አርባ አምስት ደቂቃ በስደት የቆየሁት “ኢትዮ ልሳን ተጋሩ” በሚል ስያሜ በሚጠራ የፓልቶክ ውስጥ አገር ነው። እዚህ አገር የስራ ቋንቋው አማርኛ በመሆኑ ሾልኮ የገባ መረጃ የማግኘት ችግር የለበትም። በለብታ መረጃውን ሲያወርዱት በመካከሉ “ ይህን ጉዳይ በውስጥ መስመር እናድርገው” ከሚል ማሳሰቢያ በቀር በስደት ቆይታዬ ያመለጠኝ ነገር የለም።

የአርባ አምስት ደቂቃ ስደተኛ

ያለምንም ማጋነን በዚህ “ ተጋሩ “ በሚብላ ጥቂቶች በፈጠሩት የፓልቶክ አገር ውስጥ ሆኖ የሚባለውን መስማት ለአንድ ኢትዮጵያዊ ከስደትም በላይ ነው። ኢትዮጵያን እንዴት አድርገው እንደሚያፈርሷት እቅድ ያወጣሉ። ኢትዮጵያን በማፍረሱ በኩል ክርክር የላቸውም፣ ስምምነት የተደረሰበትና በአርማታ የተዘጋ አጀንዳ ነው። እነሱ ሊያፈራርሱን፣ እኛ ልንፈራርስ!!

ውይይቱ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተያዘውን “ መሪ ዕቅድ” እንዴት ማፋጠን ይቻላል በሚለው ጉዳይ ነው። እኔ በስደት በቆየሁበት አርባ አምስት ደቂቃ ታዲያ አንዱና ዋናው መሳሪያ ሚዲያ በመሆኑ “ዲጂታል ወያኔ” የሚባል ዌብሳይት መክፈት፣ ወደ ሳተላይት የሚገባ የቴሌቪሽንና ሬዲዮ ፕሮግራም ማስጀመር የሚለው የውይይት አጀንዳ በስፋት ተነስቶ ድንገት ቦንብ ፈነዳ።

አቅጣጫና ሃብት – ከፍንዳታው በፊት

ሳቢና አክሱም የምትባለዋ ተናጋሪ “location and finance” ስትል የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ክፍለጊዜ ስለሚጀመርበት አግባብ አወጋች። ሱዳን በመጀመሪያ ደረጃ ስትራቴጂክ አገር መሆኗን፣ ከዚያ ቀጥሎ ኬንያ እንደምትከተል አስረዳች። ሱዳን በርካታ ትግራዋይ ጋዜጠኞችና የተለያዩ ባለሙያዎች ስላሉ በቀላሉ መቅጠር እንደሚቻል። አሜሪካና አውሮፓ የሰራተኛ ደመዎዝ አስቸጋሪ በመሆኑ ሱዳንን መጠቀም ግድ እንደሚሆን… ሃሳቡ በአዎንታ ተቀባይነት አገኘ።

በስካንዲቪያን አገሮች ብቻ 50 ሺህ የሚጠጉ ትግራዋይ እንዳሉ፣ በአማኤሪካ ካናዳና አውስትራሊያም… ብቻ ስሌቱ ተሰላና የፋይናንስ ችግር ሊኖር እንደማይችል ስምምነት ላይ ተደረሰ። ነገር ግን ይህን ሃይል ማስተባበር ቀላል እንደማይሆን ተጠቁሞ አንድ የቋሚ ክፍያ ዘዴ መመቻቸት እንዳለበት ማስታወሻ ተያዘ።

“ የትግራይ ሕዝብ የትግራይ መከላከያ ሰራዊትና እናንተን ይዘን አናፍረም” በሚል ስልክ እንደሚደውል አንዱ ተናጋሪ ገለጸና ሳቅ ተጀመረ።

ፎጣ ለባሽ 

“ ፎጣ ለባሽ ” በእነሱ አገላለጽ እኔ ነበርኩ። ወይም እኛ ነን። ቃል በቃል “ ጎንደሬን” እየጠሩ እንደነሱ ዓይነት “ የፎጣ ለባሽ ጎንደሬ አይነት ኪስ ውስጥ የሚያዝ ሚዲያ አንከፍትም” ሁሉም ሳቁ። ለጊዜው ግብቼ ለመናገር ክጅሎኝ ነበር። እስከመጨረሻ መስማት ስላለብኝ ታገስኩ። “ጠኔያም ሁሉ” እያልኩ ሰማሁ። ሲስቁ ሊዘባርቁ የፈለጉት ብዙም ዋጋ ስለማይኖረው ልተወውና በንግግራቸው ውስጥ “ ፎጣ ለባሽ” ያሉትን ሃይል ሊበሉት እንዴት እንደሚከጅሉና ሌት ተቀን እንደሚቃዡ መጠቆም እወዳለሁ። የገረመኝ ግን እነሱን የሚመስሉ “ አማሮች” ያሉዋቸው አሉ። ይህኔ ነው ወራጅ … እርስ በርስ ጎጃሜ፣ ጎንደሬ፣ ሸዋ፣ ወሎዬ የምትል ሁሉ ዋ!! ከወዲሁ አንድ ሁን። የትህነግ ወራሽ ሁላ፣ አማራ እመራለሁ እያለ ለዳግም ዱላና እንዳይዳርገን!!

የትግራይ ሚዲያ ቦርድ ብሎ ነገር የለም

“ትልቅ ድረ ገጽ መቋቋም አለበት” በሚል ሃሳብ የተጀመረውና የሳተላይት ቴሌቪዥን ስለመጀመር አስፈላጊነት ሲምከሩ የነበሩት እጅግ ጥቂት የትግራይ አገረ መንግስት መስራቾች ቃል በቃል “ የራሳችን አገር ለመመስረት ጊዜው አሁን ነው” በሚል በነደፉት ስልት ወዲያው ልዩነት አንስተው ተታኮሱ። ቦንቡ ፈነዳ!

ቤን የሚባለው የፓልቶክ አገር ትጋሩ ተዋናይ “ አንድ የሚያዲያ ቦርድ ተቋቁሟል” ሲል መረጃዎችን ወጥ የማድረገ፣ ህግና ደንብ አውጥቶ የመቆጣጠር ወዘተ ስራ እንደሚሰራ ሲያብራራ፣ ሃንዛ ጥይቱን ተኮሰ። አሁን የፓልቶኳ ተጋሩ ሞቀች።

“ እኔ” አለ ሃንዛ “ እኔ የምኖረው አሜሪካ ነው። የማከብረውም የአሜሪካንን ህግ ነው። አንድ ተጋሩ … አምባሳደር አክቲቪስት ምናምን መጥቶ ልቆጣጠር ካለ ዞርበል ነው የምለው” ሲል ተቋቋመ የተባለውን የትግራይ የውጭ አገር ሚዲያ ቦርድን እንደማይቀበል ተናገረ። አከለና ጉዳዩ ሕዝብን ማስተባበር ነው። ግንኙነቱም ከህዝብ ጋር ሊሆን እንደሚገባው አጥብቆ አቋሙን ገለጸ።

ቤን ለማስረዳት ሞከረ። አንድ ሬስቶራንት ሲከፈት በአገሩ ደንብ መሰረት መሆኑንን አመልክቶ ስለ ቦርዱ ለማብራራት ሲሞክር ነበልባል የሆነችው ሳቢና አክሱም ገባችና “ ሁሉም ሚዲያ ዓላማ ዓለው። ዓላማህን ላውጣልህ አይባልም” ስትል ተቃውሞዋን አቀረበች።

“ አስፈላጊ ከሆነ ሁሉም ሚዲያ የራሱን ቦርድ አቋቁሞ ይሰራል እንጂ ህግ ባለበት አገር ሌላ የሚዲያ ህግ ሊወጣ አይችልም” ስትል ሃንዛን ደገፈች። ንግግሯ የከረረና እንደማትስማማ የገለጸችበት መንገድ “ በቃ” አይነት በመሆኑ ውይይቱ ወዲያው “ ቱርክ ለኢትዮጵያ ምንም አታደርግም” ወደሚለውና “ ሩሲያ ኢትዮጵያን ካገዘች አደገኛ ይሆናል” ወደሚለው ስሜትና ህልም ላይ የተተከለ የ“ጨዋ” የሚባለው አይነት ኮተት ወሬ ተቀየረ። በነገራችን ላይ ነባር አምባሳደሮች ያሉበት በውጭ አገር የትግራይ ሚዲያ ቦርድ ይፋ ሆኗል። ቦርዱ ትግራይን አስመክቶ ወጥ የሆነ መረጃ እንዲሰራጭ፣ ልዩነት እንዳይፈጠር በውጭ አገር ሆኖ ሌላ የሚዲያ ህግ ለማውጣት ወይም የተለየ ሃሳብ እንዳይንሸራሸር በር ለመዝጋት ያለም ነው።

ኦኤም ኤን ተጠልፏል

ሳተላይት ቴሌቪዥን ለመጀመር በቀረበው ሃሳብ ላይ የአቶ ጃዋርን ሞዴል መጠቀም እንደሚያስፈልግ በምሳሌነት ሲስነሳ ቢኒ “ ጃዋር ጎበዝ ነው። ከኳታር እርዳታ ያገኝ ነበር” በማለት እነሱም የውጭ አገር እርዳታ የሚየገኙበትን አግባብ መሞከር እንዳለባቸው አነሳ። ኢሳት ከኤርትራና ከግብጽ ሲረዳ ነበር ሲሉም አከሉ። ሳተላይት ርካሽ የምታከራየው ግብጽ ስለሆነች ግንኙነት እንደሚጀመር አወሳ።

አሁንም ሳቢና አክሱም መጣችና “ ኦኤም ኤን ዛሬ ተጠልፏል፤ ለጃዋር እየታገሉ አይደለም። እነ ህዝቅኤል ገቢሳ እንኳን ኩሽ ሚዲያ ላይ ብቻ ነው ያሉት” ስትል ሃዘኗን ገለጸች። አያይዛም ለወር ኪራይ አምስት ሺህ ዶላር ለመክፈል ቋሚ መዋጮ ስለሚያስፈልግ ሊረዱ የሚፈልጉ ኦሮሞዎች፣ አማራዎችና የውጭ መንግስታትን በአግባቡ እርዳታ መጠየቅ አስፈለጊ መሆኑንን ገለጸች …

እኔ – ፎጣ ለባሹ

እኔ ፎጣ ለባሹ እዛ ሰፈር የሄድኩትና በፈቃደኛነት የ45 ደቂቃ ስደተኛ ለመሆን የወሰንኩት በአንድ የተጋሩ ጓደኛዬ ግብዣ ነው። እሱ እንዳስረዳኝ ከሆነ ሰዎቹ እንደ እኔ ጓደኛ ዓይነት ለሆኑትም ጭምር እንደሚያወሩ አያውቁም። ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚባል ነገር አይታያቸውም። እንመሰርታለን የሚሉዋት “ አባይ ትግራይ” በሁለት አገር ፍርስራሽ ላይ መሆኑ እስከመጨረሻ የሚያስከፍላቸውን ዋጋ ሊረዱ አለመቻላቸው ባልደረባዬን ያበሳጨዋል።

“ትህነግ” ኢትዮጵያንና ኤርትራን አፍርሶ በሁለቱ አገሮች ፍራሽ ላይ “ ታላቋን ትግራይ” ለመገንባት” ሶስት አስርት ዓመታት በመንግስትነት ስልጣን ላይ ሆኖ ሰርቷል። እኔና ጓደኛዬ የሚያግባባን አንድ ትልቅ ጉዳይ ቢኖር “ መቶ ሚሊዮን ሕዝብ ለማፍረስ መነሳት እብደት ነው” በሚለው ስሌታችን ነው። ከዛ ደግሞ ኤርትራም አለች። እኒህን ሁለት አገሮች አመንዥገው ለመብላት ትህነጎች ምን ያህል ጊዜ ይፈጅባቸው እንደሆነም በወጉ አላሰቡም። ይቻላል ወይስ አይቻልም የሚለውን ቁልፍ ጉዳይ ትተነው!

እንደተባለው ትግራይ አገር ትሁን። ዛሬ ላይ ካላት ህዝብ ግማሹን በሴፍቲ ኔት ፕሮግራም የልመና ስንዴ እየሰፈረች የምታሳድር ክልል፣ ዛሬ ዓለም ሁሉ ስለ ረሃቧና ጥማቷ የሚያወራላት ትግራይ ለመሆኑ ሰላሳ ዓመት እንዴት ነበር የከረመችው? ዛሬ በላይቭ ረሃቧ ሲዘገብ፣ ልብን የሚደቁ ምስሎች ሲሰራጩ፣ አዕምሮ የሚያውኩ መረጃዎች ፖለቲካውን ለማጦዝ በሚል ሲለቀቅ እያየን “ በፉገራ ሌጋሲ በመኖራቸው የሚያፍሩ፣ ሰላሳ ዓመታት በቁጩ ሌጋሲ መጠርነፋቸው የሚያማቸው የትግራይ ጀግኖችን ማየት ሲገባን እያለቀሱ ፉከራ የሞት ሁሉ ሞት ነው”

የመውጪያም ሆነ የመግቢያ ኮሪዶር የሌላት፣ በግራና ቀኝ ሆን ተብሎ ጠላት የተበጀላት ምስኪን ክልል እንዴትስ ነው አገር ልትሆን የምትችለው? የሚለውን ሁሉ አቀፍ ጥያቄ በማንሳት አገ እንዲህ ባሉ ቀፎዎች መመራቷ ያሳፍርላ ከማለት ውጪ ምን ይባላል?

ወዳጄን አመስግኜ ከአርባ አምስት ደቂቃ የስደት የፓልቶክ አገር ስወጣ ETHIOPIA LAND OF HORIZON” የሚለው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሞቶ ታወሰኝ። ኢትዮጵያ በአዲስ አድማስ ስር መከራዋንና የመርዘኞችን መውጊያ እየነቀለች መሆኗንን አሰብኩ። ከሁሉም በላይ “ የወረስነው የእዳ ጽሁፍ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እግር በግር በመከታተል የሚቆረጡ በርካታ ጉዳዮች እንዳሉ የተናገሩትን ሚስጢር አሰላሁት።

በዚህ ጉዞ “ የሚጠሉን የምንሰራው የገባቸው ናቸው” ሲሉ እኚሁ ጠቅላይ ሚኒስትር የተናገሩትን ደግሜ አላምኩት። በስደት አርባ አምስት ደቂቃ በቆየሁበት ተጋሩ ሌሎች ተመሳሳይ ድቅያ ያላቸው የሳይበር ሰራዊቶች ለይተው የሚያደቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩን መሆኑ ንግግራቸው እንዲገባኝ ረድቶኛል። በተለይም በመናበብ የሚሰሩት “ የተጋሩ አጋር ሚዲያዎች” ለዚህ “ እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” ዘመቻ የሚሄዱበትን እርቀት ሳስብ “ ኢትዮጵያን ማዳን ወይስ አብይን ሲዘልፉ ውሎ ማደር ይቀድማል?” የሚለው ጥያቄ ነብሴን ይወጥራታል። “የበላን ያብላላል” እንዲሉ ምን ያህል ጎርሰው እንዲህ እንደታወሩ …

በቀጣይ “እንቡጡን በጥስ፣ እንደበተስከው የምታውቀው አንተ ብቻ ነህና” በሚል ጥሁፍ እመለሳለሁ

ዋለ ሃይሌ – ከፎጣ ለባሾቹ አንዱ

  • በሀሰተኛ ሰነድ ህጋዊ ባለቤቱ ሳያውቅ ቤት በሸጠውና በተባበረው ላይ ከባድ የሙስና ክስ ተመሰረተ
    በሀሰተኛ ሰነድ ህጋዊ ባለቤቱ በማያውቅበት ሁኔታ የራሱ ያልሆነን ቤት በሸጠው እና በተባበረው ግለሰብ ላይ ከባድ የሙስና ወንጀልና በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ክስ ተመሰረተ በኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ ሀሰተኛ ስምና ሰነዶችን በመጠቀም ህጋዊ ባለቤቱ በማያውቅበት ሁኔታ 72 ካ.ሜContinue Reading
  • የታዳጊዉ ወጣት በጎነት -በህግ ማስከበር ዘመቻ
    ታዳጊዉ ወጣት ተመስገን ጥጋቡ ይባላል፡፡ተወልዶ ያደገዉ በሰቆጣ ከተማ ነዉ፡፡አባቱ መቶ አለቃ ጥጋቡ አማረ ይባላል የመከላከያ ሰራዊት አባል ሲሆን ለሀገሩ ሰላም መከበር ሲል መስዋእትነት ከፍሏል፡፡ እናቱ ወይዘሮ በላይነሽ ዳዊት ትባላለች ህፃን እያለ በህይወት እንዳጣት ታዳጊዉ ወጣት ተመስገን ተናግሯል፡፡ አባቱ መቶ አለቃ ጥጋቡ አማረ የመከላከያ ሰራዊት አባል ሆኖ ሀገሩን ሲያገለግል ከቆየ በኋላContinue Reading
  • “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በበጀት ዓመቱ 7.5 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል” የፕላንና ልማት ሚኒስቴር
    የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዘንድሮ በ7 ነጥብ 5 በመቶ እድገት የሚመዘግብበት መሆኑን የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም እንደሚያመላክት ተጠቆመ። የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ተካሂዷል። በመድረኩም የበጀት ዓመቱ የስድስት ወራት ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚና የዘርፎች አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል። ሪፖርቱን ያቀረቡትContinue Reading

Leave a Reply