የኦሮሞ ዞን ምክር ቤት ጥብቅ ገደብ ጣለ

የኦሮሞ ዞን ምክር ቤት ከግንቦት 7—8 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ባካሄደው 5ኛ ዙር 18ኛ መደበኛ ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ባለ አስር ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

የአቋም መግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦

1ኛ/ በየትኛውም ቦታና ሁኔታ ጥይት ያለ አግባብ መተኮስ የተከለከለ ነው።

2ኛ/ ጥይት የተኮሰዉን ሰዉ መደበቅ አይቻልም።

3ኛ/ ከተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

4ኛ/ በዞናችን ውስጥ እና በአጎራባች ዞኖች አከባቢ ምንም አይነት ወታደራዊ ስልጠና መሰልጠንና ማሰልጠን ፈፅሞ የተከለከለ ነው።

5ኛ/ የብሄር ግጭት ለመፍጠር መንቀሳቀስ በህግ ያስጠይቃል።

6ኛ/ አጋጣሚዎችን በመጠቀም የኃይማኖት ግጭት ለመፍጠር መንቀሳቀስ በህግ ያስጠይቃል።

7ኛ/ ከመንግሥት ውጭ ማንኛውም ቅስቀሳ ማድረግ እና መሳተፍ አይቻልም።

8ኛ/ በግል ፣ በቡድን እና በድርጅት ስም በተከፈተ የፌስቡክ አካውንት የአቋም መግለጫ ማውጣት እንዲሁም የጥላቻ እና ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ንግግር ማራገብ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

9ኛ/ ሺሻ ቤት ከፍቶ ማስጠቀም እና ሺሻ ቤት ዉስጥ ገብቶ መጠቀም አይፈቅድም።

10ኛ/ ለማይታወቅ ግለሰብ ቤት ማከራየት እና የማይታወቅ ግለሰብ መደበቅ የተከለከለ እንደሆነ ምክር ቤቱ የጋራ መግለጫ በማውጣት ጉባኤው ተጠናቋል።

የኦሮሞ ዞን ምክር ቤት ግንቦት 8/9/2014 ዓ.ም ከሚሴ

You may also like...

Leave a Reply