አውሮፓ ህብረት – ላለፉት 28 ዓመታት በኢትዮያ ተላላኪ መንግስት እንደነበር ለኢትዮጵያ ህዝብ አመነ

“የአውሮፓ ህብረት ምርጫ የማይታዘበው በበጀት እጥረት መሆኑንን ገልጾልናል” ሲሉ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ። ህብረቱ ወዲያውኑ ” በበጀት እጥረት ምክንያት ሳይሆን የቀረነው ስላልተጋበዝን ነው” ሲል ድምጹን አሰማ። ምላሽ ሰጠ። ጉዳዩ ከዚያ በላይ አልሄደም። ነገሩ ህወሃት የሚባለው አገዛዝ ቀደም ሲል የገባው ኮንትራት ነበርና ብዙም አስገራሚ እንዳልነበር በወቅቱ ብዙ ተብሎ እንደነበር ይታወሳል።

አውሮፓ ህብረት ንበረትነቱ የህወሃት በሆነ ምርጫ ቦርድ፣ ህወሃት እስከታች በጠረነፈው መዋቅር፣ ጋዜጠኖችና ሰላማዊ ተቃዋሚዎች መንቀሳቀስ በማይችሉበት፣ ነጹሃን “ድምጻችን ተሰረቀ” በሚል ሲጠይቁ በጥይት ተጨፍጭፈው የተገኘን የአሸናፊነት ውጤት አምኖና ” ዴሞክራሲያዊ ” በሎ የተቀበለ ተቋም እንደሆነ የሚዘነጋ አይደለም። እሱ ብቻ ሳይሆንም አሜሪካኖችም በተመሳሳይ ፈረሳቸውን ሲያሞካሹና ሲመሰክሩለት እንደነበር ማንም የማይክደው ሃቅ ነው።

“የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ላለፉት ሃያ ስምንት ዓመታት የሚፈልገው አይነት ተላላኪ መንግስት ተተክሎ እንደነበር ለኢትዮጵያ ሕዝብ አረጋገጠ” ሲሉ አስተያት የሰጡ ወገኖች መነሻቸው ከላይ የተገለጸውና ዛሬ ላይ የተሰጠው መግለጫ ነው። ህበረቱ ቀደም ሲል እየለመነ የሚታዘበውና ሙሉ በሙሉ በህወሃት አሸናፊነት የሚደመደመውን ምርጫ ” ህጋዊና ዴሞክራሲያዊ ” ሲል የኖረው ህወሃት የሚባል እንዳሻው የሚላላክለት ” እቃ” መንግስት ስለነበረው ነው።

Related stories   ከብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

ለዛጎል አስተያየት የሰጡ ወገኖች ” ካሁን በሁዋላ በኢትዮጵያ ተላላኪ መንግስት አይፈጠረም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መናገራቸውን፣ ይህንንም የተናገሩት የአውሮፓና ሌሎች አገራት ሚዲያዎች ባሉበት መሆኑንን አስቀድመው ያነሳሉ። አብይ አህመድ ለነጮቹ በደንብ አድርገው የሚነግሩዋቸው አካላቶች ባሉበት ” እጅ ጥምዘዛ አይሆንም” በማለት ካሁን በሁዋላ ስልጣን በህዝብ ” ምርጫ ብቻ” እንደሆነም አስረግጠውም ገልጸዋል። አስተያየት ሰጪዎቹ ይህንን ካስታወሱ በሁዋላ ” ህብረቱ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ቀሏል፤ ኢትዮጵያም ምን ያህል ባዋረዷትና ባቆሸሽዋት ተላላኪዎች ስትመራ እንደኖረች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። የተናቀ ህዝብ በቁጣና እልህ ምላሽ ሊሰጥ ይገባል” የሚል ሃሳብ ሰንዝረዋል።

ዛሬ ምርጫ ቦርድን የሚመሩትን ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ማንም የሚጠራጠራቸው አካል እንደማይኖር፣ ተቃዋሚዎች ሳይቀሩ ምስጋና በአደባባይ የሚሰጥዋቸው መሆናቸው፣ ተቋሙ በነጻነት የመፍረድ አቅም የተጎናጸፈ መሆኑ ህብረቱን በትዕዛዝ የሚፈልገው ዓይነት ” ተላላኪ” መንግስት እንደማይመረጥ ስላረጋገጠ በማይሆንም ምክንያት ምርጫ እንደማይታዘብ ይፋ ማድረጉን አስተያየት ሰጪዎቹ ይገልጻሉ።

See also  «ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ

Related stories   Why Egypt’s and Sudan’s “Fears” Over GERD Are Exaggerated!

ሰብለ ወንጌል ሃይሌ ነዋሪነቷ ደቡብ አፍሪካ ነው። በደቡብ አፍሪካ የሲቪል ተቋም እንደምትሰራ ተናግራለች። እሷ እንደምትለው የአውሮፓ ሕብረት ራሱን በራሱ የሃፍርት ማቅ ውስጥ ከቷል።

” ቢያንስ ብርቱካን ሚደቅሳንና እሷ የምትመራውን ተቋም ማክበር ሲገባው የስለላ መሳሪያ ላስገባ ብሎ ከምርጫ ታዛቢነት ማግለሉ ቀደም ሲል ኢትዮጵያ በነሱ ተላላኪዎች ስትመራ እንደነበረች ማረጋገጫ ከመስጠት የዘለለ ትርጉም የለውም። ይህንን ሃቅ በማረጋገጣቸው ምስጋና የገባቸዋል” የምትለው ሰብለ ” ወያኔዎች አስንቀውናል፣ አዋርደውናል፣ ተልከስክሰው አልከስክሰውናል።ከሰውነት ተራ ወጥተው መሳቂያ አድረገውናል። ይህ ያሳዝናል? ህብረቱ ይህንን አረጋግጦልናል። ሕዝብ ከእንግዲህ ራሱ በሚፈልገው ለመተዳደር መውሰን አለበት” ስትል ጥሪዋን አቅርባለች።

Related stories   Ethiopia, Kenya exchange views to deepen ties

” ባንዳነትን አንፈቅድም” ያለችው የአውሮፓ ህብረት መቶ ከመቶ ተላላኪው መንግስ ምርጫውን በአሸናፊነት ሲጠናቅቅ አጃቢ ሆኖ መኖሩ ሊያሳፍረው ሲገባ ይህንኑ ገድሉን ” ምርጫውን አልታዘበም” በሚል መናገሩ ለኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ ድልም ጭምር መሆኑን አውስታለች። አያይዛም ” የህግ ያለህ፣ የሰብአዊ መብት ያለህ፣ ብለን ስንጮህ እያውቁ እንዳልሰሙ ሆነው ዝም እንዳሉንም ማረጋገጣቸውን ህዝብ ተረድቶ ዞር በሉ” ሊላቸው እንደሚገባ አመልክታለች። በበርካታ ጉዳዮች ሊያጠቁን ይነሳሉ አንድ እንሁን ስትልም አደራ ብላለች።

በቀጣዩ ምርጫ ፓርላማው በርካታ የተቀናቃኝ ፓርቲ አባላት እንደሚገቡበት ምንም ጥርጥር እንደሌለው በርካቶች ያምናሉ። ፓርላማው በሃሳብ ሙግትና ደረጃ ከፍ የሚልበት ምርጫ እንደሚሆን አውሮፓ ህብረትም ይረዳል። የህግ ሰዎች እንደሚሉት ህብረቱ ድህነት ላይ መሰረት ያደረገ ጥቃት ከመፈጸም የዘለለ ምርጫን እውቅና የመንፈግ ማንዴት እንደሌለውም አመልክተዋል። ጉዳዩ ተረኛ ተላላኪ መንግስት የማቆም ብቻ እንደሆነም ጠቁመዋል።


  • “ደብረ ኤሊያስ ገዳም የደረሰበት ጉዳት የለም” ወረዳው፤ መከላከያ ስራውን መጨረሱ ተሰማ
    አካባባዊ በተለይም ገዳሙ ወታደራዊ ማስለጠኛ፣ የሚፈለጉ ሰዎች መመሸጊያ፣ ሃይማኖታዊ ዓላማውን የሳተ በመሆኑ በአባቶች፣ በሃይማኖት መሪዎች፣ በመንግስት ሃላፊዎችና ታውቃ ሰዎች ቢለመኑም ፈቃደኛ እንዳልሆኑ፣ በስተመጨረሻም ደብሩም ሆነ መኖኮሳቶች ምንም ሳይሆኑ መከላከያ ገብቶ ስራውን አከናውኖ መጨረሱ ተሰማ። በርካታ ታጣቂዎች ለመከላከያ እጃቸውን መስጠታቸውም ተገልጿል። ወረዳው መከላከያ ስራውን ጉዳት ሳያደርስ ማከናወኑን ይፋ ሲያደርግ እጅቻውን ስለሰጡናContinue Reading
  • አሮጌውን ወይን በአዲስ አቁማዳ ! የኖርንበት ፣ የቸከ የሰለቸ የፖለቲካ …
    የኢትዮጵያ ታሪክ የእርስ በእርስ ጦርነት civil war & strife ነው። ይሄንን ያደፈ ጉድለታችንን ማስተካከል የምንችለው መሀከለኛውን መንገድ የያዙ ስብስቦችን በማብዛት ነው። ችግሩ በእኛ ሀገር ፖለቲካ መሀከሉን መንገድ ልትይዝ ስትሞክር የሚወረወርብህ ፍላጻ መብዛቱ ነው። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ኢዜማ ነው። ህወሃትም ፣ የኦሮሞ ብሄረተኜችም ፣ በቅርብ የተፈለፈሉት የአማራ ብሄረተኞችም ለፓርቲው ያላቸውን ጥላቻContinue Reading
  • US Special Envoy for HoA Amb Mike Hammer to Visit Ethiopia
     US Special Envoy for the Horn of Africa Ambassador Mike Hammer will visit Ethiopia on May 31 – June 6. In Ethiopia, Ambassador Hammer will meet African Union officials on implementation of the November 2, 2022 Cessation of Hostilities Agreement (COHA). He will discuss progress and priorities including transitional justiceContinue Reading

Leave a Reply