ከ29 ሚሊዮን ብር በላይ ግብይት የፈፀሙ በማስመሰል ሀሰተኛ ደረሰኝ የሰጡ ሁለት ግለሰቦች በእሰራት ተቀጡ

በሀሰተኛ መታወቂያ የወጣ የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን በመጠቀም ግብይት ሳይኖር ከ29 ሚሊዮን ብር በላይ ግብይት የፈፀሙ በማስመሰል ሀሰተኛ ደረሰኝ የሰጡ ሁለት ግለሰቦች እና በህገወጥ ተግባሩ ላይ የተሳተፈ ግለሰብ በእስራት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ተከሳሽ ተስፋሁነኝ ተሾመ ሐምሌ 24/2013 ዓ.ም በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ቦታው ቄራ ዳውን ታውን ህንፃ አካባቢ በሚገኝ ንግድ ቤት ውስጥ በሀሰተኛ መታወቂያ የወጣ የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን በመጠቀም ግብይት ሳይኖር 17 ሚሊዮን 940 ሺሕ ብር ሃሰተኛ ደረሰኝ ቆርጦ ሲሰጥ እጅ ከፍንጅ ተይዟል፡፡

በተመሳሳይ ገነት ሀይሉ በልደታ ክ/ከተማ ባልቻ ሆስፒታል አካባቢ ከሚገኝ አሕመድ ህንጻ ውስጥ በሀሰተኛ መታወቂያ በወጣ የግብይት ማሽን ግብይት ሳይኖር 12 ሚሊየን 135 ብር ግብይት እንደተፈፀመ በማስመሰል ሃሰተኛ ደረሰኝ ቆርጣ ስትሰጥ እጅ ከፍንጅ ተይዛለች፡፡/ዋልታ/

See also  ‹‹ በምርጫው ሂደት በጥላቻ ንግግር ላይ የሚሰማሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አመራርና አባላትን በህግ የመጠየቅ ስራ ይሰራል›› አቶ አወል ሱልጣን በጠ.አ. ህግ የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ

Leave a Reply