የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አቶ ሬድዋን ሁሴን ስምምነቱን ተከትሎ የተሰሙትን “መግለጫዎች የጠበቅናቸው ናቸው” ሲሉ ከብሔራዊው ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ “ተናግረዋል”ተሻለ ጥቅምና ኢንቨስትመን ለሚያቀርብ ድርድሩ ከፍት ነው” ሲሉ የኢትዮጵያን የመደራደሪያ አቅም ማደግ አመላከቱ። ስም ሳይጠቅሱ “መግለጫ ካወጡት መካከል የራሳችን የምንላቸው ሰዎች ከሌላው በለላይ ሲወራጩ ሲታይ ያስቆጫል፤ ያሳዝናልም ” በማለት ተናግረዋል። የሶማሌ መሪ አዲስ ህግ መፈረማቸውን አስታወቁ።
አማካሪው ይፋ አያድርጉት እንጂ ወቀሳቸው ማን ላይ እንደሆነ ሊሸሸግ የሚችል አይደለም። ቀደም ሲል ኢህአዴግ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አልሸባብን በውክልና እያሰለጠኑና እያስታጠቁ እንደነበር ጠቅሶ በተደጋጋሚ ሲውነጅልና ማዕቀብ ሲያስጥል መቆየቱ አይዘነጋም።
ከለውጡ በሁዋላ ከኢትዮጵያ ጋር የነበረውን የጸብ ግድግዳ በማፍረስ ተጀመሮ የነበረው ግንኙነት ግልጽ ባይነገርም እየተበላሸ እንደሆነ ማስረጃዎች ከበቂ በላይ ናቸው። ኢሳያስ አፉወርቂ በተደጋጋሚ ወደ ሶማሊያ ጦር እያስለጠኑ መላካቸው ብቻ ሳይሆን፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቅ እየገቡ እንደሆነ በመረጃ ተረጋግጧል።
ጉዳዩ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዳያበላሽ በሚል ካልሆነ በስተቀር ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከኢትዮጵያ ቀውስ ጀርባ እንዳሉበት፣ በስልጠናና በሎጂስቲክ በኩልም በውክልና እንደሚሰሩ ለደህነት ቅርብ የሆኑ እየተናገሩ ነው። አንዳንዶች ከኢሳያስ እንቅስቃሴ አንሳር የመንግስት ትህትና እንደሚያስገርማቸው ይናገራሉ።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አቶ ሬድዋን ሁሴን፣ “የራሳችን የምንላቸው ሰዎች ከሌላው በለላይ ሲወራጩ ሲታይ ያስቆጫል፤ ያሳዝናልም” ሲሉ ጉዳዩን በገሃድ በሚመስል ደረጃ መቃወማቸው ከዚሁ ከላይ ከተነሳው ጉዳይ ጋር በተያያዘ ይመስላል።
ኢትዮጵያ አውሮፓን ካስለቸውና ካስጨነቀው የስደተኞች ፍልሰት አኳያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ስምምነት ማሰሯን የሚያስታውሱ የሶማሊላንድንና የኢትዮጵያን ስምምነት ሙሉ በሙሉ አይጋፉም። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳለው የእንግሊዝና የፈረንሳይ እንዲሁም የሩሲያን ጨምሮ ከበርካታ አምባሳደሮች ጋር በጉዳይ መክሮ መልካም የሚባል መረዳዳት ላይ መድረሳቸውን አስታውቋል።
የትዮጵያን አንድነትና ጥንካሬ እንደሚፈልጉ በተደጋጋሚ በሚቀርቧቸው ሚዲያዎች የሚያስነግሩት ኢሳያስ አፉወርቂ ያሉበት የአረብ ሊግን ጨምሮ ከካይሮ ተቃውሞ ማሰማታቸው “ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ መድረክ ጋር የሚያገናኛትን የባሕር በር ካገኘች በሁለት እግሯ ልትቆም ትችላለች የሚል ሥጋት ስላላቸው ነው” ሲሉ ሬድዋን ተናግረዋል። ከዚሁ ስጋታቸው አንጻር እነዚሁ አካላትን “እሳትና ነዳጅ ሲያቀብሉ አይተናል” ሲሉ በግርድፉ ተግባራቸውን አሳይተዋል።
ኢትዮጵያ ራሷ የምትቆጣጠረውና የምታለማው የባሕር በር መኖሩ ለሀገሪቱ ደኅንነትና የንግድ እንቅስቃሰሴ ትልቅ ሚና እንደሚኖረውም ሳይታለም የተፈታ ሃቅ መሆኑንን ያወጉት አቶ ሬድዋን ለሶማሊላንድ ዕውቅና የመስጠቱን ጉዳይም በጥቅሉ አስረድተዋል።
የመግባቢያ ሰነዱ ጉዳይ ወደ ተሟላ ስምምነት ደርሶ መሬቱን ስንረከብና ሂደቱ ሲቋጭ እነሱ እውቅና ለማግኘት የሚያደርጉትን ጥረት በተመለከተ ኢትዮጵያ አቋም የምትወስድበ ደረጃ ላይ እንደሚደረስ ነው አቶ ሬድዋን በፖለቲካ ቋንቋ ያወሩት። በዚሁ መነሻ ስምምነቱ ወደ ተግባር ሲፈጸምና ርክክቡ ሲከናወን ኢትዮጵያም አቋሟን ይፋ ታደርጋለች።
አቶ ሬድዋን ሌላም ተመሳሳይ ንግግር ከሌሎች አገራት ጋርም እየተደረገ መሆኑንን ገልጸዋል። “የተሻለ ኦፈር፣ ድርድር፣ ኢንቨስትመንት እና ዘላቂነት ካለ አሁንም ንግግሩ ይቀጥላል” ንግግሩ ይቀጥላል ብለዋል።
ኤርትራ ኢትዮጵያ በርበራ ወደብ ላይ ከሰፈረች አሰብ ላይ የምትጠየው የገበያ ዋጋና ጥቅማ ጥቅሞች እስከ ሃምሳ በመቶ እንደሚወርድ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው። ኢትዮጵያ የሃምሳ ዓመት ውል ካሰረች ኤርትራ ለምታቀርበው የባህር በር ስምምነት እንደቀድሞ ሰፍ ብላ አትገባበትም። በዚህ መነሻ አዲሱ ስምምነት የኢትዮጵያን የመደራደሪያ አቅም ያሳድጋል። ኢሳያስ አፉወርቂንም ያስቆጣው በርካታ ጥቅሞችን ለኤርትራ የሚሰጠው የስምምነት ውል ጠረጴዛቸው ላይ ተቀምጦ ሳይፈርሙ ጊዜ ሲገድሉ ኢትዮጵያ ሌላ አማራጭ ማግኘቷ ነው። ይህን የሚያጠናክሩት አቶ ሬድዋን “የተሻለ ኦፈር ከቀረበ ድርድሩ ይቀጥላል” ያሉት በዚሁ መነሻ ስለመሆኑ አይጠራጥርም። ዘጠና ሰባት ከመቶ ከመቶ የደረሰው የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የፖለቲካ አቅም እንደፈጠረላት ያስታወሱ፣ የባህር በር ባለቤት በመሆን የባብ ኢልማንደብ ሰርጥ ላይ መካተቷ ተቀባይነቷንና የፖለቲካ ተጽዕኖ ፈጣሪነቷን እንደሚያገዝፈው የዘርፉ ባለሙያዎች በተደጋጋሚ ምክንያት እየዘረዘሩ አያቀረቡ ነው።
ሶማሊላንድ የምትሰጠው የባህር በር የሚገኘው በበርበራ እና ዘይላ መካከል የሚገኝ ሎግሃያ የሚባል አካባቢ መሆኑንን እንደሆነ የደህንነት አማካሪው ገልጸዋል። ቦታው የቀይ ባህርና የሲውዝ ካናል መግቢያ ላይ መሆኑን ጠቅሰው እጅግ ስትራቴጂክ እንደሆነ ባለሙያዎች ሰፊ ትንታኔ እየሰጡ ነው። “ደም እንደጎርፍ ይወርዳል” ሲል ያስጠነቀቀው አልሸባብ ምን አልባትም የሎጂስቲክ ድጋፉ ሊመናመን እንደሚችል ስለአካባቢው ያጠኑ እየተናገሩ ነው። እናም ጩኸቱ በደም እያጠባት ላለችው የሞቃዲሾዋ ሶማሊያ ጭንቀት ሳይሆን ህልውናው ነው።
የአሜሪካ ልዩ መልክተኛና የአትላንቲክ ካውንስል የፖለቲካ ጉዳዮች ተመራማሪ አምባሳደር ጄ ፒተር ፋም ስምምነቱን “የሚደነቅ” ሲሉ ለቢቢሲ መናገራቸው ምን አልባትም የአሜሪካ አቋም ማመላከቻ ፍንጭ እንደሆነ ተገምቷል። የአትላንቲክ ካውንስል የአሜሪካ ፖሊሲ ማወለጃ ተቋም እንደሆነ የሚያውቁና በቅርብ ከአጥኚዎቹ ጋር የሚገናኙ እንደሚሉት ከአትላንቲክ ካውንስል ሰዎች አንድ ጉዳይ ዝም ተብሎ አይወራም።
ኢጋድና የአፍሪካ ኅብረት የሞቃዲሺዋ ሶማሌ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ያሰማቸውን ቅሬታ ተከትሎ “ውጥረት እንዲረግብ” ጥሪ አቅርበዋል። አሜሪካና እንግሊዝ፣ አረብ ሊግና ግብጽ በገሃድ ” ኢትዮጵያን ወዮልሽ” ሲሉ በኢትዮጵያዊነት ስም ራሳቸውን የሚጠሩ “ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት የለባትም” በሚል ሂሳብ ከሌላ ጎን ሆነው ቅስቀሳ ተያይዘዋል።
ይህ በንዲህ እንዳለ የሞቃዲሾ መንግስት ፕሪዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የፈጸመችውን ስምምነት “ውድቅ የሚያደርግ” ህግ መፈረማቸውን በአኤክስ ገጻቸው አስታውቀዋል። ህጉ ስምምነቱን ዋጋ እንዳይኖረው የሚያደርግ እንደሆነ ጠቁመዋል። አስፈላጊ መሆኑንንም አመልክተዋል።
ሶማሊላንድ በበኩሏ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ መሐመድን አስጠንቅቃለች። ከአዲስ አበባ መልስ ሃርጌሳ ሲገቡ እጅግ ከፍተኛ የተባለ አቀባበል የተደረገላቸው የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ” አገራችንን አልሸጥንም። ከኢትዮጵያ ብዙ እንጠቀማለን። ለሃምሳ ዓመት በሊዝ ነው ያከራየነው።” ሲሉ ተናግረዋል። አያይዘውም እየታመሰች ያለች አገር የሚመሩትን የኦማሌ ፕሬዚዳንት አስጠንቀቃዋል። ስምምነቱን የሚያስቆም አንዳች ሃይል እነደሌለም አመልክተዋል።