የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ነርስ ከ6ኛ ፎቅ በመዝለል ራስን የማጥፋት ሙከራ ፈጸመችው

ከ6ኛ ፎቅ ላይ በመዝለል ራስን የማጥፋት ሙከራ ፈጸመችው የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ነርስ በሕይወት ተረፈች

– ተጎጂዋ ከአደጋዉ በሕይወት ብትተርፍም ከባድ ጉዳት ደርሷባታል

ዛሬ ሌሊት 10:30 በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዉስጥ አዋላጅ ነርስ የሆነች ዕድሜዋ 40 የተገመተ ነርስ ከሆስፒታሉ ከ6ኛ ፎቅ ላይ ዘላ ወደ ምድር በመዉደቋ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባት የእሳት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል፡፡

ከ6ኛ ፎቅ ላይ በመዝል ወደ ታችኛዉ ወለል ላይ የወደቀችዉን ተጎጂ ከወደቀችበት ለማንሳት ምቹ ሁኔታ ባለመኖሩ ለኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ጥሪ መደረጉን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል። የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችም በመሰላልና በገመድ በመጠቀም ተጎጂዋን በሕይወት ማውጣት መቻላቸው ተነግሯል።

ተጎጂዋ በሆስፒታሉ ተረኛ አዋላጅ ነርስ ሆና ምሽቱን የተለመደ ሥራዋን ከባልደረቦቿ ጋር ስታከናዉን ቆይታ መስኮቱ ላይ ወንበር ካስቀመጠች በኋላ ዘላ ወደ ምድር መዉደቋን ንጋቱ ማሞ ጨምረዉ ለሬዲዮ ጣቢያው ተናግረዋል፡፡
https://t.me/addismaleda

See also  በአፋር የተደበቁ 15 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Leave a Reply