በደራሼ አካባቢ ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንት በጥፋተኝነት የተጠረጠሩ ከ450 በላይ ግለሰቦችና 17 አመራሮችና የፀጥታ አካላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን እንዲሁም በደቡብ ኦሞ ዞን አካባቢ ደግሞ 650 የሚሆኑ ግለሰቦችና 11 አመራሮች በሕግ እንዲጠየቁ መደረጉ ተገለጸ።ክልሉን የግጭት ማዕከል ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው አመለከቱ።
ግንቦት 19 ቀን 2014 (ኢዜአ) በብሔር ስም እየነገዱ ክልሉን የግጭት ማዕከል ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሠላም ኃይሎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው አስታወቁ።
የደቡብ ክልል የፀጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ ክልላዊ የፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም የክልሉን ሠላምና ደህንነት በማስመልከት የተከናወኑ ተግባራትና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ውይይት መድረክ በወላይታ ሶደ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በዚህ ወቅት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው እንዳሉት በሀገራዊ ለውጡ ማግስት ያለፈው ሥርዐት ብልሹና ከፋፋይ አስተሳሰብ መሠረት ያደረጉ ግጭቶች መከሰታቸውን አስታውሰው በዚህም በርካታ ጥፋት ደርሷል ብለዋል።
ይህንን ጥፋት ለማስቆም በተለይ በክልሉ ክህዝቦች ጋር በቅርበት በተከናወኑ ስራዎች ባለፉት ሁለት አመታት በክልሉ አንፃራዊ ሠላም ማስፈን መቻሉንና በተገኘው ሠላም ወደ ልማት በመዞር ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየቱን ጠቅሰዋል።
ሆኖም በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ላይ የተራዘሙ ግጭቶች እየተስተዋሉ ነው ያሉት አቶ ርስቱ በቅርቡ በደራሼ ልዩ ወረዳ አካባቢ የተከሰተው ግጭት የፀጥታ አካላትንም ጭምር ለአሰቃቂ መስዋዕትነት የዳረገ መሆኑን አውስተዋል።
በተለይም በደራሼ ፣ ኮንሶ ፣ ኧሌ እና አካባቢው ላይ ግጭቶችን ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት ቀጠናውን እያወኩ ፣ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እየገቱ እንደሚገኙ ገልጸው እነዚህ አካላት በብሔር ስም የሚነግዱና ክልሉን የግጭት ማዕከል የማድረግ ዓላማ ያነገቡ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
የክልሉ መንግስት ባለፈው አንድ ወር እነዚህን አካባቢዎች ከማረጋጋት ባለፈ ሕግን የማስከበር ሥራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመው አሁንም በፀረ ህዝብ በሆኑት ኃይሎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በደራሼ አካባቢ ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንት በጥፋተኝነት የተጠረጠሩ ከ450 በላይ ግለሰቦችና 17 አመራሮችና የፀጥታ አካላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን እንዲሁም በደቡብ ኦሞ ዞን አካባቢ ደግሞ 650 የሚሆኑ ግለሰቦችና 11 አመራሮች በሕግ እንዲጠየቁ ተደርጓል ብለዋል።
በኮንሶና ኧሌ በነበረው ግጭት እንዲሁም በስልጤ ዞን ለመቀስቀስ ተሞክሮ በነበረው የሐይማኖት ግጭት ምክንያት የተጠረጠሩ ግለሰቦችም በቁጥጥር ሥር የማዋል ሥራም እንዲሁ እየተከናወነ እንደሚገኝ አመላክተዋል።
በክልሉ በየአካባቢው ህዝቦች የሚነሱ የአደረጃጀት ጥያቄዎች ለግጭት መንስኤ ሊሆኑ አይገባም ያሉት አቶ ርስቱ እነዚህን አጀንዳዎች ተጠቅመው ክልሉን ለማወክ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ብለዋል። ለዚህም የፀጥታ አካላት ብቻ ሳይሆኑ የፖለቲካ አመራሩም በቁርጠኝነት መታገልና ህዝቡን የማንቃት ሥራ መስራት አለበት ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
- National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: CouncilThe Ethiopian National Security Council has issued a statement on latest developments in the country. In its statement, the Council underscored the need to mend the deep-seated national fractures through an inclusive approach. More stories HISTORY REPEATING… Read more: National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: Council
- Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia” The Republic of Somaliland, is a sovereign state with its own laws and constitution, reaffirmed by the people of Somaliland in a democratic constitutional referendum. The Government of the Republic of Somaliland’s Statement Regarding the G7 Communique… Read more: Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia”
- Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamismPermitting foreign firm’s involvement in the import, wholesale and retail business, which was restricted to local companies, would bring a new dynamism in Ethiopia’s economy, well-noted experts said. Speaking to the Ethiopian Press Agency (EPA), Ethiopian Economics… Read more: Foreign firms’ local market involvement entails economic dynamism
- Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourningKenya’s military chief Gen. Francis Ogolla died in a helicopter crash west of the country, President William Ruto announced Thursday and declared three days of national mourning. The helicopter was carrying 11 people, including Gen. Ogolla, when… Read more: Kenya’s military chief dies in a helicopter crash, Nairobi declares three days of national mourning