“እኔ ምንም የለኝም ለሰዎች ልሰጥ የምችለው ብቸኛው ነገር ደስታ ነው”

ሪች ዋልተርስ ይባላል ኮሎምቢያዊ ነው ሪች ዋልተርስ ቤት አልባ እና ጎዳና ተዳዳሪ ሲሆን ውሎው እና አዳሩ በኮሎምቢያ ጎዳናዎች ላይ ነው። ቀኑ ተገባዶ የኮሎምቢያ አበባ ገበያ ሲበተን ሪች ዋልተር ወደ አበባ መደብሮች በመሄድ ከገበያተኞች የተረፉ እና ከመጠረዝ የተረፉ አበቦችን ይሰበስባል

ይህንን የሚያደርገው ለራሱ አይደለም ይልቅስ በኮሎምቢያ መንገዶች ላይ ለሚያገኛቸው ሰዎች “ደስተኛ ሁኑ! መልካም ቀን ይሁንላችሁ” እያለ ለመስጠት ነው::

ከፊቱ ላይ ፈገግታ የማይጠፋው ዋልተርስ “እኔ ምንም የለኝም ለሰዎች ልሰጥ የምችለው ብቸኛው ነገር ደስታ ነው” ይላል:: ከሪች ዋልተርስ እጅ አበባ የተቀበሉ ሰዎች “ከአበቦቹ ጋር አብሮ የሚለግሰው ፈገግታ እና ደስታ ልብን ያሞቃል” ይላሉ

አንዳንድ ነገሮች ዋጋቸው እልፍ ቢሆንም ነጻ ናቸው !!
በእንድሪያስ ዘመላዕክ

See also  ኢትዮጵያዊቷ ሳይንቲስት

Leave a Reply