ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር አልዘጋሁም አለች – ዜናው የሽብሩ አካል ነው

‘Citizen TV’ የተባለው የኬንያ ቴሌቪዝን ጣቢያ በትናንትናው ዕለት “ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘጋች” የሚል መረጃ አስረጭቶ ነበር። የቴሌቪዥን ጣቢያው ኬንያ ከ800 ኪሎሜትር በላይ የሚረዝመውን የሁለቱን ሀገራት ድንበር ላልተወሰነ ጊዜ መዝጋቷን ለዘገበበት ዜና ምንጭ አልጠቀሰም።

የኬንያ ፖሊስ አገልግሎት (Kenya Police Service) ዛሬ እንዳስታወቀው የኬንያ-ኢትዮጵያ ድንበር መዝጋቱን በተመለከተ በሚዲያ የተሰራጨው መልዕክት የተሳሳተ መሆኑን አስታውቋል።

“አንዳንድ ሚዲያዎች በተሳሳተ መንገድ እንደዘገቡት ሳይሆን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስነው ድንበር አልተዘጋም” ያለው የኬንያ ፖሊስ “ያደረግነው በድንበር አካባቢ ያለውን የጸጥታ ቁመናችንን ማጠናከር ነው” ሲል አብራርቷል። የኬንያ ፖሊስ በተጨማሪም በድንበር አካባቢ ያለው ሁኔታ የተረጋጋ መሆኑን ገልጿል።

የኬኒያ ፖሊስ በትናንትናው ዕለት “አጎራባች” ባላቸው ሀገሮች እየታዩ ነው ካላቸው የጸጥታ ሁኔታዎች አኳያ አምስት ነጥቦችን የያዘ መግለጫ አውጥቶ የነበረ ሲሆን ከነጥቦቹ መካከል በድንበር አካባቢ የጸጥታ ቁጥጥርን ማጠናከር የሚል ይገኝበታል።

ኢትዮጵያ ቼክ (https://t.me/ethiopiacheck/899)

Leave a Reply