የካይሮ የ ‘ኢንዱስትሪ -ድርቅ’ ትርክት

የዓባይልጅ

ግብፃዊ የውሃ ምህንድስና ፀኃፍት ምሁራዊ ውሸተ-ዜና ከሚቆጣጠሩት በላይ ተምታቶባቸዋል።የቀደሙ አመታት ትርክታቸውን ትተን ከወራት ወዲህ የነዟቸው ነጥቦች ብቻቸውን አስረጂ ይሆናሉ። ፕሮፌሰር አባስ ሻራኪ ዶክተር ሙሐመድ ሐፌዝ ሀኒ ኢብራሂም እና ሌሎችም ከራሳቸው ልቦለዳዊ ቁጥሮች ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።

(እኔ)፣ ከቀናት በፊት የሶስተኛውን ሙሌት ብስራት ቅዳሜ ረፋድ ጠብቁ ብያችሁ ነበር፤ ወደ ኋላ በነበሩ ጥቂት ቀናት ከቦታው ባገኘሁት የውሃው ከፍታ ግስጋሴ መረጃ አንፃር ያሰላሁት፤ ያለሳቴላይት ወይም ኮርቻውን ባላገናዘበ መንገድ ነበር። ከዛም ሁለቱ ማስተንፈሻዎች መከፈታቸውን ከራሳቸው ግብፆች ሰማን። (ይፋ ባይደረግም ይህን እውነት አላጡትም ማለት ነው።) በዚህም ውሃው ወደ ጫፍ ሲጠጋ ወደ ኮርቻው መሙላት ጀመረ፤ ቀናቶች ተራዘሙ፤ መጠኑም በተመሳሳይ ከተገመተው ከፍ አለ።
▪️አሁን የሙሌቱን ብስራት ነገ ላይ እየጠበቅኩት ነው ብላችሁስ? ወጣ ወረደ ይኸው ብያችኋለሁ! እጠብቃለሁ!

የካይሮ ባለሙያዎች ከዘንድሮው ክረምት መግቢያ አንስቶ እስከዛሬዋ እለት በነበራቸው ትርክት አንደኛ፣ ስለ ግድቡ የግንባታ ግስጋሴ ያስቀመጡት ስሌት ነበር።
በግንባታ አፈፃፀሙ መሰረት በነሀሴ 10 እኤአ ( በነገው እለት) ግድቡ ያጠራቅመዋል ብለው ያስቀመጡት የውሃ መጠን ሁለተኛው ትርምሳቸው መሆኑ ነው። ከሁለቱ የውሸት ትርክቶች በተቃራኒው ራሳቸው በፅሁፍ ማስፈራቸውን ተመለከትኩ። በዚህም ከአመታዊ የዝናብ መጠን ቅናሽና ለሁለቱ ሀገሮች ውሃው ይቀንሳል የሚል ውሸታቸውን የዓባይ ሙሌት በልቶታል።
ቀደም ሲል ያሰፈሯቸው ነጥቦች አንዱ የዘንድሮው የግድቡ ማእከላዊ ኮሪደር ከፍታ የኮንክሪት ሙሌት የቀደሙ አፈፃፀሞችን አገናዝበን ነው በማለት የደመደሙት 595 ሜትር ቢደርስ ነው የሚለውን እዚጋ ያዙልኝ..።

ለግብፅ የሚደርሰው የውሃ መጠን ይቀንስብናል የሚለው የተለመደ አቤቱታ ነው። ከዚሁ በተያያዘ የዘንድሮው የዝናብ መጠን ከታሪካዊ የድርቅ ሪከርዶች ከአንደኛው ጋር እኩል ነው ሲሉም ነበር። በተለይም በ1980ዎቹ ከተከሰተው የተፋሰሱ ኢንዱስትሪያል ድርቅ ሪከርድ ጋር እኩል ነው ሲሉ ትንተና ሰጥተውበት ነበር። ይሁንና ውሃው ሱዳን ላይ የጎርፍ አደጋ ሲፈጥር ተመለከትን። ከግብፃዊው ፕሮፌሰር አባስ ሻራኪ ደግሞ በቂ ውሃ እያገኙ ስለመሆናቸው የገለፁት ከቀናት በፊት ነው።

በሐምሌ 18እኤአ ከሃያ አንድ ቀናት በፊት፣ ስሌታቸው ግድቡ በዘንድሮው ሙሌት አጠቃላይ የውሃ ይዞታ 18 ቢሊዮን እንደሆነና ነሀሴ 15 ሞልቶ እንደሚፈስ ደምድመው ነበር። በነገው እለት ነሐሴ 10እኤአ ያሰፈሩት ጠቅላላ የውሃ መጠን 13 ቢሊዮን BCM ይላል። ዛሬ በዋዜማው ነሀሴ 9 ራሳቸው የፃፉት ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ወደ ኮርቻ ግድቡ እየተኛ ነው የሚል ሆኗል። በዚህ ሁኔታ ውሃው ሞልቶ ሲፈስስ እስከ 22 ቢሊዮን ውሃ ከተሞላ በኋላ ነው ብለው ገለፁ።
በዚህ አመት የግድቡ መሀል ኮሪደር እነሱ ካሰሉት በ 5 ሜትር መብለጥ የቻለ ሲሆን ከከፍታውና የዝናብ መጠን ጋር አስልተው የሰጡት የውሃ መጠን የ 9 ቢሊዮን BCM ልዩነት ሊያመጣ ችሏል።
ምሁራዊ ውሸተ-ዜናቸው ከመሬቱ ሀቅ መጣረሱ የተለመደ ቢሆንም የዘጠኝ ቢሊዮን BCM ልዩነቱ ደግሞ ከራሳቸው የውሸት እውነታ ጋር መጣረሳቸውንም ይጨምራል። (18 BCM ሆነ 22BCM ከእነሱ እንጂ በኛ በኩል ምንም አልተባለም። ስለ ቁጥሩ የሚባል ይኖራል ተብሎም አይጠበቅም። በአምናው ሙሌት የነበረውን ቁጥር ግብፃዊያኑ ሲቀናንሱትም ይታወሳል)

See also  ደመቀ መኮንን ዛሬ ያነጋገሯቸውን የአውሮፓ አገራት ዲፕሎማቶችን ወቀሱ

ይህን ለምን እንደሚያደርጉ ባለሙያ ጠይቄ ነበር። እይታቸውን እንደነገሩኝም፣ ስለቁጥሩ ማነስ ወሬ ሲነዛ ከሀገር ውስጥ ጫና ተፈጥሮ አፈፃፀሙ ከዛ በላይ መሆኑን ለማሳመን ኦፊሺያል ቁጥር በመንግስት እንዲገለጥላቸው በማሰብ ሊሆን ይችላል አሉኝ። እነሱ የሚነዙትን ውሸት ለማምከን ተብሎ ትክክለኛው መጠን ኦፊሺያሊ ቢነገራቸው ለሌላ የአቤቱታ አጀንዳቸው ግብአት ማግኘት ቻሉ ማለት ነው ሲሉም ጨምረው ገለፁልኝ።
(ትክክለኛውን ስሌት ማምጣት እንደሚቸገሩ ከዘጠኝ ቢሊዮኑ ልዩነት መታዘብ ይቻላል/ይህ ብቸኛው ምክንያት ባይሆንም..)
ታዲያ ስንት ውሃ ተያዘ እያሉ ሲያጣጥሉ የነበሩት እነ አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ኦፊሻል ቁጥሩን ለካይሮ የማድረስ አላማ ይመስልባቸዋል” ቢቢባል መሰረተ ቢስ ውንጀላ ነውን?

FinishTheGERD #eslemanabay

Leave a Reply