December 3, 2021

አቡካዶ ቀጣዩ ወርቅ!ከግብርናው ዘርፍ ስኬት ተንጥሮ በዳታ የተደገፈ መረጃ ይፋ ተደረገ

መንግስት ባለፉት ሶስት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ ማሳካት ከተቻለው ግቦች መካከል ቆንጥሮ ይፋ አድርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በማህበራዊ ገጻቸው ይፋ ያደረጉት መረጃ እንዳሳየው አቡካዶ ቀጣዮ ወርቅ እንደሚሆን አመላክቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ይፋ ባደረጉት መረጃ  በገበያ መር የግብርና ልማት አሰራር አጠናክሮ ለመተግበር እንዲያገዝ ገበያ መር ኩታ ገጠም እርሻ ልማት በ3 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄከታር ላይ 10 ሰብል ምርት አይነቶች በአራት ክልሎች እየተሄደ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ከአነስተኛ እሰከ ከፍተኛው ኮምባይነር እና የመሰኖ ውሃ መቆፈሪያ ሪግ እና ሌሎች የእርሻ መሳሪያዎችንና ግብዓቶችን አቅርቦት ቀላል እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሆን ለማድረግ በማንኛውም ደረጃ ከውጭ የሚገቡ የአርሻ መሳሪያዎችን ከቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሁም በሀገር ውስጥ ለማምረትና ለመገጣጣም የሚያሰፈልግ ግብዓት በተመሳሳይ ከማንኛውም ዓይነት ቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲደረጉ ተወስኖ መተግበር ተጀምሯል ተብሏል፡፡

May be an image of text

በአለም ገበያ ተቀባይነቱ እየጨመረ የመጣሁን የአቮካዶ ልማት ለማስፋፋትም ገበያ መርኩታገጠም እርሻ ልማት 34 ሺህ 271 በሄክታር መሬት ላይ ለምቷል።ከሁለት አመት በፊት በሙከራ ላይ የነበረው የመስኖ ሰንዴ በሚቀጥለው አመት እሰከ 7 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ ያስችላል።የደጋማ አካባቢ የተሻሻለ የሰንዴ ምርትና ምርታማነት በቴክሎጂ አጠቃቅም እና በአሲዳማነት የተበላሹ የሰንዴ መሬት በማከም የሚከናውን ሲሆን በምርት ዘመኑ 9 መቶ ሺህ ሄክታር የስንዴ መሬት በእነዚህ አሰራሮች የለማ ሲሆን ይህም በአጠቃላይ ሀገራዊ የስንዴ ምርታማነት ላይ የ13 ነጥብ 88 በመቶ እድገት አስመዝግቧል፡፡

በ2012 በጀት አመት የፅጌሬዳና የበጋ አበባ የወጪ ንግድ መጠን ሲታይ 74 ሺህ ቶን ለመላክ የተቻለ ሲሆን የቅንጥብ አበባ የወጪ ንግድ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን መላክ ተችሏል፡፡የቡና ምርታማነትን ከ6 ነጥብ 19 ወደ 7 ነጥብ 5 ኩንታል በሄክታር ማሳደግ የተቻለ ሲሆን በእርጅና ምክንያት ምርት መስጠት ያቆሙ እና ምርታማነታቸው የቀነሰ 297 ሺህ 330 ሄክታር የቡና ማሳ ታድሶ ወደ ልማት እንዲገባ በማድረግ አጠቃላይ ምርት ከ508 ሺህ 839 ወደ 680 ሺህ 800 ኩንታል ጨምሯል።

የመስኖ አቅርቦትን ለማሻሻል በተለይም በአርብቶ አደር አካባቢዎች የመስኖ መኖ ልማት ላለፉት ሁለት ዓመታት በተደረገ የሙከራ ትግበራ በማስፋት በዚህ ምርት ዘመን 1496 ሄክታር ማልማት ተችሏል።የአንሰሳት ጤናን ለማሻሻል በሶሰት አመታት ሰጋት ላይ የተመሰረተ የክትባት አገልግሎት ሽፋን 90 በመቶ ሲደርሰ ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ 10 በመቶ አድጓል።ከ2011በጀት ዓመት ጀምሮ እስካሁን 121 ሺህ 356 ሄክታር ሊያለሙ የሚችሉ የመስኖ አውታሮች በግለሰብ እና ማህበረሰብ የሚተዳደሩ ዝግጁ ሆኗል።

በባለፋት ሶስት አመታት 254 የሚሆኑ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ የግብይት ማእከላት በተለያዩ ክልሎች ተገንብተውና ተደራጅተው አገግሎት ላይ ውለዋል፡፡በሌላ በኩል በባፉት ሶስት አመታት በገጠር ለሚኖሩ የተማሩ፣ ያስተማሩና ትምሕርት ላቋረጡ ወደ ስራ በማሰማራት በሰባት ዘርፎች በአጠቃላይ በቋሚና በጊዜያዊ 4 ነጥብ 2 ሚሊየን የስራ ዕድል ተፈጥሯል።በሶሰቱ ዓመታት ከተፈጠረው የስራ እድል ውስጥ የግብርና ዘርፍ 61 በመቶ ኢንዱሰትሪ ዘርፍ 21 በመቶ እና የአገልግሎት ዘርፍ 18 በመቶ መሆኑንን ፋና ዘግቧል።


Leave a Reply

Previous post ማዕድን ቀጣዩ የኢትዮጵያ ጉሮሮ – “የሕዝብ ሃብት ለሚያባክኑ ዝምታ የለም” ታከለ ኡማ
Next post ኦሮሞ ኦሮሞን አድፍጦ እየገደለ ነው፤ ኦነግ ሸኔ ለስራ የሚጓዙ አምስት ኦሮሞዎችን ገደለ
Close
%d bloggers like this: