በነ ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል የክስ መዝገብ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የፀረ ሽብር እና ሕገመንግሥታዊ ጉዳዮች ችሎት ክስ አሰምቷል።
በክስ መዝገቡ 58 ግለሰቦች እና 4 ድርጅቶች በሽብር ወንጀል መከሰሳቸው ይታወሳል።
ክስ ለማሰማት በተያዘው የዛሬው ቀጠሮም 21 ተከሳሾች ቀርበው ክሳቸው በንባብ ቀርቦላቸዋል።
ተከሳሾቹ የዋስትና ይከበርልን ጥያቄ ለፍርድ ቤቱ ቢያቀርቡም የፌዴራሉ አቃቢህግ የዋስትና መብታቸው ሊከበር የማይችልባቸውን ምክንያቶች በመጥቀስ ተከራክሯል።
አቃቢህግ ለ21ዱም ተከሳሾች ያለውን የክስ ስርዝር ከማስረጃዎች ጋር አቅርቧል።
ፍርድ ቤቱ በተከሳሾች የቀረበውን የዋስትና ጥያቄ እና የአቃቢ ህግን ምላሽ መርምሮ በመዝገቡ ላይ ትእዛዝ ለመስጠት ለጥቅምት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
እነ አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ በመዝገቡ ተካተው ነገር ግን በአካል ያልተገኙ ተከሳሾችንም ፌዴራል ፖሊስ ካሉበት ይዞ እንዲያቀርብ ችሎቱ ትእዛዝ ሰጥቷል። ዘገባው የኢብኮ ነው