አውሮፓ ሕብረት ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋገጠ፤ ተመድም ተመሳሳይ ቃል ገባ

ሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም 27 የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሕብረቱ ከፍተኛ ተወካይ (የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ምክር ቤት) ሊቀ መንበርነት ባደረጉት ስብሰባ÷ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ቀስ በቀስ ወደ መደበኛ ደረጃ ለማድረስ አዲስ እና መሰረታዊ መደምደሚያዎችን በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።

ውሳኔው በሕብረቱ እና በኢትዮጵያ መካከል ባለው አጋርነት ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባሕር ለአውሮፓ ሕብረት ቁልፍ ስትራቴጂካዊ አጋር መሆኗም ተጠቅሷል፡፡

በመሆኑም የአውሮፓ ሕብረት ኢትዮጵያ ወደ ዘላቂ ሰላም በሚወስደው መንገድ ላይ የምታደርገውን ተጨማሪ መሻሻል ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡

ስለሆነም በእነዚህ አዲስ የፖሊሲ መደምደሚያዎች ሕብረቱ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ለተፈረመው ዘላቂ የጦርነት ማስቆም የሰላም ስምምነት ሙሉ ድጋፉን ገልጿል።

የስምምነቱን ትግበራ ቀጣይነት መሰረት በማድረግም÷ የአውሮፓ ሕብረት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ከጠንካራ የፖለቲካ እና የፖሊሲ ውይይት ጋር መደበኛ በማድረግ ወደ ሙሉ እና የተጠናከረ ስትራቴጂያዊ ግንኙነት እንዲመለስ እንደሚያደርግ አመላክቷል፡፡

በዚህ አውድ ውስጥ በተለይ ተጠያቂነት እና የሽግግር ፍትህ አስፈላጊ መሆናቸውንም ነው ሕብረቱ የገለጸው፡፡

የአውሮፓ ሕብረት የሽግግር ፍትሕን በተመለከተ የወጣውን ግሪን ፔፐር (Green Paper) በመቀበል የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መመዘኛዎች እና ደንቦች ጋር በተጣጣመ መልኩ በውስጡ የተካተቱትን አማራጮች በማሻሻል ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስድ ያበረታታል።

በምክር ቤቱ መደምደሚያ ላይ የአውሮፓ ሕብረት በአብዛኛዎቹ ግጭት በተከሰተባቸው የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች በቅርቡ የተሻሻለውን ሰብዓዊ አገልግሎት አቅርቦት በደስታ እንደሚቀበለውም ነው የተመለከተው፡፡

በከባድ ድርቅ እና ሌሎች ቀውሶች የተጎዱትን ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ጨምሮ የተስፋፋው የሰብዓዊ ዕርዳታ ፍላጎቶች በቂ እና የተቀናጀ ምላሽ የሚሹ መሆናቸውንም እንደሚያምንም አስታውቋል፡፡

ከዚሁ ጎን ለጎን የኦሮሚያና የአማራ ክልሎችን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ጥቃቶች የአውሮፓ ሕብረትን በእጅጉ እንዳሳሰበው ገልጿል።

See also  ባለቀይ መለዮ- በቁርጠኝነትና ታማኝነት የታወቀ የውጊያ የማርሽ ቀያሪ

የኢትዮጵያ መንግስት ግልፅ፣ ሁሉን አቀፍ፣ አካታች እና ሕዝብን ያማከለ ብሄራዊ የውይይት ሂደት እንዲቀጥል የአውሮፓ ሕብረት ጠይቋል፡፡

በመላው ኢትዮጵያ የግጭት አፈታት፣ ዕርቅ እና የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን በማጠናከር ላይ ተጨማሪ መሻሻል እንዲኖር የአውሮፓ ሕብረት መደበኛ የባለ ብዙ-ዓመት የልማት አመላካች መርሐ ግብሩን (EU MIP) እንደገና ለመጀመር ዝግጁ መሆኑንም ነው ያስታወቀው፡፡

በሌላ ተመሳሳይ ዜና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ትግበራን በሁሉም መስክ እንደሚደግፍ አስታወቀ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ጉዳይ ሚኒስት ደመቀ መኮንን ከተመድ ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሀመድ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም አቶ ደመቀ መኮንን የሰላም ሂደቱ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው የሰላም አጀንዳውን በሌሎች አካባቢዎች ለመፈፀም መንግስት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ይህን ጥረት የሚመጥን ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል፡፡

ምክትል ዋና ፀሐፊዋ ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯን በራሷ መፍታቷን አድንቀው፥ ፈታኝ የሆነውን የሰላም ሂደት ትግበራ በሁሉም መስክ እንደግፋለን ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ የመልሶ ማቋቋም ዳግም ግንባታ እቅዱን ማገዝ እንደሚገባ በመጥቀስም፥ ሰላሙ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተስፋ ሰጪ መሆኑን ዋቤዎቹን አመሳክሮ የዘገበው ፋና ነው።

ለወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ አንድ ሚሊዮን የጉልበት ሰራተኛ ይፈለጋል፤ ከአንድ ነጥን አንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ሰሊጥ ይጠበቃል
   Facebook   Twitter   Messenger   Linkedin   Pinterest "ከየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል አስተማማኝ ሰላም ያለው እዚህ ነው። ለሰራተኞች እንደ ቤተሰብ ዝግጅት አድርገናል። ኑ" ሲሉ የተሰሙት አምስት መቶና ሶስት መቶ ሄክታር ሰሊጥና ማሽላ ያመረቱ ባለሃብቶች ናቸው። የዞኑ ግብርና ቢሮ ሃላፊ እንዳሉት አንድ …
የጎንደርን ከተማ ምን አይነት ተኩስ እንደሌለ ተገለጸ፤ ጎንደር ተይዛለች ተብሎ ነበር
"ጎንደር ከተማን ሙሉ በሙሉ ይዘናታል" ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ ጠይቀው ለጀርመን ድምጽ መረጃ በሰጡ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ ቃል አቀባይ አየር ማረፊያውን ሆን ብለው እንዳልያዙ አመልክተዋል። እሳቸው ተናገሩ የተባለው በጀርመን ድምጽ እየተሰማ በለበት ሰዓት በተመሳሳይ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ውጊያ …
“የሞተው ባልሽ ገዳዩ ወንድምሽ፣ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ”
የሞተው ባልሽ ገዳዩ ወንድምሽ (ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ) የሚለው የቆየ ተረት ልብን የሚያደማ ኩነትን ማሳያ ነው። እቺ መከረኛ ሚስት ባልዋ በእናቷ ልጅ ወንድሟ ተገደለ። ሟች ባል፣ ገዳይ ወንድም … ኢህአፓ "ሃይማኖት ነው" በሚል ሲገልጸው በነበረው ትግል በቀይና …
በአማራ ክልል የተነሳው ጦርነት በሰላም ሊቆጭ እንደሚችል ተሰማ
በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ጦርነት በሰላማዊ መንገድ የሚቋጭበት አግባብ ተስፋ ሰጪ ደረጃ መድረሱ ተሰማ። የኢትዮ12 የዜና አቀባዮች እንዳሉት ሰላም ወደድ የሆኑ ዜጎች ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እያደረጉ ያለው ጥረት ውጤታም እየሆነ መሆኑንን ነው ያመለከቱት። በሰላም ጥረቱ ውስጥ የሚሳተፉትን ወገኖችና …

Leave a Reply