በአዲስ አበባ 200 ሺህ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎች የሚንቀሳቀሱት በህገ ወጥ ቦሎ ነው

የተሽከርካሪ እና አሽከርካሪ ቁጥጥር ባለስልጣን እንዳስታወቀው በህጋዊ መንገድ ከምርመራ ተቋማት ቦሎ የሚወስዱ ተሽከርካሪዎች 48 ከመቶ ብቻ ናቸው ብሏል፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ወራቶች በህጋዊ መንገድ ከምርመራ ተቋማት ፍቃድ አግኝተው ቦሎ የወሰዱ ተሽከርካሪዎች 330ሺህ ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡

የአሽከርካሪ እና ተሸከርካሪ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍሬው ደምሴ እንደተናገሩት፣ አሁን ላይ በአዲስ አበባ ደረጃ 650ሺህ ተሸከርካሪዎች እንደተመዘገቡ ገልጸው በየአመቱ ቦሎ የሚወስዱ ተሽከርካሪዎች ግን 450ሺህ የሚሆኑት ብቻ ናቸው ብለዋል፡፡

የተቀሩት ተሽከርካሪዎች አመታዊ ተሽከርካሪ ምርመራ የት እየሄዱ እንደሚያደርጉና ቦሎም ከየት እንደሚወስዱ አይታወቅም ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ደረጃ እውቅና ተሰጥቷቸው ተሽከርካሪ ምርመራ የሚያደርጉ ከ50 በላይ የምርመራ ተቋት እንዳሉ የተነገረ ሲሆን፣አብዛኛዎቹ የአቅም ክፍተት እንዳለባቸው ተጠቅሟል፡፡

የአሽከርካሪ እና ተሸከርካሪ ቁጥጥር ባለስልጣን እነዚህ ችግሮም ለመቅረፍ ከምርመራ ተቋማቱ ጋር በመቀናጀት አዲስ አሰራር መዘርጋቱንም ነው የገለጸው፡፡
በዚህም ተሽከርካሪዎች አመታዊ የቴክኒክ ምርመራ በቴክኖሎጂ በታገዘ የምረመራ አገልግሎት የሚሰጣቸው ይሆናልም ተብሏል፡፡

See also  ጊዜ እየጠበቀ የሚያገረሸው የአኙዋና ኑኤር ግጭትን ተከትሎ ሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ፣ እጃቸው ያለበት ባለስልጣናት እየተመረመሩ ነው

Leave a Reply