ሰየኦን ላይን የንግድ አገልግሎት ማዕከሉ አማዞንን ጨምሮ መገናኛ ብዙኃንና ታዋቂ የአለም አቀፍ ተቋማት ድረ ገጾች መስራት ማቆማቸው ተነግሯል።
ድረ ገጾቹ መስራት ያልቻሉበት ምክንያት አለመታወቁን አልጀዚራ አስነብቧል።
ድረ ገጻቸው አለመስራቱ ከታወቁ ተቋማት መካከል ፋይናንሽያል ታይምስ፣ ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ብሉምበርግ ኒውስ፣ ሲኤንኤን በመገናኛ ብዙኃን መስክ ተጠቅሰዋል።
የኦን ላይን የንግድ አገልግሎት የሚሰጠው ግዙፉ አለም አቀፍ ተቋም አማዞንም ድረ ገጻቸው ከማይሰሩ ተቋማት መካካል አንዱ ነው።
የእንግሊዝ መንግስት ዋና ድረ ገጽም መስራት ማቆሙ ነው በመረጃው የተገለጸው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ቢቢስና ኒዮርክ ታይምስ በከፊል እየሰሩ መሆናቸው ተጠቁሟል።