ዓለም ባንክ የ6 ቢሊየን ዶላር አዲስ ፕሮጀክት ለማጽደቅ ማቀዱን አስታወቀ – አሜሪካ ድጋፍ እንደምትሰጥ አረጋገጠች

አሜሪካ ፕሮጀክቱ እንዲጸድቅና ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንድትሆን ድጋፍ እንደምትሰጥ አረጋገጠች፤ በኢትዮጵያና አሜሪካ መካከል ተፈጥሮ የነበረው ብዥታ መቀረፉና የዕዳ ሽግሽግ እንደሚደረግ ታወቋል

ከዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) የጸደይ ወቅት ጉባኤ ጎን ለጎን የተደረጉ ውይይቶች የኢትዮጵያን እውነታ ያስረዱና ጥቅሟን ያስጠበቁ መሆናቸውን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ተናገሩ። በአሜሪካ በተካሄዱ ውይይቶች ዓለም ባንክ በቀጣይ ሁለት ዓመታት ውስጥ በዓለም አቀፉ የልማት ማህበር አማካኝነት ለኢትዮጵያ የ6 ቢሊየን ዶላር አዲስ ፕሮጀክት ለማጽደቅ ማቀዱንም ነው የተናገሩት።

ኢትዮጵያ በልማት ማዕቀፍ ውስጥ የባንኩ ከፍተኛ ተጠቃሚ መሆኗ እንደሚቀጥልም ተነግሯል። ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ጋር በተደረገው ቆይታም በቡድን 20 ሀገራት በጋራ ማዕቀፍ ውሳኔ መሰረት የዕዳ ሽግሽግ እንዲደረግ ቢወሰንም እስካሁን ሳይተገበር የቆየው ምክረ ሃሳብ ዳግም እንዲታይ ከስምምነት ላይ መደረሱን አስረድተዋል።

አይ ኤም ኤፍ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙን እንደሚደግፍና የውጭ ምንዛሪ ድጋፉን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ውይይቶች እንዲካሄዱ ከስምምነት መደረሱን የገንዘብ ሚኒስትሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ከጉባኤው ጎን ለጎን ለአሜሪካ መንግስት የኢትዮጵያን እውነታ የሚያስረዳ የዲፕሎማሲ ስራ መሰራቱን ያነሱት ሚኒስትሩ፥ በኢትዮጵያና አሜሪካ መካከል የተፈጠረውን ብዥታ ከማጥራትና ግንኙነትን ከማደስ አንጻር ውጤታማ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።

በዓለም ባንክ እና አይ ኤም ኤፍ በኩል የሚታሰቡ ፕሮጀክቶች እንዲጸድቁ አሜሪካ ድጋፏን እንደምትሰጥ አረጋግጣለችም ነው ያሉት።

ግንኙነታቸው ወደ ቀደመ መልኩ እንደሚመለስና እንደመልካም ማሳያም ዓለም ባንክ በግጭት ምክንያት የተጎዱ አካበቢዎችን መልሶ ለመገንባትና ለማቋቋም 300 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ሲያጸድቅ አሜሪካ እና አጋሮቿ በሙሉ ድምጽ ድጋፉን ማጽደቃቸውን አውስተዋል።

በሰሜኑ ግጭት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የከፋ አቋም ይዞ የቆየው የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዩ ኤስ ኤይድም ቢሆን ከዳይሬክተሯ ሳማንታ ፓወር ጋር የተደረገውን ውይይት ተከትሎ ያቋረጣቸውን ፕሮጀክቶች እንደሚያስቀጥልና ለመልካም ወዳጅነትም በድርቅ እና በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑንም አስረድተዋል።

በአጠቃላይ በአሜሪካ የነበረው ቆይታ እጅግ ውጤታማ እና የኢትዮጵያን ጥቅም ያስከበረ ስለመሆኑም ነው የገለጹት።

አያይዘውም ድጋፎቹም ሆኑ የታደሰው ግንኙነት ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታን ታሳቢ ያላደረገ መሆኑን ጠቁመው፥ ውሳኔዎቹ ብዥታን ማጥራትና የኢትዮጵያን እውነታ ማሳወቅ በመቻሉ ከመረዳት የመነጨ ነው ብለዋል።

ዜናው የፋና ነው

Related posts:

የመሰረተ ልማት ቀበኞች ላይ " የሞት ቅጣት"May 26, 2022
ኢሳያስ - ዘመቻው እስከ መጨረሻ ቀብር ይሆናል ሲሉ ትህነግን አስጠነቀቁMay 25, 2022
በአማራ ክልል እፎይታ እየነገሰና የትህነግ የወረራ ዕቅድ መምከኑ ተሰማMay 25, 2022
ንግድ ባንክ ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ ከ50 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን አስታወቀMay 25, 2022
ቢለኔ ታይም መጽሔትን ማብራሪያ ጠየቁ፤ የተሰላ ጥቃትና የአንድ ወገን ትርክት ማቅረቡን ኮንነዋልMay 25, 2022
"ከውስጥ በር ለማስከፈት ... ከጣራ በላይ ጩኸት" አብን አማራን ለሶስተኛ ዙር ወረራ እያመቻቹ ያሉትን በይፋ አወገዘMay 24, 2022
በኢትዮጵያ በተከሰቱ ግጭቶች ሁሉ የትህነግ እጅ እንዳለባቸው በመረጃ ተረጋገጠMay 24, 2022
ፋኖ እየጨፈረ ከመከላከያና አማራ ልዩ ሃይል ጋር የግዳጅ ቀጠናውን ተረከበMay 23, 2022
ተልዕኮ አስፈጻሚዎችና ከ1780 በላይ ሕዝባዊ ኀላፊነታቸውን ያልተወጡ ተጠርጣሪዎች ተያዙMay 23, 2022
በሕግ ማስከበር ዘመቻ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ዋሉMay 23, 2022
በአማራ ክልል መፈንቅለ መንግስት ታቅዶ ነበርMay 23, 2022
Number of IDPs Hits Record High GloballyMay 22, 2022

Leave a Reply