የህብረቱ ስብሰባ ውጤታማ ሆኖ መጠናቀቁን የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንትና የህብረቱ ሊቀመንበር አስታወቁ

– ሊቀመንበሩ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምስጋና አቅርበዋል፣

– አፍሪካውያን ድምጻቸውን የሚያስከብር ዓለም አቀፍ ሚዲያ ያስፈልጋቸዋል፣


የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበር እና የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የቀረበው የአፍሪካውያንን አጀንዳ የሚያራምድ ሚዲያ የማቋቋም ሃሳብ የሚደገፍ ነው።

የህብረቱ ስብሰባ ውጤታማ ሆኖ መጠናቀቁን ጠቅሰው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን ላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል በ35ኛ የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የመዝጊያ ስነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የቀረበው የአፍሪካውያንን አጀንዳ የሚያራምድ ሚዲያ የማቋቋም ሃሳብ የሚደገፍ ነው።

በአፍሪካውያን ላይ የሚቀርቡትን ትርክቶች የምንከላከለው በሚዲያ ነው ብለዋል። በሚዲያ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ያነሱት የአፍሪካን ሃሳብ የሚያቀነቅን ሚዲያ መቋቋም አለበት ብለዋል፤ ይህ ሀሳብ የሚደገፍ ነው።

የፓን አፍሪካን ሃሳብ የሚያቀነቅንና 24 ሰዓት ሙሉ ስለአፍሪካ የሚዘግቡ ጣቢያዎችና ጋዜጦች ያስፈልጉናልም ብለዋል።

በጉባኤ ተሳታፊ ለሆኑ መሪዎች ላደረጉት የሞቀ አቀባበልና ጉባኤው የተሳካ አንዲሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምስጋና አቅርበዋል።

የኮቪድ ወረርሽኝ ጊዜ ለስብሰባው የተገኙ አፍሪካውያን በተመሳሳይ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

የህብረቱ ኮሚሽነር ሙሳ ፋቂ በበኩላቸው መረጃ ወሳኝነት አለው፤ የአፍሪካን ፍላጎትና ጥቅም የሚያስከብር ሚዲያ አስፈላጊ ነው። አፍሪካውያን ድምጻቸውን የሚያስከብር ዓለም አቀፍ ሚዲያ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።

የአየር ንብረት ለውጥ፣ የኢኮኖሚ ትስስር፣ ጤና፣ሰላምና ጸጥታ የአፍሪካውያን ቀጣይ አጀንዳዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በጌትነት ተስፋማርያም ENA

Leave a Reply