ከአምስት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ከፊል ስፍራ ተቆርሶ ለግብርና ኢንቨስተሮች መሰጠቱ ያስቆጣቸው ሦስት ምሁራን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ደብዳቤ ጻፉ።
የባቢሌ ፓርክ ደን ተመንጥሮ ለኢንቨስተሮች መሰጠቱ ከፍተኛ የድርቅ አደጋ እንደሚጋርጥ በመግለጽም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጣልቃ እንዲገቡ ምሁራኑ በደብዳቤያቸው ጠይቀዋል።
በኢትዮጵያ ትልቁ የዝሆኖች መጠለያ የሆነው እና በምሥራቅ ሐረርጌ የሚገኘው የባቢሌ ፓርክ ለኢንቨስተሮቹ መሰጠቱ ለዝሆኖቹ ብቻ ሳይሆን ለሕዝቡም አደጋ መሆኑን ምሁራኑ ይናገራሉ።
ደብዳቤውን የጻፉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የብዝኃ ሕይወት ተመራማሪ ዶክተር ሃብቴ ጀቤሳ፣ የአካባቢ ጥበቃ ከፍተኛ ባለሙያ ዶክተር አዳነ ፀጋዬ እና ዶክተር አዲሱ አሰፋ ናቸው።
ፓርኩ የደን ምንጠራ ማካሄድ ከፍተኛ የድርቅ አደጋ ሊያስከስት እንደሚችልም ዶክተር ሃብቴ ያስረዳሉ።
“በፓርኩ ውስጥ ያለው ስፍራ ተጋላጭ አካባቢ ነው። ደን ምንጠራ ማካሄዱ በቅርብ ጊዜ ማገገም አይቻልም። ለበረሃነት፣ ለድርቅ የተጋለጠ ነው። ለዝሆኖቹ ብቻ ሳይሆን ሕዝቡን እጅግ አደገኛ የድርቅ ስጋት ውስጥ ይጥለዋል”ብለዋል።
እየተመነጠረ ያለው ደን በመቶ ዓመታት ውስጥ እንኳን ማገገም እንደማይችል እና የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማም እንዳልተደረገበትም ነው ምሁሩ የገለጹት።
በተለይም ኢትዮጵያ ከተጋረጠባት የድርቅ አደጋ ጋር ተያይዞም ችግሩን የበለጠ ያከፋዋል ይላሉ።
በሐረርጌ አካባቢ በድርቅ ምክንያት 80 ሺህ ሕዝብ መፈናቀሉንም ጠቅሰው “በዚህ አካባቢ እንዴት ነው ደን የሚመነጠረው? እጅግ የሚያሳዝን ነው” በማለት በድርጊቱ የተሰማቸውን ሐዘን ለቢቢሲ ገልጸዋል።
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዋነኝነት ደብዳቤ ለመጻፍ ያነሳሳቸው አንደኛው ጉዳይ የአረንጓዴ አሻራ በሚል ከሚያደርጓቸው የአካባቢ ጥበቃ ጋር በተያያዘ እንደሆነም ይናገራሉ።
በፓርኩ እየተከናወነ ያለውም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የደን ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ተግባር ጋር “የሚጋጭ ነው” ሲሉም ዶክተር ሃብቴ ያስረዳሉ።
“እሳቸው ይሄንን ነገር ሰምተውታል ብዬ አላስብም። ከሰሙ እንደሚያስቆሙት እርግጠኛ ነኝ” ብለዋል።
- በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ መሬት ለኢንቨስተሮች መሰጠቱ በዝሆኖች ደኅንነት ላይ ስጋት ፈጠረ30 ነሐሴ 2023
- የባቢሌ ዝሆኖች ህልውና አደጋ ላይ ነው14 ነሐሴ 2019
- ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ዝሆኖች በታጣቂዎች ተገደሉ1 ሰኔ 2020
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የባቢሌ ፓርክ የደን ምንጠራ ጉዳይ ከሰሙ አቅጣጫ ሰጥተው ያስቆሙታል “በሚል ትልቅ ዕምነት” ደብዳቤ መጻፋቸውንም አስረድተዋል።
በፓርኩ ውስጥ በአሁኑ ወቅት የደን ምንጠራ እየተካሄደ እንደሆነ እና የዱር እንስሳት ጥበቃ ልማት ሠራተኞች (ሬንጀሮች) እንደተባረሩ እንዲሁም መደብደባቸውንም እንደሰሙ ዶክተር ሃብቴ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
“እንደሰማነው መከላከያ ነን በሚሉ የመከላከያ መለዮ በለበሱ እና ማንነታቸው በማይታወቁ ሰዎች ተወስደው ተገርፈዋል። ከፓርኩም ተባርረዋል” ብለዋል ዶክተር ሃብቴ ።
ቢቢሲ ከጥቂት ሳምንታት በሰራው ዘገባ ለልማት ተፈቅዶልናል ያሉ ባለሃብቶች ዶዘር አስከትለው በመሄድ ወደ ፓርኩ ለመግባት ሲሞክሩ በዝሆኖቹ መጠለያ ጠባቂዎች በመከልከላቸው ግጭት መፈጠሩን አመልክቶ ነበር።
በዚህም ሳቢያ በተወሰኑ መንግሥት የመደባቸው እና ሕጋዊ የደንብ ልብስ በለበሱ የዱር እንሰሳት ጥበቃ ልማት ሬንጀሮች ላይ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ዱር እንሰሳት ጥበቃ ባለሥልጣንም ድርጊቱ ዝሆኖችን ለአደጋ የሚያጋልጥ እና አኗኗራቸውን የሚያናጋ በመሆኑ ከኦሮሚያ ክልል ጋር በመሆን የፓርኩ ደኅንነት ለማስከበር እየሠራ መሆኑን ገልጿል።
ስፋቱ 6980 ካሬ ኪሎ ሜትር የሆነው የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ውስጥ ለእርሻ ልማት በሚል በባለሃብቶች እየታረሰ ነው የተባለው ቦታ በፓርኩ ሰሜናዊ ክፍል ኤረር ሸለቆ በሚባለው ስፍራ ያለ ነው።
ባለሃብቶች በተለይ ለእርሻ፣ ለከብት ማደለቢያ እና ለንብ እርባታ አካባቢውን ይፈልጉታል። በዋናነትም ስፍራው ከ50 ዓመታት በላይ በመንግሥት እጅ ስለቆየ ጥብቅ እና ለም መሬት ስለሆነ እንዲሁም ወንዝ ዳር በመሆኑ ውሃ በቀላሉ ማግኘት ስለሚችሉ ባለሃብቶች ዐይናቸውን እንደጣሉበት ባለሙያዎች ይናገራሉ።
ቢቢሲ አማርኛ
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank MembershipThe Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to become member of BRICS’ New Development Bank. In a media briefing… Read more: Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከሃምሳ… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙንna ለዚህም ተግባራዊነት ከሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊየን በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን ተገለጸ። 1… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ በህብረቱ ስም የወጣው ዜና ሃሰት፣ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን መንግስት አስታወቀ። መረጃው ቀድሞውንም… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን ምኑ ነው አፍሪካ ህብረትን… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች