ጁንታው የማይካድራ ዓይነት ጭፍጨፋ በሑመራ ከተማ ለመፈጸም ያቀደውን ዕቅድ የመንግስት የጸጥታና የድህንነት ሃይላት እንደደረሱበት ተሰማ። ፋክት ቼክ እንዳለው፣ ዕቅዱን ለማስፈጸመ ጁንታው ጦርነቱን ወደ አፋር ማስፋትን ምርጫው አድርጎ ነበር።
የመንግስት የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ “ማስጠንቀቂያ አንድ” በሚል ተገኘ ያለውን መረጃ “በዕቅዱ መሠረት ከትግራይ ክልልና ከሱዳን አስርጎ በሚያስገባቸው ሠርገ ገቦች አማካኝነት ጭፍጨፋውን እንደሚፈጽም ገልጧል” የሚል እንዳለበት ቃል በቃል ገልብጦ አስነብቧል።
ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲመች በራያና አፋር በኩል ተደጋጋሚ ትንኮሳ በመፈጸም የመከላከያ ሠራዊቱንና የአማራ ልዩ ኃይልን ትኩረት ማዛባት፣ ይህም ሲሆን የጦር ኃይል ወደ ራያና አፋር እንዲሳብ ማስገደድ፣ በዚሁ ዕቅድ መሰረት የምዕራቡ ኃይል ሲሳሳ በሁመራ በኩል ጥቃት በመክፈት ድርጊቱን ለመፈጸም ማቀዱን የተገነው መረጃ እንደሚያመለክት አስታውቋል።
ከዚሁ ጎን ለጎን “ጁንታው ከሰሞኑ የአማራ ልዩ ኃይልና መከላከያ በሑመራ ጭፍጨፋ እንደሚፈጽሙ በማኅበራዊ ሚዲያ ማሠራጨት እንደሚጀምር ዕቅዱ ያሳያል” ሲል የመንግስት የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል።
በሌላ የተቋሙ ማስጠንቀቂያ ሁለት መረጃ ደግሞ ጁንታው ከሰሞኑ በአፋር ግንባር በፈጠረው ትንኮሳ ከአፋር ልዩ ኃይልና ከመከላከያ ሠራዊት ምላሽ እንደተሰተው አስታውሶ፣ በዚህ ትንኮሳ ወቅት ያሰለፋቸው ያልሠለጠኑ ሕጻናትና ሴቶችን እንደሆኑ አመልክቷል። ጁንታው ከአካባቢው ሲሸሽ ከ300 በላይ አስከሬኖች በሲኖ ትራክ ጭኖ ወደ መቀሌ መፈርጠጡ ገልጿል።
የደኅንነት ምንጮች እንደጠቆሙት ጁንታው በዚህ መልክ የሚያሸሻቸውን የሕጻናትና የሴቶች አስከሬኖች በአንድ መቃብር በመቅበር የጅምላ ግድያ የተፈጸመባቸው መቃብሮች አስመስሎ ለማቅረብ እየተዘጋጀ ነው ሲል የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪይ አስታውቋል።
የመረጃ ማዕከሉ ከገለጸው በተጨማሪ የአፋር ልዩ ሃይልና በአካባቢው ያሉ አክቲቪስቶች በምስል በማስደገፍ ህጻናትና አንጋፋ ሴቶችን ጨምሮ በትሀንግ ሃይል ላይ ከፍተኛ ኪሳራ መድረሱን እየገለጹ መሆኑንን መዘገባችን፣ መከላከያም የተለያዩ ቦታዎችን በመጥቀስ በአፋር በኩል ጥቃት ለመሰንዘር የሞከረውን ሃይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታውቋል። እንደሚሰማው ከሆነ በትህነግ ላይ የደረሰው ሰብዓዊ ቀላል የሚባል እንዳልሆነ ነው።
በአሁኑ ሰዓት አብዛኞች እንደሚሉት ይህ ህጻናትንና አረጋዊያንን ለችግር እየዳረገ ያለ ጦርነት የሚቆምበት መፍትሄ ትህነግን ባገለለ መልኩ እንዲፈጸመ ሃሳብ እያቀረቡ ነው። አንዳንዶች ደግሞ ምሁራን የተሻለ የሚሉትን ሃሳብ እንዲያቀርቡ እየጠየቁ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ “ትህነግ ካንሰር ነው” በሚል መክሰም እንዳለበት የሚናገሩ አሉ።
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን ምኑ ነው አፍሪካ ህብረትን ስጋት ላይ ጥሎት… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑም ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል የዕዳ ጫናን… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ተበዳዮችን ለመካስ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል፡፡ በሀገራችንም የሽግግር ፍትህ አስፈላጊነት ታምኖበት ፖሊሲ ሲዘጋጅ መቆየቱ የሚታወቅ… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና በፕሬዚዳንቱ ስምና ፊርማ የተሰራጨው ደብዳቤ የሚሊሻ ሃይሉ ጸጥታ በማስከበሩ… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ሮማናት አደባባይ ላይ የተለመደው አይነት የፈንጠዝያ ድጋፍ… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን