ህወሓት ከሽብርተኛነት ተሰረዘ

  • 61 የፓርላማ አባላት ተቃውመውታል፤
  • አምስት የፓርላማ አባላት ደግሞ ድምጽ ከመስጠት ታቅበዋል

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ህወሃትን ከሽብርተኝነት ሰርዟል።

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከሽብርተኛ ድርጅት እንዲሠረዝ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ ባሄደው ልዩ ስብሰባ ህወሓትን ከሽብርተኛ መዝገብ ለማንሳት በቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በአብላጫ ድምፅ ውሳኔውን አፅድቋል።

በዛሬው ልዩ ጉባኤ 280 የፓርላማ አባላት ተገኝተው ነበር፡፡

በዚህ ልዩ ጉባኤ የህወሓት ከሽብርተኝነት መሰረዝ 61 የፓርላማ አባላት ተቃውመውታል፤አምስት የፓርላማ አባላት ደግሞ ድምጽ ከመስጠት ታቅበዋል።

በዚህም መሰረት በአብላጫ ድምጽ ህወሃት ከሽብርተኝነት ዝርዝር እንዲነሳ ተወስኗል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

See also  “ህወሃት በሚያኮርፍባቸው የሶማሊያ ‹አሸባሪ› ድርጅቶች ይጠረጠራል”

Leave a Reply