ኦሮሞ ኦሮሞን አድፍጦ እየገደለ ነው፤ ኦነግ ሸኔ ለስራ የሚጓዙ አምስት ኦሮሞዎችን ገደለ

” ኦሮሞ እያደፈጠ ኦሮሞን ይገድላል” በማለት ድርጊቱን የሚያወግዙ ዛሬ ላይ በኦሮሚያ ሊያገዳድልና ጫካ ሊያስገባ የሚችል ምን መሰረታዊ ምክንያት እንዳለ አይገባቸውም። “በኦሮሚያ ማንኛውም ለኦሮሞ አስባለሁ የሚል ድርጅት መሪ ቢሆን አሁን ከሚሆነው በላይ ምን የተለየ መና ለህዝቡ ያቀርባል” ሲሉ ይጠይቃሉ። ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚሰጥም አካል የለም።

የቀድሞ የምዕራብ ወለጋ ዞን ጸጥታ ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ አምስት የመንግሥት ሠራተኞች በታጣቂዎች መገደላቸውን ቢቢሲ አማርኛው ዘግቧል። ቢቢሲ ሰዎቹ የተገደሉት ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ከቆንዳላ ወረዳ ወደ መንዲ ለስራ እየተጓዙ በነበረበት ወቅት መሆኑንን የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳደሪ አቶ ኤልያስ ኡመታን ጠቅሶ ነው ያስታወቀው። ግድያውን የፈጸመው ራሱን “የኦሮሞ ነጻነት ጦር” የሚለው፣ ነገር ግን አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ኦነግ ሸኔ መሆኑንንም ዘገባው አመልክቷል።

ቢቢሲ በዘገባው ግድያውን ” ከሳምንት በፊት ከተገደለው የኦቢኤን ጋዜጠኛ ገዳይ ከተባለውና ክህግ አግባብ ውጭ እርምጃ ከተወሰደበት ወጣት ጋር አገናኝቶታል። “የአምስቱ ሰዎች የመገደል ዜና የተሰማው ከአንድ ሳምንት በፊት አባ ቶርቤ በተባለ ቡድን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኛ መገደልን ተከለትሎ የቡድኑ አባል ነው የተባለ ወጣት በመንግሥት የጸጥታ ኃይል በአደባባይ ከተገደለ በኋላ ነው” ሲል ቢቢሲ ተናጋሪውን ሳይገልጽ ዜናውን “የአባ ቶርቤ አባል” ነው ተብሎ ከተገደለው ወጣት ጋር ማያያዙ አነጋጋሪ ሆኗል።

ከዞን አመራር በተጨማሪ አንድ አሽከርካሪ እና ጥበቃ ለማድረግ ከዞን አመራሩ ጋር አብረው ሲጓዙ የነበሩ ሁለት የሚሊሻ አባላት እና አንድ የኦሮሚያ ፖሊስ አባል መገደላቸውን ተነግሯል። የዞን አመራር የቀብር ሥርዓት ትናንት መፈጸሙን የተገለጸ ሲሆን፤ እስካሁን ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር የዋለ ሰው አለመኖሩን የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪው ገልጸዋል።

አቶ ዋቅጋሪ ቀጄላ
አቶ ዋቅ ጋሪ የአራት ልጆች አባት

አምስቱ ሰዎች የተገደሉበት ጥቃት የተፈጸመው ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በሚዋሰኑበት ስፍራ መሆኑን አቶ ኤልያስ አመልክተው፤ ጥቃት ፈጻሚዎቹን ለመያዝ በአካባቢው የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ፍተሻ እያደረጉ ነው ብለዋል።

አቶ ዋቅ ጋሪ የአራት ልጆች አባት ሲሆኑ አቶ ዋቅጋሪ ቀደም ሲል የምዕራብ ወለጋ ዞን የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል። ከዚህ በፊትም የወረዳ አስተዳዳሪ እንዲሁም የከተማ ከንቱባ በመሆኑን ሰርተዋል። አቶ ዋቅጋሪ የሁለት ዲግሪ ትምህርታቸውን አጠናቀው ለምረቃ ተቃርበው እንደነበረ ተነግሯል።

See also  በአፍሪቃ ቀንድ የፖሊሲ ኩዴታ - "የጎመን ምንቸት ውጣ"

በምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኙ የኦሮሚያ አካባቢዎች ውስጥ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በታጣቂዎች በሚፈጸሙ ተደጋጋሚ ጥቃቶች በአካባቢው ካሉ የመንግሥት ባለስልጣናትና የጸጥታ ኃይሎች በተጨማሪ በርካታ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች ተገድለዋል።

በኦሮሚያ ክልል በዚህ ዓመት ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ 18 የመንግሥት ባለስልጣናት፣ 112 የፖሊስ አባላት እና 42 ሚሊሻዎች መገደላቸውን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባለፈው ሳምንት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በኦሮሚያ ወንድም ወንድሙን እየገደለ ልጆችን ያለ ወላጅ የማስቀረቱና እርስ በርስ ጠላት የመሆኑ ጉዳይ እያየለ መሄዱ አሳሳቢ መሆኑ እየተነገረ ነው። በተለይም መሰረቱን ወለጋ ያደረገው ኦነግ ሸኔ በሌሎች አካባቢዎች የኦሮሞ ተወላጆች ዘንዳ እየፈጠረ ያለው ስሜት፣ በውስጥ ለውስጥ የሚራመደው የዲቃላ ፖለቲካ ጉዳይና ስልጣንን ከሸዋና መካከለኛው ኦሮሞ ልጆች ለመንጠቅ የሚደረገው ግብግብ ሌላ መዘዝ ሳያመጣ የሚመለከታቸው ሁሉ ነገሩን እንዲያበርዱ በተደጋጋሚ የሚያሳስቡ እየበረከቱ ነው።Leave a Reply