ቁጥራቸው ሶስት መቶ ሃያ የሚሆን የአሸባሪዎች ሃይል በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ መደምሰሳቸው ታወቀ። ይህ ሃይል የተደመሰሰው ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ሲንቀሳቀስ በምስል መረጃ ክትትል ተደርጎበት እንደሆነ ታውቋል።

ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በገነባቸው ዲጂታል ቴክኖሎጂ የሚደገፈው የእግረኛ ሰራዊት ይህ ሱዳን እየሰለጠነ ካለው የትህነግ ሃይል ሶስት መቶ ያህሉ ወደ ኢትዮጵያ ክልል ሲገባና አመቺ ቦታ ላይ ሲደርስ ከቦ እንደደመሰሰው ለኦፐሬሽኑ ቅርብ የሆኑ አመልክተዋል።

የኦሮሚያ ብልጽግና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ ታዬ ደንደዓ ዝርዝሩን ባይገልጹም ሶስት መቶ ሃያ የህወሃት አሸባሪዎች ሱዳን ሰልጥነው ወደ ወልቃይት ሲገቡ ሙሉ በሙሉ ተደምሠዋል” ሲሉ አስታውቀዋል። አቶ ታዬ እንዳሉት ይህ የተደመሰሰው ሃይል የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት መለያ ለብሶና ተመሳስሎ ወገንን ለማጥቃት ያቀደ እንደነበር አመልክተዋል።

“ጁንታዉ ራሱን እንደገና ለማቋቋም በሱዳን አሸባሪዎችን አሠልጥኗል! በትንሹ 320 አሸባሪዎችን በወልቃይት በኩል የመከላከያን ዩኒፎርም አልብሶ ለማስገባት ሞክሯል። ጀግናዉ መከላከያችን ትላንት ሁሉንም ደምስሷል። ድሉ ደግሞ አሸባሪዉን በተግባር ከመደምሰስ ይዘላል። በዋናነት ጁንታዉ የመከላከያ ሰራዊታችንን መስሎ የሠራቸዉን ድራማዎች ያጋልጣል። በትግራይ ወገኖቻችን ላይ ዝርፍያ፣ ግድያና አስገድዶ መድፈር ሲፈፅም የከረመዉ አሸባሪዉ ህወሀት ያሰማራዉ ወንበዴ መሆኑን አጋጣሚው ግልፅ አድርጓል! እዉነትና ንጋት እያደር ይጠራል!” ሲሉ ህወሃት የመከላከያ ሰራዊት መለያ በመልበስ ሲፈጽማቸው ለነበሩ ሃጢአቶች ማጋለጫ ታላቅ ግብዓት መሆኑንን አመልተዋል።

በቅርቡ የትግራይ ቲሌቪዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆኖ የተሾመው ጋዜጠኛ አርአያ በፊስ ቡክ ገጹ እንዳለው ደግሞ በሁመራ በኩል ለማምለጥ ሲገሰግስ የነበረ የትህንግ ሃይል መደምሰሱንና አንገታቸው ተቆርጦ የተገኙ መኖራቸውን አስታውቋል። አያይዞም እርምጃ የተወሰደባቸው ማንነታቸው እንዳይታወቅ አንገታቸውን የሚቀሉትን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ ቀረጻ እንዲካሄድ መደረጉን ተናግሯል።


Leave a Reply