በኦሮሚያ በሌብነት ጉዳይ አናቱ ተፈርቷል፤ በ289 ሺህ ካሬ.ሜ.መሬት ላይ ማጣራት ተጀምሯል

ትህነግ ይከተል በነበረው “አበስብስ” የሚባል ለውጭ የተግኮረጀ ስልት በርካታ በስልጣን ላይ ያሉ ሃላፊዎች ከሌብነት የጸዱ እንዳልሆነ መረጃዎች ያረጋግጣሉ። በተለይ ኦሮሚያ ላይ ሌብነት ገሃድ እንደሆነ ማሳያዎችም አሉ። ሰሞኑንን ይፋ የሆነውን የሌብነት ዘመቻ ተከትሎ ኦሮሚያ ሌቦች ላይ መዝመቱን ይፋ አድርጓል። ዋናው የሌብነቱ አናቱ መፈራቱ እየተገለጸ ባለበት ወቅት ይህ መረጃ መሰጠቱ ጉዳዩን ይበልጥ አነጋጋሪ አድርጎታል።

ኢዜአ በኦሮሚያ ክልል በሙሰኞች ላይ ጠንካራ ሕጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መግለጹን ጥቅሶ ድታ የተነተራሰ ዜና ዘግቧል። በዚሁ ዜና የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባለፉት ሶስት ወራት የሙስና ወንጀል የፈጸሙ አካላት ላይ የተወሰደውን እርምጃ አስመልከቶ መሬትና ገንዘብና ንብረት ከሌቦች ላይ መወረሱን አስታውቋል። የታሰሩ መኖራቸውና ዕግድ የተጣለበት ሃብት መኖሩን አመልክቷል።

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ጉዮ ዋሪዮ በሰጡት መግለጫ ባለፉት ሶስት ወራት ከ1 ሺህ 300 በላይ ግለሰቦች የሙስና ወንጀል መፈጸማቸው ተረጋግጦ ጉዳያቸው ውሳኔ አግኝተዋል። ይሁን እንጂ ሌብነትን ለመዋጋት በብሄራዊ ደረጃ ከታወጀው አዋጅ ጋር ሲታይ ጅምሩ ቀድሞ ቢሆንም ክልሉን በልቶታል ከተባለው ሌብነትና ከሸኔ ጋር የተያያዙ ዝርፊያዎች አንጻር ሲመዘን ዜናው ሚዛን የሚደፋ እንዳልሆነ እየተተቸ ነው።

እያንዳንዱ የወንጀሉ ተሳታፊ ከአንድ ዓመት ከ6 ወር እስከ 16 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑንን ሃላፊው ቢያስታውቁም፣ ሪፖርት እንጂ አሁን ላይ ወቅቱ ስለሚጠብቀው የሙስና ዘመቻ የተባለ ነገር የለም።

በተለያዩ ከተሞች ከ230 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ መሬት፣ 70 ሚሊዮን ብር፣ ሶስት የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና ሶስት መኖሪያ ቤቶች ለመንግሥት ገቢ መደረጉን፣ባለፉት ሶስት ወራት 285 ከሙስና ጋር የተያያዙ መዝገቦች ላይ ምርመራ እየተደረገ ሲሆን፤ ጉዳዩ እስኪጣራ ድረስ 67 ሚሊዮን ብር መታገዱን፣ በተጨማሪም 289 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት፣ በተለያ ከተሞች የሚገኙ ሰባት መኖሪያ ቤቶችና ሶስት ተሽከርካሪዎች ታግደው መርመራ እየተደረገ መሆኑን ሃላፊው በሪፖርታቸው አመልክተዋል።

መሬት አስተዳደር፣ የመንግሥት ግዥና ጨረታ ዋና ዋና ለሙስና ወንጀል ተጋላጭ የሆኑ ዘርፎች መሆናቸውንም ጠቁመዋል። በሙስና ወንጅል ተሳትፈው የተገኙትም መሓንዲሶች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ ባለሃብቶችና ደላሎች መሆናቸውንም አቶ ጉዮ ገልጸዋል። የክልሉ መንግሥት ከየትኛውም ጊዜ በላይ ሙሰኞች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኑ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ገልጸው፤ የክልሉ ሕዝብ መንግሥትን በቅርበት እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል።

See also  በአጣዬና አካባቢው የተፈጸመውን የወንጀል ድርጊት የሚያጣራ የፌዴራልና የክልሉ የምርመራ ቡድን ሥራ ጀመረ

Leave a Reply