የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ምክር ቤት ከሸኔ ጋር አብረው ሕዝብ ያዘረፉትን አመራሮች በቁጥጥር ስር አዋል፣ አዲስ አመራር ተካ

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ምክር ቤት ከወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ጋር በተገናኘ የአመራር ለውጥ አደርጓል። አሸባሪው የህወሓት ቡድን ከአማራና አፋር ክልሎች ተደምስሶ እስከውጣበት ጊዜ ድረስ ከውረራቸው አከባቢዎች በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን አንዱ ነው። ቡድኑ በልዩ ዞኑ በወረራ በቆየባቸው ወቅት ግድያ፣ዘረፋ እና ንብረት የማውደም ተግባር ፈፅሟል። ከሌሎ አከባቢዎች በተለየ እንዚህ ድርጊቶችን በሽብር ቡድኑ ብቻ የተፈፀሙ እንዳልነበሩ ተመልክቷል።

ህወሓት በኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ከሸኔ ሃይሎች ጋር ከማበሩ ባሻገር የልዩ ዞኑ የተወሰኑ የአመራር አካላት የሁለቱን ቡድኖች የጥፋት ተልእኮ ለማስፈፀም ሲንቀሳቀሱ እንደነበርም ተገልጿል። በተቃራኒው ህዝቡን ከሁለቱ ቡድኖች ጥቃት ማህበረሰቡን በመከላከል እስከ ህይወት መስዕዋትነት የከፍሉ አመራሮችም እንደነበሩ ምስክርነታቸውን የሰጡ ብዙ ናቸው።

ይህንንም ተከትሎ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በኋላ በርካታ የዞኑ አመራሮችን ከኃላፊነት በማንሳት በአዲስ ተክቷል። ከሽብር ቡድኖቹ ጋር ያበሩ ኣካላትም በህግ ቁጥጥር መዋላቸው ተገልጿል።

በምክር ቤቱ የተሾሙ አዲስ የልዩ ዞኑ አመራሮች ማህበረሰቡን በማደራጀት የአከባቢውን ሰላም በዘላቂነት ማስጠበቅ እና የዞኑ ነዋሪዎች በሽበርተኞቹ የህወሓት እና ሸኔ ቡድኖች ካደርሱባቸው የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች እንዲያገግሙ ማድረግ ተቀዳሚ ተግባራቸው እንዲሆን የዞኑ ምክር ቤት አሳስቧል።

በልዩ ዞኑ በሸባሪ ቡድኖች ምክንያት ከቤት ንብረታታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች የመደገፍና ተቋርጠው የነበሩ የመንግስት የአገልግሎት ተቋማት ደግም ስራ የማስጀመር ስራ እየተከናወነ መሆኑንም የዞኑ አዳዲስ አመራሮች ለኢቲቪ ተናግረዋል። Via EBC


Leave a Reply