማዋ ሰርገው ለመግባት የሞከሩ የአሸባሪው ቡድን ተላላኪዎች መያዛቸውንና አሁንም የከተማዋ ወጣቶችና ሕዝቡ ከወገን ጦር ጋር በመሆን እየተከታተለ መሆኑን ገልጸውልናል፡፡

ጀግናው መከላከያና መላው የጸጥታ ኃይል የአሸባሪ ቡድኑን አባላት በመልቀም ርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝና ቦሩ ሜዳም ሆነ ከቦሩ ሜዳ ራቅ ያሉት አካባቢዎች በጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ውስጥ መሆናቸውን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አግልግሎት አስታውቋል፡፡

Leave a Reply