«ደሴን ለመውረር አሰፍስፎ የነበረ አሸባሪው እስከወዲያኛው ተሸኝቷል»

– ደሴን ለመውረር አሰፍስፎ የነበረ አሸባሪው የህወሃት ወራሪ ኃይል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል

– በወሎ ዩኒቨርሲቲ ፎቶ ለመነሳት ገብቶ የነበረ የጥፋት ቡድኑ ፎቶ ናፋቂም ባለበት አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ እስከወዲያኛው ተሸኝቷል

– የደሴ ከተማና አካባቢዋን ተቆጣጥረናል በማለት ጮኸው የሚያስጮሁ የወራሪው ወሬ አራጋቢዎችም በስፍራው እየተፋለሙ የሚገኙትን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ወኔና ጀግንነት አልተረዱም

በጢጣ በኩል ሰብሮ በመግባት የደሴ ከተማን ለመቆጣጠር የሞከረው አሸባሪው የህወሃት ወራሪ ኃይል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል።

የመጣውን ኃይልም ደሴ ከተማ ከመግባቱ በፊት ሙሉ በሙሉ ባለበት ማስቀረት መቻሉን በወሎ ግንባር ወራሪውን ኃይል እያጸዱ የሚገኙ የመከላከያና ደህንነት ምንጮች ለኢዜአ ጠቁመዋል።

የደሴ ከተማና አካባቢዋን ተቆጣጥረናል በማለት ጮኸው የሚያስጮሁ የወራሪው ወሬ አራጋቢዎችም በስፍራው እየተፋለመ የሚገኙትን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ወኔና ጀግንነት ካለመረዳት የመነጨ እንደሆነ አስታውቀዋል።

በግንባሩ የተሰለፉ የሰራዊት አመራርና አባላትም ወራሪውን ኃይል ለአንዴና መጨረሻ ለማጥፋት አኩሪ ተጋድሎ እየፈጸሙ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

በኩታበር በኩል አሰፍስፎ ደሴን ለመውረር የመጣው ወራሪ ኃይልም ምንም ማድረግ እንዳይችል ተደርጎ መደቆሱን ገልጸዋል።

በወሎ ዩኒቨርሲቲ ፎቶ ለመነሳት ገብተው የነበሩ የጥፋት ቡድኑ ፎቶ ናፋቂዎችም ባሉበት አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ እስከወዲያኛው መሸኘታቸውን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።

ደሴና አካባቢዋን ለመውረር ከየአቅጣጫው ተሰባስቦ አሰፍስፎ የነበረውን ኃይልም አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የደሴን ከተማ በወገን እጅ እንዳለች ማስቀጠል መቻሉን ገልጸዋል።

የደሴ ከተማ እና አካባቢው የሽብር ቡድኑን የአፈሳ ወሬ ባለመስማት አካባቢውን ጸንቶ እንዲጠብቅና ለግንባሩ ሰራዊት ሲያደርጉት የነበረውን ደጀንነት እንዲያስቀጥሉ ጠይቀዋል።

በግንባሩ ያሉ የሰራዊት አባላት የጥፋት ቡድኑን ማጽዳት ይቀጥላሉ ያሉት ምንጮቻችን በቅርብ ጊዜም ይህኑ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነ ወራሪ ኃይልም እስከወዲያኛው የሚሸኙበት ቀን ሩቅ እንዳልሆነ አረጋግጠዋል።

ENA

See also  ሩሲያና ኢትዮጵያ በመረጃና ደህንነት ጉዳዮች የሚያደርጉትን ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጸ

Leave a Reply