ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ዛሬ ከጉራጌ ማህበረሰብ በቤተመንግስት በነበረው ውይይት ከተናግሩት

“ደሜ የጉራጌ ነው፣ በፖለቲካ አስተሳሰብ ደግሞ የዜግነት ፖለቲካ ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉት ውጥንቅጦች መቋጫ ነው ብዬ አምናለሁ። ለዚህም እየሰራሁ ነው። ጉራጌን በተመለከተ ሃሳቤን ለመግለፅ ያህል ከሆነ ሁሌም እንደምለው ውሳኔውን ለህዝቡ እንተውለት ነው። እኔ አውቅልሃለው አልለውም። ህዝቡ ያለው ደግሞ ታች ነው።”

-ጉራጌ የሚታወቀው በባህል፣ በኢኮኖሚ ምሳሌነት በመሆን እና ከሌሎች ብሔረሰቦች አብሮ በመኖር መተሳሰብንና አብሮነትን የሚያስተምር ማህበረሰብ ነው እንጂ በብሔር ፖለቲካ (identity politics) ሲሳትፍ አይቼ አላወቅም።

-ጉራጌ በዘር ተደራጀቶ በኢትዮጰያ ፖለቲካ ሲሳትፍ በታሪክም የለም፤ አይቼም አላውቅም። ማህበረሰቡ በዘር መደራጅት ጥቅም እንደሌለው ጠንቅቆ ስለሚያውቅ የብሔር ፖለቲካ አጥብቆ እንደሚጠላ አውቃለሁ። አሁን ግን ባህልና ፖለቲካ የተቀላቀል ይመስላል።

-ጉራጌ በዘር መደራጅት የመጀመሪያው የሚጎዳው የጉራጌ ማህብረሰብ ነው፤ ቀጠሎም ለዘመናት ለፍቶ ያቃናው ሀገሩ (ኢትዮጵያ) ይጎዳል። በብሔር ተደራጀቶ ነጻ የወጣ ህዝብ የለም። የጉራጌ ማህበረሰብ ሰነልቦናው በብሔር ለመደራጅት የሚምች አይደልም። የብሔር ፖለቲካ ጉዳቱ እየዋል/አያደረ ዋጋ ስልሚያስከፍል ጉራጌ በዘር መደራጅት በመላው ኢትዮጰያ ሰርቶ የሚኖረው 60% የሚሆነው የጉራጌ ህዝብ ዋጋ አለመስጠት ጭምር ነው።

-ጉራጌ ባለበት ቦታ ሁሉ ዴሞከራሲያዊና ሰብአዊ መብቱ ተከብሮለት በሰላም እንዲኖር የመጀመሪያው ኢትዮጵያ ሰላም መሆን አለባት። ስለዚህ የጉራጌ ማህበረሰብ የሚያዋጣው መላው ኢትዮጰያ ሰላም እንዲሆን አብክሮ መስራት ይጠበቅበታል።

በታሪክ አባቶቻችን ምንም በሌለበት ለሀገር ግንባታ የከፈሉት ዋጋ ብዙ ነው፤ በዚህ ጊዜ ሀገራችን የብሔር ፖለቲካ ጫፍ በነካበት ወቅት አብሮ ማጫጫህ ሳይሆን የጉራጌ ህዝብ አሁናዊ ኢትዮጰያ ችግር የሚፈታብት ዘዴ በመፍጠር የአባቶቻቸን አደራ መውጣት ይኖርብናል።

-ስለዚህ የጉራጌ ማህበረስብ የሚያዋጣው መላው ኢትዮጰያ ሰላም እንዲሆን ጠንክሮ መስራት ይጠበቅበታል። ሀገሪቱ በዘር ተከፋፈሎ የሚያልቅ ከሆነ የመጀመሪያ ተጎጂ የሚሆነው የጉራጌ ማህበረስብ ነው።

Via samson Michaelovic

See also  "ጩኸቱ ግን የማነው? መነሻውስ ከየት ነው?ፍላጎቱስ ምንድን ነው?"

Leave a Reply