ምርጫችን አንድ ብቻ ነው…

‹‹ተኩስ አቁም›› በምእራባውያን ለትህነግ የታዘዘ የእድሜ ማራዘሚያ!

(በድሉ ዋቅጅራ)

ኢትዮጵያ አደጋ ውስጥ ወድቃ፣ ዜጎች ተጨንቀው የነበረው ትህነግ የአማራና የአፋርን ህዝብ ላይ ሰቆቃ ውስጥ ከትቶ ሰሜን ሸዋ በደረሰበት ጊዜ ነበር፤ ያ ግን ለምእራባውያን ወደ ግባቸው የተጠጉ መስሏቸው ስለነበር አላስጨነቃቸውም፡፡

ጦርነቱን ትህነግ ከጀመረበት ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ በአንጻራዊነት የእፎይታ ጭላንጭል ያየችበት ጊዜ አሁን ነው፤ ህወሀት ወደ መቃብሩ እየተገፋ ነው፤ ወደ ሞት፡፡ ለምእራባውያኑ ይህ አይተውት አይደለም አስበውት የሚያውቁት አይደለም፡፡ ትህነግ የሌለበት ምስራቅ አፍሪካ፣ እንቢ ባይዋን ኢትዮጵያንና ማእቀብ ያልገደላትን ኤርትራ ይዞ ማየት ለአሜሪካና ለአውሮፓውያን የምጽአት መጀመሪያ ነው፡፡ ስለዚህ ለአለም አሁን ኢትዮጵያ ታይቶ የማይታወቅ መአት ውስጥ ናት ብለው ያሟርታሉ፡፡ በመሆኑም በአስቸኳይ፣ መቀሌ ከመያዙና ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ ለእግሩ ማሳረፊያ ከማጣቱ በፊት ተኩስ መቆም አለበት፡፡

ድርድሩ የትህነግን እየተቆረጠ ያለ ትንፋሽ የሚቀጥል ከሆነ ኢትዮጵያ መቼም ሰላም አይኖራትም፡፡ ድርድሩ የትህነግን አሟሟት ወግ ያለው ለማድረግ፣ በመቀሌና አካባቢዋ ተጨማሪ የሰው ህይወት እንዳያልፍ ለማድረግ እንጂ ትንፋሹን ለመቀጠል እንዳይሆን መጠንቀቅ ያሻል፡፡

ይህ ግን ቀላል አይደለም፤ ነጩ ቤተመንግስት በኢትዮጵያ ጉዳይ ምን ያህል እንደተወጠረ ለተመለከተ የሚመራው የራሱ ሀገር ያለው አይመስልም፡፡ የትህነግ ትንፋሽ ሲሰል የእነሱ ጫና ከመቸውም በላይ ከብዷል፡፡ ጫናው በቆምነበት ሊያጎብጠን፣ ከእርምጃችን ሊገታን፣ ሊያንገዳግደን ይችላል፤ ሊሰብረንና ሊያንበረክከን ግን አይገባም፡፡ ምርጫችን አንድ ብቻ ነው፤ የሚያስከፍለውን ከፍሎ ትህነግን መቅበር!

See also  ገራዶ-ገራዶ አለቀልሽ ልቤ ተንዶ ተንዶ - ወሎ!

Leave a Reply