4 ተቋማት በእነእሌኒ ገብረመድኅን ላይ ምርመራ እንዲጀመር ለኤፍ ቢ አይ እና ኒውዮርክ አቃቤ ሕግ ቢሮ ጥያቄ አቀረቡ

4 ተቋማት በእነእሌኒ ገብረመድኅን ላይ ምርመራ እንዲጀመር ለኤፍ ቢ አይ እና ኒውዮርክ አቃቤ ሕግ ቢሮ ጥያቄ አቀረቡ

ኅዳር 23/2014 (ዋልታ) በአሜሪካ የሚገኙ አራት የሲቪል ተቋማት በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠን የኢትዮጵያ መንግሥት በኃይል ለመቀየር ያሴሩ ግለሰቦች በሕግ እንዲጠየቁ ለኤፍ ቢ አይ እና ኒውዮርክ አቃቤ ሕግ ቢሮ አመለከቱ፡፡

ይህ የግለሰቦቹ አካሄድ ከ118 ዓመት በላይ የዘለቀውን የኢትዮጵያ እና አሜሪካ ወዳጅነት በእጅጉ የሚጎዳ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

በአገሪቱ ሕገመንግሥት መሰረት ማንኛውም አሜሪካዊ በሌሎች አገራት ጉዳይ ጣልቃ መግባትን የሚከለክል ከመሆኑም በላይ ይህን ተላልፎ የተገኘ አካል ቅጣት እንደሚጣልበትም ይደነግጋል፡፡

ከሳምንት በፊት የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጨምሮ የአውሮፓና አሜሪካ ዲፕሎማቶች በድብቅ ያደረጉት የሽግግር መንግሥት የመመስረት የበይነ መረብ ውይይት ከላይ የተጠቀሰውን የአገሪቱን ሕግ የሚጥስ በመሆኑ የአሜሪካ የፌደራል ምርምራ ቢሮ (FBI) እና የኒውዮርክ አቃቤ ሕግ ቢሮ በእነዚህ ግለሰቦች ላይ ምርመራ እንዲያካሂዱ ነው ተቋማት የጠየቁት፡፡

በበይነ መረብ ውይይቱ ላይ ከተሳተፉት መካከል የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጀው ሕወሓት አመራሩ ብርሃነ ገብረክርስቶስ፣ ኤፍሬም ይስሃቅ እና እሌኒ ገብረመድህን ይገኙባቸዋል፡፡

ጥያቄውን ያቀረቡ ተቋማት ግሎባል ኢትዮጵያን አድቮኬሲ ኔክሰስ፣ ወርልድ ዋይድ ኢትዮጵያን አክሺን ፈንድ፣ ዩኒቲ ፎር ሂውማን ራይት ኤንድ ዴሞክራሲ እና ኢትዮ-አሜሪካን ዴቨሎፕመንት ካውንስል መሆናቸውን ዋልታ ከተቋማቱ የጋራ ደብዳቤ ላይ ተመልክቷል፡፡

Walta

2 thoughts on “4 ተቋማት በእነእሌኒ ገብረመድኅን ላይ ምርመራ እንዲጀመር ለኤፍ ቢ አይ እና ኒውዮርክ አቃቤ ሕግ ቢሮ ጥያቄ አቀረቡ

  1. እሌኒ ብቻ ነች አሜሪካዊ ተሰብሳቢ ፈረንጆቹስ ..? ፕሮፌሰር ኤፍሬምስ..? የኦሆዴድ ኣባላት ናቸው ?

    1. እሷ አክቲቭ ስለሆነችና ከመንግስት ጋር እየሰራች ስለሆነ የከረረባት ይመስለኛል። ሌሎቹን ግን እኮ አሉበት

Leave a Reply