የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢዎች አዲስ አበባ ገቡ፤ ቅድመ ምርጫው ላይ ግምገማው ይህ ነው የሚባል እንከን አልተገኘበትም

No photo description available.

\ስድስተኛውን አጠቃላይ አገራዊ ምርጫ የሚታዘቡ የአፍሪካ ሕብረት የረጅም ጊዜ የምርጫ ታዛቢዎች አዲስ አበባ መግባታቸው ተገለጸ። የሕብረቱ የአጭር ጊዜ ታዛቢዎች ከምርጫው አንድ ሳምንት በፊት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡም ተገልጿል። በቅድመ ምርጫ ግምገማ የተሰማሩ ጉዟቸውን አጠናቀው ከምርጫ ቦርድ ጋር የመጨረሻ ውይይት ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበውን ግብዣ ተከትሎ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት ምርጫውን የሚታዘቡ የአፍሪካ ሕብረት የአጭርና የረጅም ጊዜ ታዛቢዎችን ስምሪት ማድነቃቸው ይታወሳል።

ሕብረቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ ከሕብረቱ አባል አገራት የተውጣጡ ስምንት አባላት ያሉት የረጅም ጊዜ የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን ግንቦት 25 እና 26 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ መግባቱን ገልጿል።

ታዛቢዎቹ በአጠቃላይ ምርጫ ሂደቱ ያለው የፖለቲካ ከባቢ አየር፣ የምርጫው ሕጋዊ ማዕቀፎች፣ የምርጫ ዝግጅትና አስተዳደር ግልጽነትና ውጤታማነት፣ የምርጫ ቅስቅሳ ሁኔታ የመታዘብ ስራ እንደሚያከናውኑም ተጠቅሷል።

ይህ በንዲህ እንዳለ ለቅድመ ምርጫ ግምገማ ወደ ኢትዮጵያ ያቀኑት ተቋማት ቅድመ ምልከታቸውን አጠናቀው ሪፖርታቸውን ለማቅረብ ዛሬ ከምርጫ ቦርድ ጋር የሪፖርት ማሟያ ውይይት እንደሚያደርጉ ተሰምቷል። የኢትይ 12 የአዲስ አበባ ተባባሪ እንዳለው በቅድም ግምገማው ይህ ነው የሚባል የነቀፌታ ችግር እንዳልተገኘ ስራውን እየሰሩ ካሉ ሰምቷል።

አብዛኛው ሕዝብ ምርጫው ተደርጎ መገላገል እንደሚፈልግ፣ ከምርቻው በሁዋላ ሰፊ ተስፋ እንዳላቸውና የምርጫው መጠናቀቅ በጉልህ እንደሚያጠባበቁ የተሰበሰቡ አስተያየቶች እንደሚጠቁሙ የወሬው ምንጮች ገልጸዋል። በአንዳንድ ቦታዎች ረብሻ ይነሳል የሚል ስጋት ያላቸው ቢኖሩም ማን? ለምን? እንዴትና? የት ረብሻ እንደሚያደርግ አያውቁም። በወሬ ደረጃ ግን ሰዎችን የሚያስጨንቁ አሉ።

በብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ዘንድ ስጋት እንደማይታይ ታዛቢዎቹ ተረድተዋል። አብዛኞቹ በተዘዋወሩባቸው ስፍራዎች ህዝብ የኮሮና ስጋት እንደሌለበት፤ ለስጋት የሚዳርግ ምንም ጉዳይ አለመኖሩን አይተዋል። ምርጫ ቦርድ ስጋት አለባቸውን ያላቸውን ስፍራዎች በአማራ ክልልና በኦሮሚያ ምርጫ እንዳይካሄድባቸው መወሰኑ ይታወሳል።Leave a Reply

%d bloggers like this: