ስለ ልደቱ ሰላይነት የአይን እማኝ ምስክርነት- እስከ ዛሬ አፍኜ ይዤው ነበር

ሰላም ወገኔ ባላውቅህም ከምትጽፋቸው በመነሳት ቁስለትህ ተሰማኝ በማለት ይጀምራል የተላከልኝ ምስክርነት፡፡ እኛ የደህንነት ሰዎች በስራ አጋጣሚ ያገኘናቸውን መረጃና ማስረጃዎች አደባባይ ለማውጣት የሙያ ስነ ምግባራችን ስለማይፈቅድ ይህን ጉዳይ እስከ ዛሬ አፍኜ ይዤው ነበር፡፡ነገር ግን አሁን አንድም ነገሮች በብዙ መልኩ ስለተለዋወጡ ሁለትም የአንተ ቁስለት ውስጤ ዘልቆ ስለተሰማኝ ለአንተ ልነግርህ ህሊናዬ አስገደደኝ፡፡


አንድ ቀን ቲዎድሮስ አደባባይ ዝቅ ብሎ ኤክስትሪም ሆቴል በር ላይ ጃኬት የለበሰና ካኪ ፖስታ የያዘ ይጠብቅሀል ምንም መነጋገር የለም ተቀብለህ ብቻ ና ተብዬ ታዘዝኩ፡፡ሄድኩ አገኘሁት ፤ አላውቀውም አያውቀኝም፡፤ፖስታውን ስቀበለው ፊቱን ሊሸሽገኝ ሞከረ፤ያው የእኛ ስራ የአይጥና ድመት ጨዋታ አይደል፤እኔም በአንድ ጨረፍታ በአይኔ ፎቶ አነሳሁት፡፡


በምርጫ 97 የምርጫ ክርክር ላይ ያንን ፊት ሳየው ተገረምኩም ደነገጥኩም፡፡ልደቱ ነበር፡፡ከዛ ነገሮችን በግሌ ማጣራት ጀመርኩ ይልና ስለ ልደቱ ከቤተሰቡ ጀምሮ ይዘረዝራል፡፡እኔ ለዚህ ገጽ በሚመጥን መልኩ አሳጥሬ በነጥብ ላቅርበው፡፡
1-ልደቱ በልጅ ወሬ አቀባይነት ደረጃ የተመለመለው ደሴ ታክሲ ሲነዳ ነው፤፡የታክሲ ሾፌር በየቀኑ ከብዙ ሰው ጋር ስለሚገናኝ ለስለላ ስራ ተመራጭ ነው፡፡ ግን ይህ ብቻ በቂ አይደለም፤ አስተዳደጉ ማህበራዊ ህይወቱ ሁሉ ይጠናል፤ልደቱ ተስማሚ ሆኖ ተገኘ እና ተመለመለ፤ የወሎ ቅርንጫፍ ደህንነት ሀላፊ ለነበረ ዬሱፍ ለሚባል ሰውም መረጃ ማቀበል ጀመረ ፣


2-በወቅቱ የደሴ ህዝብ ወያኔን አልተቀበለ ስለነበረ የልደቱና መሰሎቹ ስራ በጣም ወሳኝ ነበር፡፡ እናም ታክሲ እየነዳ የሚያቀብለው መረጃ ጠቀሚ ሆኖ በመገኘቱና የእኛም መስሪ ቤት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን መሰለል ስለፈለገ በወቅቱ አዲስ አበባ በሚኖርና ፍትህ ሚኒስትር ውስጥ ዓቃቤ ህግ በነበረ ሰው አማካኝነት መንግሰታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ እንዲቀጠር ተደረገ፡፤


3- በስራው ብቃት እያሳየ የመጣው ልደቱ ወደ አዲስ አበባ ተወስዶ ከአቶ ኢሳይያስ ጋር እንዲገናኝ ተደርጎ የወኪል ስልጠና ተሰጠው፡፡የተፈለገው የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ገብቶ እንዲሰልል ስለነበረም የፖለቲካ ስልጠና በእነ በረከት አማካኝነት ወሰደ፡፡ይህ ብቻ ግን በቂ አልነበረም፡ የታሰበው ፕ/ር ኣሥራት ይመሩት የነበረው መአህድ ውስጥ እንዲገባ ስለሆነ ምንም የማይቸግረው በደህና የኑሮ ደረጃ የሚኖር ለማስመሰል በአአ ጦር ኃይሎች አካባቢ ቤት ተገዛለት፡፡ የዱባይ ነጋዴነት ሽፋንም ተሰጥቶት፡፡መአህድ ገባ፡፡

See also  ‹‹ በምርጫው ሂደት በጥላቻ ንግግር ላይ የሚሰማሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አመራርና አባላትን በህግ የመጠየቅ ስራ ይሰራል›› አቶ አወል ሱልጣን በጠ.አ. ህግ የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ


4-እዛ በሚገባ ስራውን እየሰራ ሳለ ደህንነት ነው ሰርጎ ገብ ነው የሚሉ ወሬዎች ሲበዙ ይህን ለማክሸፍ ስደተኞችና ከስደት ተመላሶች ቢሮ እንዲሰራና የድርጅቱን መኪና እዬያዘ መአህድ ቢሮ እንዲሄድ እዛ ተቀጠርኩ እያለም እንዲያወራ ተደረገ፡፡ትንሽ ቆይቶም ቤቱ አላማረኝም የደህንነት ይመስላል መቀጠል አልፈልግም በማለት ወሬውን አንዲነዛ ተደረገ፡፡ከዛም ተባረረ ተባለ፤እሱም ያሉኝን ስላልተቀበልኳቸው የሙከራ ጊዜየን ስጨርስ አስወጡኝ ብሎ አስወራ፡፡ ብዙዎችንም አሳመነ፡፡ ( ይገርማል እኔም ይህን ነገር በማመን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከሰዎች ጋር ስከራከር ነበር)


5-ልደቱን በማንኛውም ጊዜ ያገኙት የነበረው ከህወሓት የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ብቻ ሲሆኑ እሱም የአማራ ወይም የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ሰዎች እንዲያገኙት አይፈልግም ነበር፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ከልደቱ ጋር የሚገናኙት 1ኛ ፣ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ 2ኛ፣ ወልደስላሴ ወ/ሚካኤል 3ኛ፣ ጋይም የሚባል ነበሩ፡፡ ይልና ይህ ሰው ልደቱን የማግኘት አጋጣሚው እንዴት እንደተፈጠረ ሲገልጽ፤


6– ወሩ ትዝ አይለኝም ጊዜው 1990 ዓ.ም ነው፤ ኢሳያስ ወደ አድዋ ሄዶ ነበር፡ ጋይም ደግሞ ወላጅ እናቱ በመሞታቸው ወደ አክሱም ሄደ ፤የቀረው ወልደስላሴ ደግሞ ለመዝናናት ወደ ሶደሬ አቅንቷል፡፡ በልደቱ እጅ ላይ መረጃ አለ ግን ሶስቱም ሊያገኙት በሚችሉበት ደረጃ አይደሉም፤በመሆኑም ወልደስላሴ በራዲዮ እኔን አዘዘኝና እና ይህን ጉድ ለማወቅ አበቃኝ፡፡


7- ልደቱ በደህንነት መስሪያ ቤቱ ውስጥ እያደገ ሲሄድ ኑሮውም አኗኗሩም መኖሪያ ሰፈሩም መቀየር ነበረበትና ጦር ኃይሎች አካባቢ የተገዛለትን ቤት እሸቱ በዳኔ ለተባለ ሰው በመሸጥ እነ በረከት ባቦጋያ አካበቢ መሬት እንዲሰጠው አድርገው አሁን የሚኖርበት ቤት ተሰራለት ፣ ጠንካራ ሽፋን እንዲኖረው በመፈለጉ በሸህ ሁሴን አላሙዲን የገንዘብ ድጋፍ አስመጭና ላኪ እንዲሆን ተደረገ ፣ ባለሀብት እንዲባልም በላሊበላ ግምቱ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ሎጅ እየገነባ ይገኛል ።
እውነተኛ ኢትዮጵያዊ የሆናችሁ እንደዚህ ወገኔ የምታውቁትን ተንፍሱ

By tamrat tarekegne Facebook

Leave a Reply