በአዲስ አበባ ባሳለፍነው ዓርብ በአርሂቡ ሪል ስቴት ሕንጻ ግንባታ ሥራ ላይ የነበሩ 3 ሠራተኞች ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ የሕንጻው ግንባታ እንዲቆም መደረጉን የከተማዋ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡ የህግ ጥያቄም እንደሚነሳበት ተመልክቷል ፋና እንዳለው ባለስልጣኑ ጉዳዩን አጠንክሮ ይዞታል።
የባለስልጣኑ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ ባሳለፍነው ዓርብ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 6 በጅምር ግንባታ ላይ የሚገኝ ባለ 9 ወለል የአርሂቡ ሪል ስቴት ሕንጻ ግንባታ ሥራ ላይ የነበሩ 3 ሠራተኞች ሕይወት አልፏል፡፡
ሠራተኞቹ ሲሚንቶ ወደ ላይ የሚያወጡበት ጋሪ የተሸከመው የብረት ገመድ በመታጠፉ የብረት ገመዱን ለማስተካከል በእጃቸው ይዘው በሚያንቀሳቅሱበት ወቅት በአቅራቢያው ከነበረ የኤሌክትሪክ ገመድ ጋር በመገናኘቱ ከሕንጻው ወደ መሬት ወድቀው ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።
ተጨማሪ አንድ ሰራተኛ ወደ ሕክምናተቋም መወሰዱን ያብራሩት አቶ ገዛኸኝ÷ሶስቱ ሠራተኞች ግን ወዲያውኑ ሕወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።
የደረሰውን አደጋ ተከትሎም ሕንጻው የግንባታ እንቅስቃሴውን እንዲያቆም መደረጉን ነው ያስታወቁት፡፡
ከዚህ ባለፈም የሕንጻው ባለቤት፣ የአማካሪውንና የተቋራጩን የግንባታ ፈቃድ በመያዝ ከአደጋው ጋር በተያያዘ ማብራሪያ እንዲሰጡ መታዘዛቸውን ገልጸዋል።
በሕንጻ አዋጅና መመሪያ መሰረት ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቁመው÷ለጠፋው ሕይወትም በሕግ እንደሚጠየቁ አክለዋል ፡፡
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከሃምሳ ሺህ በላይ ማሻቀቡ ይፋ… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙንna ለዚህም ተግባራዊነት ከሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊየን በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን ተገለጸ። 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ህብረቱ አረጋግጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ በህብረቱ ስም የወጣው ዜና ሃሰት፣ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን መንግስት አስታወቀ። መረጃው ቀድሞውንም ዜናው “ሴራ” ነው በሚል… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ህብረቱ አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን ምኑ ነው አፍሪካ ህብረትን ስጋት ላይ ጥሎት አካውንቱን… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑም ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል የዕዳ ጫናን ለማቃለል… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል