መደበኛ የክስ ሂደታቸውን እየተመለከተ ያለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የጸረ-ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 18 በእነ ጁሃር መሃመድ ከተከሰሱ 24 ተከሳሾች በጽሁፍና በቃል ለቀረበለት አቤቱታ ” የእኛ እምነት ነጻ ከሆናችሁ እናንተን ነጻ ማውጣት ነው” ሲሉ የችሎቱ ዳኛ መናገራቸው ተሰማ።

ዳኛው ይህን ያሉት በነ ጃዋር መዝገብ 24 ተከሳሾች ከዛሬ ጀምሮ ጉዳያቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት እንደማይቀርቡ ማስታወቃቸውን ተከትሎ ነው። ተከሳሾቹ በትግራይ ይፈጸማል ያሉትን ለመቃወም በሚል ለሁለት ቀናት የረሃብ አድማ እንደማዲያደርጉም ገልጸዋል።  

ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ያለመቅረብ ውሳኔያቸውን ያስታወቁት፤ መደበኛ የክስ ሂደታቸውን እየተመለከተ ላለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የጸረ-ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 18 በጽሁፍ ባቀረቡት አቤቱታ ነው። በችሎቱ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ጃዋር መሐመድ፤ የኮሎኔል ገመቹ አያና እና የሌሎች ተከሳሶችን ጉዳይ በመጥቀስ የፍርድ ቤት ውሳኔ በተገቢው መንገድ ተፈጻሚ እየሆነ አይደለም ብለዋል። 

“እኛ እዚህ የመጣነው ከተፈረደብን ለመቀጣት፤ ነጻ ከተባልን ለመውጣት ነው” ያሉት አቶ ጃዋር፤ “ከዛሬ ጀምሮ በገዛ ፍቃዳችን ፍርድ ቤት አንቀርብም” ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አስታውቀዋል። ዜናውን የዘገበው ኢትዮ ኢንሳይደር እነ ጃዋር ፍርድ ቤት መቅረብ እንደማይፈልጉ ያስታወቁበትን ምክንያት ዝርዝር አላቀረበም። አቶ በቀለ ገርባ በበኩላቸው “በግድ ተጎትተን እና ተደብድበን ካልሆነ በቀር ወደዚህ ፍርድ ቤት አንመጣም”ማለታቸው ተዘግቧል።

የፖለቲካ ሃሳብ ማስተላለፊያ የሆነው የችሎት መድረክ ሙሉ ስዕል የሌለው ዜና እንዳልመለከተው እነጃዋር በትግራይ የጅምላ ጭፍጨፋ መኖሩን ጠቅሰው መንግስትን አውግዘዋል። ይህን ሲሉ ችሎቱ ምን ምላሽ እንደሰጠ አልተገለጸም። እነ ጃዋር የችሎት ሂደቱን በማደናቀፍና የፍርድ ሂደቱ በቶሎ እንዳይጠናቀቀ እንቅፋት እየሆኑ መሆኑንን አቃቤ ህግ በተደጋጋሚ መናገሩ አይዘነጋም።

ባለፈው ሳምንት ” መንግስት ሲረጋጋ ከሁለት ዓመት በሁዋላ ጉዳያችን ያታይ” ሲሉ የተሰሙት እነጃዋር ዛሬ ጭራሹኑ ወደ ችሎት እንደማይመጡ አቋም መያዛቸውን ሲያስታውቁ ” የኦሮሞ ሕዝብ አንድ ሆኖ ይህን መንግስት ይታገል” የሚል ጥሪ ከተከሳሾቹ አንዱ መናገራቸው በዜናው ተካቷል። ከፍርድ ቤት ፍቃድ ውጪ የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ተብሎ ከዚያ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቋል። 

ፍርድ ቤቱም በበኩሉ ተከሳሾቹ ያነሱት ሀሳብ ላይ ምክር ሰጥቷል። “የእኛ እምነት ነጻ ከሆናችሁ እናንተን ነጻ ማውጣት ነው” ያለው ፍርድ ቤቱ፤ ይሄንንም በሂደት ለተከሳሾቹ እንደሚያረጋግጥላቸው ቃል ገብቷል። ፍርድ ቤቱ የዛሬውን ችሎት ከማጠናቀቁ በፊት ለመደበኛ የክስ ሂደቱ ሁለት ቀጠሮዎችን ሰጥቷል። 

የመጀመሪያው ቀጠሮ ዐቃቤ ህግ በእነ ጃዋር መሐመድ ላይ የቆጠራቸው ምስክሮች ላይ አሉ የሚላቸውን የደህንነት ስጋቶች ዘርዝሮ በግንቦት 30፤ 2013 በፍርድ ቤቱ ሬጅስትራር በኩል እንዲያስገባ የሚያዝ ነው። የተከሳሽ ጠበቆች፤ ዐቃቤ ህግ የሚያቀርባቸው የደህንነት ስጋቶችን በተመለከተ መልሳቸውን ሰኔ 10፤ 2013 በችሎት በኩል እንዲያቀርቡም ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ከኢትዮ ስታንዳርድ ዘገባ ለመረዳት ተችሏል። 

እነ ጃዋርና አቶ በቀለ ገርባ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ትህነግ ሊረሳ የማይችል ወንጀል ከፈጸመው ትህነግ ጋር ማበራቸው በፖለቲካ ራሳቸውን በራሳቸው እንዳጠፉ እንደሚቆጠርና፣ በርካታ ደጋፊዎችቸውን እንዲያጡ እንዳደረጋቸው በርካታ አስተያየት ሰጪዎች የሚናገሩት ጉዳይ ነው። ለትግራይ ህዝብ ድጋፍ ማስጠት አግባብ አግባብ ቢሆንም ቀደም ሲል እነ ጃዋር ከትህነግ ጋር የተናበበና አብረው እቅድ ነድፈው መንቀሳቀሳቸው በበርካታ የክልሉ ተወላጅና ኢትዮጵያዊያን ዘንድውግዘት እንዳስነሳባቸው ይታወሳል። እነ ጃዋር መከላከያ ሰራዊት ሲመታና ሲታረድ ድምጻቸውን በተመሳሳይ ደረጃ አላሰሙም።


Leave a Reply