ነሀሴ 29 ቀን 2013
ታታሪውና አይደፈሬው የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በመርሳ ድሬ ሮቃ በሚባል አከባቢ ጁንታውን ድባቅ መታው ።
በአፋር ክልል ሚሌ መስመርን ለመያዝ ቋምጦ በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ወረዳ ድሬ ሮቃ በተባለ አካባቢ በአራት አቅጣጫ ማለትም በጮቤ፡በቀለንቲ:ሰርጢ እና ቀላ በተባሉ ተራሮችን ለመያዝ እና ሰብሮ ለመግባት የመጣውን አሸባሪ ሃይል ይዞት ከመጣው ሰውና ማቴርያል ጋር መደምሰሱን የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል የአንድ ብርጌድ ዋና አዛዥ ተናገሩ ።
የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል ከአጋር ክፍሎች ጋር በመሆን ሽብርተኛው ያደረጋቸው ተደጋጋሚ ሙከራዎችን በማክሸፍ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል ብለዋል ።
በዚህም 431 ተደምስሷል ። 60 ክላሽ ፣ ብሬን 3 ፣ ስናይፐር 2 እና 1 መገናኛ ሬዲዮ ተማርኳል ።
በተለይ የአከባቢው ማህበረሰብ እና ታጣቂ ሰላሙን ነቅቶ ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ሰራዊቱ በተሳካ ሁኔታ በግዳጁ ድል እንዲያመጣ ትልቅ እገዛ ያደረገ ሲሆን ፣ በዚህም ምግብ ፣ ውሃ ፣ ተተኳሽ ሰራዊቱ እስካለበት ድርስ በማቅረብ እና አብሮነቱን በማጠናከር ለተገኘው ድል የአንበሳውን ድርሻ መያዙን የአንድ ብርጌድ ም/አዛዥ ተናግረዋል ፡፡
የቀበሌ 24 ሊቀመንበር አቶ ሃሰን ከረሙ መሃመድ ፣ ህዝቡን ፣ ወጣቱንና ታጣቂውን በማደራጀት አከባቢያችንን እየጠበቅን ሲሆን ፣ ጁንታው ወደ አካባቢያችን በተደጋጋሚ ሊገባ ሙከራዎችን ያደረገ ቢሆንም ጠንክረን በመመከት ቀበሌያችንን ሳናስደፍር ቆይተናል ። ሰራዊታችን ከመጣ በኋላም ሁሉም የቀበሌያችን ነዋሪ እስከ ግንባር ድረስ በመዝለቅ ስንቅ ፣ ተተኳሽ ለጀግናው ሰራዊታችን እያቀረብን እንገኛለን በተገኘው ድልም ኮርተንበታል በማለት ተናግረዋል፡፡
ደመላሽ ጥላሁን (ከግዳጅ ቀጣና)
ፎቶግራፍ ምትኩ ገብሩ እና መዝገቡ ያረጋል