በሚነሶታ፣ ሴንት ሉዊስ ፓርክ፣ የ27 ዓመቷ ትውልደ ሶማልያዊት ናድያ መሐመድ ከሰሞኑ በከንቲባነት ተመርጣለች፡፡
በአሜሪካ የኢትዮጵያ ስደተኞች ታሪክ ወደ 70 ዓመት እየተጠጋው ነው። እስካሁን ግን በአሜሪካ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ውስጥ እንኳን በተመራጭነት በመራጭነትም ተጽዕኖ የለውም። ንግዱ ከኢትዮጵያ ምግብ ቤትና ከሰቨን ኢለቨን፣ ሥልጣኑም ከፓርኪንግ ኃላፊነት ብዙም አይዘልም። እንዲያውም በትምህርት የገፉት ምሁራን የተሻለ አካዳሚያዊ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ለምን? ብሎ መጠየቅ ይገባል።
አሜሪካ ከተመሠረተው በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ማኅበር (ESUNA) ጀምሮ የአሜሪካ ዳያስፖራ ስንቱን ንቅናቄ፣ ስንቱን ፓርቲ፣ ስንቱን ታጣቂ ደገፈ? በኢትዮጵያ ላይ ዘላቂ ሰላም፣ የጸና ዴሞክራሲ እና ሁለንተናዊ ብልጽግና ማምጣት ግን ችሏል? መገምገም አለበት፡፡ የስቴት ዲፓርትመንት እና የዋይት ሐውስ አጥሮች ፊት ለፊት ላለፉት 70 ዓመታት የተደረጉ ሰልፎች ምን መሠረታዊ ለውጥ አመጡ? ተመርጠንና መርጠን ውሳኔ ሰጪ ከመሆን ይልቅ ለምን ውሳኔ ለማኞች ሆንን?
ለእኔ አንዱ ዋና ምክንያት ሰዎቹ አሜሪካ ገቡ እንጂ፣ አሜሪካ እነርሱ ውስጥ ስለሌለች ይመስለኛል። በዚህ የተነሣም አሜሪካ ሆነው ስለ አሜሪካ ከሚያስቡ ይልቅ አሜሪካ ሆነው ስለ ኢትዮጵያ ቢያስቡ ይቀላቸዋል፡፡ ያውም በኢትዮጵያኛ፡፡
እዚያ የገቡት ብዙዎቹ ሥልጣን ሲባል አራት ኪሎ፣ ቤት ሲባል ቦሌ፣ ንግድ ሲባል ፒያሳ የሚታያቸው ናቸው። ካፒቶል ሂልና ዎል ስትሪት አይመጡላቸውም፡፡ የሪፐብሊካንና የዴሞክራት ፓርቲ አባል ከመሆን ይልቅ የኢሕአፓና የቅንጅት፣ የአማራጭ ኃይሎችና የኅብረት ፓርቲ አባል መሆን የሚያረካቸው ናቸው። የሚያቋቁሟቸው የማኅበረሰብ(ኮሙኒቲ) ተቋማት በአሜሪካ ማኅበረ ፖለቲካ ውስጥ ተጽዕኖ ለመፍጠር ሳይሆን መቶ ሐበሻ ሰብስበው ሊቀ መንበር ለመሆን ያለሙ ናቸው። በግራንትና በማኅበረሰብ አገልግሎት ድጋፍ ከአሜሪካ መንግሥት የሚገኙትን ረብጣ ገንዘቦች ትተው የሀገራቸውን ሰው መዋጮ ለመካፈል ይተጋሉ።
እስካሁን ድረስ የአሜሪካ የአንዷ ትንሽ ከተማ ከንቲባ ለመሆን እንኳን ምኞትና ጥረት የላቸውም። በአሜሪካ የፓርቲ መድረክ አይመዘገቡም፤ አይወዳደሩም። ትልቁ የአሜሪካ የፖለቲካ ባሕር እያለላቸው በመንደር ኩሬዎች ውስጥ ሲንቦጫረቁ የሚኖሩ ናቸው። የአሜሪካን የሥልጣን ቦታዎች እንደ ሌሎቹ ማኅበረሰቦች በቅተውና ነቅተው ከመያዝ ይልቅ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣን አልተሰጠንም ብለው ያኮርፋሉ፡፡
“ይሄንን ያህል ድምጽ ሰጪ አለን፤ ምን ልታደርጉልን ትችላላችሁ” ብለው ከአሜሪካ ተመራጮች ጋር አይደራደሩም። ከዚያ ይልቅ አንድ የሴኔትና የኮንግረስ አባል አናግረው ፎቶ በመነሣት ትልቅ ጀብዱ እንደሠሩ ይቆጥራሉ። ዕውቀታቸውን፣ ገንዘባቸውንና ጊዜያቸው አሰባስበው፣ ተደራጅተውና ነቅተው የአሜሪካን ፖለቲካ ቢዘውሩ ኖሮ በኢትዮጵያ እንዲመጣ የሚፈልጉትን ለውጥ ከ70 ዓመት ባጠረ ጊዜ ያመጡት ነበር፡፡ እነርሱ ግን እዚህም እዚያም ለሚነሣ ሽፍታ ገንዘብ በመላክ፣ የተዳከሙና በብሽሽቅ የተሞሉ ሚዲያዎችን በመክፈት፣ ከዕለታዊ ስሜት የማያልፉ ሰልፎችን በማድረግ ልባቸው ውልቅ ይላል፡፡ ዳያስፖራውም ለ99ኛ ጊዜ ገንዘቡን ቢበላም ለመቶኛ ጊዜ እንደገና ለመበላት አሁንም ዝግጁ ነው፡፡
ከኩባውያን፣ ከእሥራኤላውያን፣ ከላቲኖዎች፣ ከሕንዶች፣ ከሶማልያውያን፣ ከግብጻውያን አይማሩም። እነርሱ እየተደራጁና የአሜሪካን የፖለቲካ መሥመር እየተከተሉ ኮንግረስ ይገባሉ፤ ለሴኔት ይመረጣሉ፤ የከተሞች ከንቲባ ይሆናሉ፤ የግዛቶች ገዥ ይሆናሉ፤ የአካባቢ ምክር ቤት አባል ይሆናሉ። ያንን ባይችሉ እንኳን ትርጉም ያለው ድምጽ ሰጪ ማኅበረሰብ ይፈጥራሉ። ለራሳቸውም ለሀገራቸውም የፖሊሲ ለውጥ ያመጣሉ። ኩባውያን በፍሎሪዳ ግዛት በሚደረግ ምርጫ ዋነኞቹ ተጠባቂዎች ናቸው፡፡ የአሜሪካን የፕሬዚዳንት ምርጫ እስከ መወሰን ይደርሳሉ፡፡ ላቲኖዎች በደቡባዊ የአሜሪካ ግዛቶችና በካሊፎርንያ ዋነኞቹ የምርጫ ድምጽ ወሳኞች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያውያንስ
በኢትዮጵያውያን የተቋቋሙ ከ600 በላይ አደረጃጀቶች በአሜሪካ ውስጥ አሉ። የሁሉም ማለት በሚቻል ሁኔታ ዓላማቸው አሜሪካን ለኢትዮጵያውያን ማመቻቸት ወይም አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ በጎ ተጽዕኖ እንድታሳድር በአዎንታ ማስገደድ አይደለም። ሲጀመር በዘር ይከፋፈላሉ። ሲቀጥል በሥልጣን ይጣላሉ፤ ሲሠልስ አባሎቻቸው መብታቸውን የሚጠይቁና ግዴታቸውን የሚወጡ አይደሉም። ጠብ ካልተፈጠረ አይሰበሰቡላቸውም። አንዳንድ ሰዎችም አምስቱንና ስድስቱን ድርጅቶች በሊቀ መንበርነት ይመሯቸዋል። ላለፉት ሃምሳ ዓመታት የአሜሪካ ዳያስፖራን የፖለቲካ መድረክ የሚመሩት ፊቶች ከ13 አይበልጡም፡፡ አይሰለችም እንዴ?
ፖለቲካው ሤራ፣ ስም ማጥፋትና አጭበርባሪነት ስለተጠናወተው ጨዋዎቹ ዳያስፖራዎች ወይ አርፈው ተቀምጠዋል ወይም ከማኅበረሰቡ ሸሽተዋል። ይሄም በአሜሪካ የኢትዮጵያውያን ፖለቲካ በዐቅመ ደካሞች እንዲዘወር አድርጎታል። ዐቅመ ደካሞቹ ደግሞ በአሜሪካ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መድረኮች ላይ ችለው እንደማይፎካከሩ ያውቁታል። ሐሳብን በሐሳብ መሞገት፣ በተሻለ ፖሊሲ ተከራካሪን መርታት፣ በምርጫ የቁመና ፖለቲካ ማሸነፍ የሚባለውን አይችሉትም፡፡ በዚህ የተነሣ ‹ከእገሌ ምብ ቤት አትብሉ፣ የእገሌን እንጀራ አትግዙ፣ ከእገሌ ሱቅ አትገኙ፣ ከእነ እገሌ ቤተ ክርስቲያን አትሂዱ› የሚለውን ተዋርዶ የሰባ ዓመት የዳያስፖራ ፖለቲካ ታሪካችን ዋና መገለጫ እንዲሆን አድገውታል፡፡ አሠራራቸው “ጓደኛው ሲያቅተው ወደ ሚስቱ ዞረ” ዓይነት ነው። የአሜሪካው ፖለቲካ ሲያቅታቸው በሐበሻው ላይ መረባረብ።
ይሄ ላለፉት ሰባ ዓመታት ያልተነቀለ የዳያስፖራ ፖለቲካ ጥንተ አብሶ፣ ዳያስፖራውንም ኢትዮጵያንም የጎዳ የወረደ የፖለቲካ ባህል ነው፡፡ እያለፈ ያለው ትውልድ ይሄንን አይነቅለውም፡፡ ይሄንን ለመንቀል ዐቅሙም፣ በራስ መተማመኑም፣ ባህሉም የሚኖረው የዳያስፖራው ሁለተኛና ሦስተኛ ትውልድ ነው፡፡
እነ መሊክ አምበር በሕንድ፣ የሱርማዋ ወጣት በኦማን፣ ቢላል በመካ፣ 15ኛው ሥርወ መንግሥት በግብጽ እንደሆኑት፣ አዲሱ የአሜሪካ የዳያስፖራ ትውልድም አሜሪካን በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ መስኮች ከሚመሯት ወገን እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። አሜሪካ ተወልዶ፣ በአሜሪካ ሥርዓት አድጎ፣ የአሜሪካን ማኅበረ ፖለቲካ ተረድቶ እያደገ ነው፡፡ ወላጆቹ የሚራኮቱበት መንደሬ ፖለቲካ ያንስበታል፤ ይወርድበታል፡፡ አይመጥነኝም ማለት ጀምሯል፡፡ ሀገሬን ቅጡልኝ፣ ሀገሬን አስፈራሩልኝ ከሚለው የታክሲ ተራ ፖለቲካ ተመንጥቆ በአሜሪካ የፖሊሲ ውሳኔ የሚሳተፍና ራሱ ለሀገሩ የሚወስን ንቁ ዜጋ ይሆናል።
፸ ዓመት በቃ ይላል፡፡
- ሰው ሰራሽ ቦይ በመገንባት ቀይ ባህርን መቀላቀል የኢትዮጵያ ሌላ አማራጭ?አርተፊሻል ቦይ በመገንባት ቀይ ባህርን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ኢትዮጵያ የባህር በር ሊኖራት ይችላል፤ ይህ በአለም ላይ በኢትዮጵያ የአፋር ምድር ረባዳነት የተነሳ ተፈጥሮ የሰጠው እድል ነው! በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል አርተፊሻል ቦይ በመስራት ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት መሆን ትችላለች፡፡ እንደዚህ አይነት አጋጣሚ ሊፈጠር የቻለው፤ የኢትዮጵያ የአፋር ቦታ ከባህር ወለል በታች እስከ 110 … Read moreContinue Reading
- ብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ቁጥጥሩን አጠንክሮ እንደሚገፋበት አስታወቀ፤ ህገወጥ የወርቅ አዘዋዋሪዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጀ በአገሪቱ የሚታየውን የዋጋ አለመረጋጋት ለመግራት የግንዘብ ስርጭት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ የተጀመረው ስራ ውጤት እያሳየ መሆኑ ተመለከተ፤ ተጠናክሮ ክምሩ እንደሚሰራበትና ግሽበትን በዓመቱ መጨረሻ 20 ከመቶ ለማድረስ መታቀዱ ተሰማ። ህገወጥ የወርቅ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና የማበረታቻ መደረጉ ለውጥ ቢያሳይም በቂ እንዳልሆነ ተመለከተ። … Read moreContinue Reading
- የኮሚሽኑ የቀድሞ ሠራተኞች ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የሙስና ክስ ጋር ተያይዞ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ውድቅ ሆነየአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የቀድሞ ሠራተኞች ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የአልባሳት ግዢ ጋር ተያይዞ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ውድቅ ተደረገ። ተከሳሾቹ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ ውድቅ ያደረገው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ … Read moreContinue Reading
- መንግስት የነዳጅ ድጎማን በህገወጥ መንገድ ሲጠቀሙ ነበሩ ያላቸውን 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከስርአቱ አስወጣ፣ የሰርቁትን ይከፍላሉየታለመለት የነዳጅ ድጎማን ላልተገባ ዓላማ ሲጠቀሙ የነበሩ 40 ሺህ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ ስርዓቱ እንዲወጡና ዕዳ እንዲከፍሉ መደረጉን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለጹ። ሚኒስትሯ ይህን ያሉት የመንግሥት የ2016 የመጀመሪያ የሩብ ዓመት አፈጻጸም በተገመገመበት ወቅት ነው። የግምገማው ተሳታፊዎች መንግሥት የነዳጅ ድጎማን ጨምሮ በርካታ የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋገጡ ተግባራትን ማከናወኑን አድንቀው፤ ሆኖም” ድጎማው … Read moreContinue Reading
- በዓመት አምስት ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ የሚያመርተው ፋብሪካ ከመጋቢት በሁዋላ የሲሚንቶ ዋጋ ወደ ነበረበት የሚመልሰ ነውበቀን 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ እንዲያመርት እቅድ ተይዞለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ እየተገነባ ያለውን የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የግንባታ በመጋቢት ወር ይጠናቀቃል። ምርቱ በተባለው ወር ሲጀምር የሲሚንቶ ዋጋ አሁን ካለበት በግማሽ እንደሚወርድ ይጠበቃል። ከመጋቢት በሁዋላ ፋብሪካው በ50 በመቶ የሲሚንቶ እጥረቱን ያስወግዳል። ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ኩባንያ … Read moreContinue Reading