በፀሃይ መውጫና በቅሎ ማነቂያ – ሲያበቃ ጭፍራ እንደዚህ ሆነ

“የጀግናቹ ውሎ” በሚል ርዕስ ስር የቀረበው አስገራሚ ገድል በመከላከያ ኩራትን፣ በሰራዊቱ አባላት ኢትዮጵያዊ ወኔ ሃሴትን የሚያጎናጽፍ ሲሆን መከላከያን ለማንጓጠጥ ለሚሞክሩ ደግሞ የሚያሳፍር ነው!!

ይሔ ሁሉ ዝግጅት የተደረገው ደግሞ የረጅም ጊዜ ታሪክ ባለቤትና የአፍሪካ ኩራት የሆነችውን ኢትዮጵያ ለማፍረስ ነው። ይህ የትህነግ በፀሃይ መውጫ እና በቅሎ ማነቂያ ያደረገው ዝግጅት ደግሞ አንዱ የማፍረስ ህልሙን ለማሳካት ግስጋሴው እንዳይገታ ቀድሞ የተዘጋጀበትና የተማመነበት ምሽግ ነው።

ወገል ጤና ፀሃይ መውጫ ላይ ጠንካራ ምሽግ ቆፍሯል። ምሽጎቹ ደግሞ ከመሬቱ ጋር ተመሳስለዋል። የሜካናይዝድ ኃይሉን በየመሳሪያዎቹ ርቀት ላይ እነሱንም እንደምሽጎቹ አመሳስሎ ጠምዷቸዋል። የቡድን መሳሪያ ተኳሾቹም ሆነ እግረኛ ኃይሉ እጆቻቸውን ከምላጭ መሳቢያው ጋር አጣምረው እየጠበቁ ነው።

ይሔ ሁሉ ዝግጅት የተደረገው ደግሞ የረጅም ጊዜ ታሪክ ባለቤትና የአፍሪካ ኩራት የሆነችውን ኢትዮጵያ ለማፍረስ ነው። ይህ የትህነግ በፀሃይ መውጫ እና በቅሎ ማነቂያ ያደረገው ዝግጅት ደግሞ አንዱ የማፍረስ ህልሙን ለማሳካት ግስጋሴው እንዳይገታ ቀድሞ የተዘጋጀበትና የተማመነበት ምሽግ ነው።

ይህን በወገን ኃይል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ ያሰፈሰፈውን ሽብርተኛ የመደምሰስና ምሽጉን የማስለቀቅ ግዳጅ የተሰጠው ደግሞ በደቡብ ዕዝ ለሚገኝ አንድ ኮር ነበር።

ኮሩ ይሔንን ከፊት ለፊቱ በበቂ ሁኔታ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለውን ቦታ ይዞ የሚጠብቀውን ኃይል ከቆፈረው ጉድጓድ አውጥቶ ለመቅበር ከበላይ አካል የተሰጠውን ትዕዛዝ ለመፈፀም ግንባር ቀደም ሆኖ ተንቀሳቀሰ።

ለዚህ ፍልሚያ ወደፊት የተንቀሳቀሰው ኮርም በፍፁም ኢትዮጵያዊ ጀግንነት ለ3 ቀናት ያለዕረፍት በተደረገ እልህ አስጨራሽና ተከታታይ ውጊያ ጠላት ይዞት የነበረውን ቁልፍና እስትራቴጂካዊ ቦታ የህይወት መስዋዕትነት ጭምር በመክፈል ምሽጉ ላይ ተረማምዶ ሽብርተኛውን ቡድን ሙት ቁስለኛና ምርኮ በማድረግ ቁሶቹንም ማረከ።

ይህን አኩሪ ገድል የፈፀመው የደቡብ ዕዝ አካል የሆነው ይህ ኮር ከዚህ የድል ምዕራፍ ወደሌላኛው የድል ምዕራፍ ለ2ኛ ጊዜ ተንቀሳቀሰ። ቦታው ደግሞ ከፍተኛ ሙቀትን የሚያስተናግደው ጭፍራ ነው።

አሸባሪው ህወኃት የኢትዮጵያን የገቢ እና ወጪ ኮሪደር የሆነውን ሚሌን ለመቁረጥ ያለ የሌለ ኃይሉን በማሰለፍ ከፍተኛ የሆነ ርብርብ ሲያደርግ የዚህን ሴረኛ ሴራ ለማክሸፍ ይህ ኮር ጭፍራ ላይ የጠላትን እንቅስቃሴ ለመገደብ ቆረጣ እንዲገባ ከበላይ አካል ትዕዛዝ ተሰጠው።

ኮሩ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት የሰው ኃይሉንና ትጥቆቹን ወደቦታው በማንቀሳቀስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጠንካራ የመከላከል ምሽግ ሰርቶ በተጠንቀቅ ቆመ።

ልቡ በትቢት ያበጠው ሽብርተኛ ምሽጉን ሰብሮ ለማለፍ ለተከታታይ 7 ቀናት ሌት ተቀን የሚችለውን ሁሉ አደረገ አንበሶቹ ግን አልተበገሩም ከመከላከል ወደ ፀረ ማጥቃት ተመልሰው አፍራሹን ህልመኛ አፈራረሱት ትጥቆቹንም ማረኩ ። በዚህ ግንባርም ጠላት ከፍተኛውን ጉዳት አስተናግዶ የተረፈው ፈረጠጠ።

በገቡበት ግንባር ሁሉ ድል አድራጊዎቹ የደቡብ ዕዝ የዚህ ኮር አመራሮችና አባላት ሺህ ሆነው እንደ አንድ ፣ አንድ ሆነው እንደ ሺህ ለሌላ ግዳጅ ተዘጋጁ ተባሉ። የሚፈፅሙት ግዳጅም በግልፅ ተነገራቸው። በእርግጥም ቶሎ መንቀሳቀስ አለባቸው ምክንያቱ ደግሞ ነውር ጌጡ ትህነግ ያሰማራቸው አፍራሾች አዲስ አበባ ለመግባት የሚያደርጉትን ጉዞ ለመግታት ነው።

ጀግኖቹ የዚህ ኮር አባላት በጭፍራ አዳይቱ ዞን አምስት በማድረግ የኮምቦልቻ ሀርቡ አዲስ አበባን መስመር መቁረጥና ጠላትን ቅርቃር ውስጥ መክተት ነበር። በተግባርም ሀርቡ ላይ ዝግትግት አድርገው ጠበቁት ከፊትም ከኋላም የተቆረጠው ጠላት ተጨማሪ የሰው ኃይልም ሆነ ትጥቅ ማግኘት በማይችለው ወጥመድ ውስጥ ሰተት ብሎ ገባ። ጀግኖቹም እያሳደዱ ተገተጉት። የተደናገጠው እና የተበተነው የጠላት ኃይልም አንድ በአንድ ተለቀመ ታንኮቹ ጥይትና ስንቅ የሚያጓጉዙት ተሽከሪካሪዎቹ ነደዱ። እነዚህ ነበልባል የደቡብ ዕዝ ትንታጎች ሀርቡ ላይ ትልቅ ጀግንነትን ፈፅመው የኢትዮጵያን ህዝብ የድል ዜና አበሰሩ።

በዕረፍት አልባና እልህ አስጨራሽ ሁኔታዎች ውስጥ በተደጋጋሚ ተፈትነው ያለፉት የደቡብ ዕዝ አናብስት 5 ወራትን በፈጀ ውጊያ ወደሸዋ የዘለቀውን ጠላት ከመላው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊትና የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሆነው እየደመሰሱና እያሳደዱ ህልሙን ካኮላሹበት በኋላ ቆቦ ዞብል ራማ ገብርኤል በተባለው ቦታ ላይ ከምስራቅ ዕዝ አካሎች ጋር ግዳጅ እንዲፈፅሙ ትዕዛዝ የተቀበሉት የዚህ ኮር ሳተናዎች በጠላት ስር የነበረውን ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለውን ቦታ በመቆጣጠር ድርብርብ ድልን አስመዝግበዋል።

የኢትዮጵያዊነትን አልሸነፍ ባይነት ትጥቅን ያነገቡት እነዚህ የኮር አባላት ውለው ባደሩባቸው ግንባሮች ሁሉ ፊታቸውን ሳያጥፉ ከጠላት ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ በመተናነቅ ኢትዮጵያ መቼም የማትፈርስ ሀገር መሆኗን ህይወታቸውን ጭምር ገብረው አፅንተዋታል።

ኢትዮጵያም ጀግኖች ልጆቿ ለሰሩት ታላቅ ገድል ክብር ሰጥታቸዋለች። በደቡብ ዕዝ ስር የሚገኙት እነዚህ ጀግኖችም በአሃድና በግለሰብ ደረጃ የተለያዩ ሽልማቶችን አጊንተዋል። በክፍለ ጦር ፣ በስታፍ ድጋፍ ሰጪና በሜካናይዝድ እንደአሃድ እንዲሁም በምርጥ ተዋጊ ከ3ኛ እስከ አንደኛ ደረጃ ሜዳይ እና በምርጥ ሻምበል አዛዥና ምርጥ ሎጀስቲክስ ዘርፍ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል።

ሁሌም በሰንደቅ ዓላማቸው ፊት የገቡትን ቃል በተግባር እያረጋገጡ ያሉትን የደቡብ ዕዝ የአንድ ኮር ጀግኖችን ውሎ ” ከባህር በጭልፋ” ያህል በጥቂቱ አካፈልኳችሁ። ሰላም።

አብዮት ዋሚ ፣የካቲት 4 ቀን 2014 መከላከያ ፌስ ቡክ
ፎቶግራፍ አብዮት ዋሚ

Leave a Reply