ማንኛውም የተቀመጠውን መመሪያ የሚጥስ የአውሮፕላን አብራሪም ሆነ ኦፕሬተር ለሚደርሰው አደጋ ሃላፊነት እንደሚወስድ የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስጠንቅቋል፡፡
Ethiopia Current Issues Fact Check የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ በማህበራዊ ትስስስ ገጹ ላይ ባሰፈረው ጽሁፍ፣ ቀደም ሲል ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም የአየር በረራ መረጃ ማሳወቂያ (NOTAM& AIP SUP) ቁጥር A0166/21 እና AIP SUP A04 ,2021) መተላለፉን አስታውሷል፡፡
በተላለፈው መመሪያ መሠረትም ማንኛውም የአውሮፕላን አብራሪም ሆነ ኦፕሬተር የተቀመጠውን መመሪያ ከጣሰ ለሚደርሰው አደጋ ሃላፊነቱ የራሱ የጣሰው አካል መሆኑንን መግለጫው አስታውቋል።በስምምነቱና ማስታወቂያው መስረት በኮድና በቁጥር ተሰፍሮ በቀረበው ማሳወቂያ፣ መንግስት ይህን በማያከብሩ ላይ ለሚወሰደው እርምጃ ሃላፊነት እንደማይወስድ ለምን እንዳስታወቀ ምክንያቱን አላብራራም።
በማስታወሻው በይፋ ባይገለጽም በርዳታ ስም በቀጥታ ወደ ትግራይ በረራ እንዲደረግ ተደጋጋሚ ጥያቄ መቅረቡ ይታወሳል። መንግስት ጥያቄውን ተቀብሎ፣ ትብብር እንደሚያድርግ አስታውቆ እንዳለው ” ማንኛውም በረራ አዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሶ ፍተሻ እንዲደረገበት በተደረሰው ስምምነት መሰረት የሚከናወን ነው። በዚሁ መግባቢያ መሰረት የዓለሙ የምግብ ድርጅት አውሮፕላን ከአንዴም ሁለቴ አስፈላጊው ፍተሻ ተደርጎበት መቀለ ደርሶ መመለሱ መዘገቡ ይታወሳል።
ስምምነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ለምን መንግስት ይህን መግለጫ ለማውጣት እንደፈለገ ግልጽ ባያድረግም ስምምነቱን የመጣስ ሙከራ ስለመኖሩ አመልካች እንደሆነ ከግምት በላይ አስተያየት እየተሰጠ ነው። መንግስት መመሪያውን በጣሱ አካላት ላይ እርምጃ ከውሰደ ለጣልቃ ገብነት መነሻ ምክንያት ለማድረግ ታስቦ እንደሆንም ተመልክቷል።
It is to be recalled that as of June 30th 2021, a NOTAM& AIP SUP has been issued with reference number (A0166/21 and AIP SUP A 04 2021) by the Ethiopian Civil Aviation Authority. Therefore, violations against the above NOTAM will result in high risk to any operators and/or pilots. Entities violating the issued NOTAM therefore assumes full responsibility for any related actions.
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ። ለውጭ አገር ሚዲያዎች ዜና የሚያቀብሉና እነሱኑ የሚከተሉ ስምምነቱ መክሸፉንና መንግስት… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት
- የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡምየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራንስፖርት ስምሪትና የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር ሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ 11 ግለሰቦች በስር ፍ/ቤት የተሰጠውን ዋስትና አፀና። ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ ከሀገር እንዳይወጡ እግድ እንዲጣል… Read more: የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡም
- መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለየአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ ምክንያቱም “የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ የአውሮፓ ኅብረት አገራት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቹን መልሶ ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ መሆኑን… Read more: መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ
- “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረውየሚነሳው ጉዳዩ ልብ ሰባሪ ነው፣ ያስቃል፣ ያዝናናል፣ ያስገርማል፣ ያሳዝናል፣ ይቀፋል፣ ያሳፍራል፣ ለማመን ያስቸግራል … አንባቢ ስም ይስጠው። እኔ ስጽፈው ግን በሃፍረት ስሜት ነው። ያፈርኩት ደግሞ በደርስንበት… Read more: “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረው
- ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!በፖለቲካም ሆነ በአካባቢያዊ አጀንዳ ነፍጥ ያነገቡ እና ጦርነትን አማራጭ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ኢ -መደበኛ አደረጃጀቶች ሁሉ የጦር መሳሪያ ፍላጎት ይኖራቸዋል፡፡ የጦር መሳሪያ ፍላጎት ሲኖር መሳሪያ ሸጦ ትርፍ… Read more: ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!