የአሜሪካና የአዲስ አበባው የሰላም ንግግር በውጥረት ሰንብቶ ተጠናቀቀ

የሰላም አማራጭ በሚል መንግስት፣ ዓለም ዓቀፍ ተቋማትና አገራት “አማጺ” ከሚሉት የትህነግ አመራሮች ጋር ሲካሄድ ሰንብቷል። በተያዘለት ዕቅድ መሰረት ያልተጠናቀቀው የሰላም ንግግር የተጓተተው በዋናነት አዲስ አበባ ላይ ሲደረግ የነበረው እጅ ጥምዘዛ የተሳካ ባለመሆኑ እንደሆነ ተሰማ። ይኸው አሜሪካ ከመንግስት ጋር በየቀኑ ስታደርግ የነበረው ጫና ትናንት መጠናቀቁ ታውቋል። ይህን ተከትሎ የደቡብ አፍሪካው ውጤት ይነገራል እየተባለ ነው።

ላለፉት ሁለት ዓመታት ራሱን “የትግራይ መንግስ” ሲል የሚጠራ የነበረው፣ በምህጻረ ቃል ደግሞ ሲፈጠር እንደነበረው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ የሚለው፣ ህዝብ “ወያኔ” ወይም “ሽፍታ” የሚለውን ስም ልክ እንደ ብራንድ ያጸደቀለትና እሱም በይሁንታና በኩራት ከነደጋፊዎቹ የተቀበለው፣ እነ ቢቢሲ “የትግራይ ሃይሎች” ሲሉ ያለስሙ የሚጠሩት፣ መንግስት ደግሞ ” አሸባሪ” ብሎ በፓርላማ ስም የሰጠውና አሁን አሁን ማንኛው ተቋም፣ ሚዲያም ሆነ አገር ” አማጺ” እንዲለው ሲል ህጋዊ ቁመናን የገፈፈው ድርጅት ነው ትህነግ።

ለዚህ ይመስላል አቶ ስዬ አብርሃ ሰሞኑን “ከመንግስት እኩል ለንግግር መቀመጣችን ድል ነው” ሲሉ የተሰሙት። ወንድማቸው አቶ አሰፋ አብርሃ በአባልነት የሚገኙበት የትህነግ ወኪሎች ጋር ግንኙነትና መረጃ የሚያገኙት አቶ ስዬ ለንግግር መቀመጥ በራሱ ድል እንደሆነ ቢያመለክቱም ከንግግሩ ድርጅታቸው በሚጥብቀው ልክ የሚያገኘው ነገር ሊኖር እንደማይችል ፍርሃቻቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።

የኢትዮ 12 የመረጃ ሰዎች እንዳሉት የስዬ ስጋት ትክክል ነው። ሲያስረዱም ንግግሩ ሲደረግ የሰነበተው በትህነግና በመንግስት በኩል ሳይሆን በአሜሪካና ኢትዮጵያ መካከል ነው። ልክ ደቡብ አፍሪካ እንደሚደረገው ሁሉ አዲስ አበባ ባለው የአሜሪካን ኤምባሲ አማካይነትና በቀጥታ ከአሜሪካ ነጩ ቤት ስልክ በመቀደወል ከመንግስት ጋር እለት እለት የድርድር ስብሰባ ይደረግ ነበር።


የንግግር ሂደቱ “ብዙ ጣልቃገብነት” እንዳጋጠመው ጠ.ሚ ዐቢይ ገለጹ

 “ህወሓት ህገመንግስቱን እንዲያከብር እና ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ አንድ ክልል” እንዲንቀሳቀስ ለማሳመን ጥረት እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

ህወሓት “ፍላጎችንን መገንዘብ የሚችሉ ከሆነ እና የራሱን ህገመንግስት የሚያክብር እና በህጉ መሰረት የሚንቀሳቀስ ከሆነ ሰላም ይሰፍናል ብየ አስባሁ” ሲሉ ተናግረዋል ጠቅላይ ሚስትሩ፡፡

See also  በግልጽ አስታውቃ ኢትዮጵያ አምባሳደሮችን መጥራቷ " ሰበር ዜና" ሆነ

ደቡብ አፍሪካ ያቀናው የኢትዮጵያ ልዑክ የመንግስትን አቋም ይዞ የሄደ በመሆኑ በጫና ምንም ሊቀለበስ ባለመቻሉ፣ አሜሪካ የኢትዮጵያን መንግስት ባለስልጣናት በዲፕሎማቶቿ አማካይነት ወጥራ ይዛ መክረሟንና ይህም ጫና በየቀኑ ይደረግ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

ድርድሩ ሲጀመር ማራኪ ፕሮጀክቶች፣ ሰፋፊና ዓለምን ያነጋገሩ የእርሻ ማሳዎች፣ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ሲመርቁና የክልል የመስክ ጉብኝት ላይ ትኩረት ሰጥተው የከረሙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” ጫናው ከፍተኛ ነው” ሲሉ በገሃድ መናገራቸው ይታወሳል። ይሁን እንጂ በጫና የሚሆን ነገር እንደሌለና መንግስት ከያዘው አቋም ዝንፍ እንደማይል ማስታወቁን ለሲሲስጂ ገልጸዋል።

መረጃ አቀባዮቻችን እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጫናው ተሰላችተው በመስክ ስራ መጠመዳቸውን እንደ አንድ ማሳያ ያስቀምጣሉ። አሜሪካ እያሴረችባቸው ያሉት አብይ አሕመድ ትህነግ ራሱን እንደ ክልል አይቶ፣ የታጠቀውን መሳሪያ ፈቶ፣ ካሁን በሁዋላ ለማን ስጋት እንደማይሆን እስካልተረጋገጠና በትግራይ ህጋዊ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲመሰረት ካልተሰማማ በቀር ሰላም ምኞት እንደሆነ እንቅጩን መናገራቸው ይናገራሉ። በዚሁ መሰረት ትህንግን እንደ ልማዳቸው አዘውት የተባለውን ካላደረግ መንግስት በጀመረው ህግን ያማስከበርና የታገተውን የትግራይ ሕዝብ ነጻ ከማውጣት የሚይዘው አንዳችም ሃይል እንደሌለ ገሃድ አድርገው በመጨረሻም ትናት ጭቅጭቁና ጫናው የታሰበውን ያህል ሳይሳካ አሜሪካ “እሺ” ብላ ወደ ደቡብ አፍሪካ መረጃ ማስተላለፏና በዛው መሰረት ንግግሩ እንዲጠናቀቅ መወሰኑ ተሰምቷል።

ዛሬ ኦባሳንጆ ይሰጡታል የተባለው መግለጫ የጊዜ ሰሌዳ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ትህነግ ትጥቅ እንደሚፈታ የሚታወጅበት እንደሆነ የመረጃው ሰዎች አመልክተዋል። ትህነግ ክልል መሆኑንን፣ እንደክልል ራሱን ተቀብሎ እንደሚንቀሳቀስና አስቸኳይ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም መስማማቱም ታውቋል። አምነስቲን አስመልክቶ ግን ህዝብን የጨፈጨፉና በሰብአዊ መብት ጥሰት የሚፈለጉ በሂደት በሚደረግ ማጥራት በአገሪቱ ህግና ደንብ መሰረት ለህግ እንደሚቀርቡ ቴክኒካል ስምምነት ተደርጓል።

እንደ መረጃው ከሆነ ዋናው ስብሰባ ሲከናወን የነበረው አዲስ አበባ በአሜሪካና በመንግስት መካከል በመሆኑ ትናንት ንግግሩ መጠናቀቁን ተከትሎ ነው የደቡብ አፍሪካው ንግግር መቋጫ ውጤት ይፋ እንደሚሆን የተሰማው። አሜሪካ አስቸኳይ የተኩስ አቁምን ጨምሮ አራት መሰረታዊ ጉዳዮች ከስብሰባው እንደምትጠብቅ ማስታወቁ አይዘነጋም።

See also  "በጩኸት እና በጫጫታ የአማራ ክልል መንግስትን በማዳከም አማራውን ነጻ ማውጣት አይቻልም"

የአምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ፍጹም ዛቻ የተሞላው ቲዊት በማድረግ ማስፈራራታቸው ይታወሳል። ሴትየዋ “በሰላም ንግግሩ ማብቂያ የሚደረስበትን የውስኔ አሳብ የሚቃወም ማናቸውም ወገን ላይ እርምጃ እንወስዳለን” ሲሉ ያሰራጩት መረን የለቀቀ ማስፈራሪያ ተከትሎና በሌሎችም ገፊ ምክንያቶች መንግስት ስም ሳይጠራ የነበረውን የአገር ለአገር ግንኙነት መልሶ ለመመርመር እንደሚገደድ በማግለጫ አመልክቷል። ሕዝብም በከፍተኛ ቁጥር አደባባይ በመውጣት አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ እያደረገች ያለውን ጫና እንደታቆም በቁጣ መጠየቁም ይታወሳል።


የጆ.ባይደን አስተዳደር የሰላም አማራጭ ንግግሩን ቀድሞ የትህነግን ፍላጎት አቋም አድርጎ አቀረበ

“በኢትዮጵያ ተፋላሚ ወገኖች መካከል የሚደረገው የሰላም ንግግር አራት ግቦች አሉት ። አፋጣኝ የተኩስ አቁም፣ ያልተገደበ ሰብዓዊ ዕርዳታ ፣ የሰላማዊ ሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ተጨማሪ እርምጃዎች መውሰድና የኤርትራ ወታደሮች ከሰሜን ኢትዮጵያ መውጣታቸውን ማረጋገጥ”


በዚህ መልኩ የተጣናቀቀው የሰላም አማራጭ ንግግር ምንም ይሆን ምን መንግስት ከያዘው አቋም እንደማይነቃነቅ ምንጮቹ አስታውቀዋል። የአፍሪካ ህብረትን የሰላም አደራዳሪነት እንደምትደግፍ እያስታወቀች ጫና ስታካሂድ የቆየችው አሜሪካ በውጭ ጉዳይዋ አማካይነት አስቀድማ ያስታወቅችው አራት የውሳኔ አሳቦች የተካተቱበት ወይም መንግስት “አንድ የመከላከያ ሃይል ብቻ” ባለው መሰረት ስምምነት የተደረሰበት የውሳኔ አሳብ ከአንድ ሰዓት በሁዋላ ይሰማል።

Leave a Reply