ኦሮሚያ ክልል ከተሃድሶ ኮሚሽን ጋር ተስማምቶ የመልሶ ማቋቋም ጀመረ

  • መንግስት በያዘው ዕቅድ መሰረት የክልሉን ልዩ ሃይል እንዲስተናገድ ተስማምቶ ስራ ተጀምሯል

“በኦሮሚያ ክልል የሚስተዋለውን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ እየተሰራ ነው” ማለታቸውን የዘገበው የክልሉ ሚዲያ ነው። የሚሰተዋለውን የፀጥታ ችግር እና ግጭትን በተረጋጋ ሁኔታ በውይይት በመፍታት አስተማማኝ ሰላምን ለማስፈን እንዲሁም መልሶ ለመገንባት በትኩርት እየተሰራ መሆኑን ብሔራዊ ታህድሶ ኮምሽንም አስታውቋል፡፡

ኮምሽኑ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ ምክትላቸው አቶ አወሉ አብዲን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች በተገኙበት ነው የምክክር ስብሰባ ያደረጉት። በዚሁ ስብሰባ ላይ ክልሉ በሙሉ ተባባሪነት እንደሚሰራ አስታውቋል።

የብሔራዊ ታህድሶ ኮሚሽን ኮምሽነር አቶ ተሸመ ቶጋ በሀገሪቱ ታጥቀው በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች የተለያዩ ችግሮች ገጥመዋል ፤ እነዚህን ችግሮች በፍትህ ሽግግር ለመፍታ እየተሰራ እንደሆነ በውይይቱ ላይ ጠቁመዋል ተብሏል። ችግሮችን እና አለመግባባቶችን በተረጋጋ መልኩ በውይይት እና በመግባባት መቅረፍ እንደሚያስፈልግም አምባሳደር ተሾመ በማመልከት ከታተቁ ሃይሎች ጋር ውይይት የሚደረግበት አግባብ ላይ አተኩረዋል። ክልሉም ሙሉ ዝግጅት እንዳለውና የተኬደበትን ርቀት አስረድቷል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በመድረኩ የክልሉ መንግስት በክልሉ የሚገኙ የቀድሞ ሰራዊት አባላትን መልሶ የማቋቋምና የተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ መርሐ ግብር መጀመሩን ገልጸዋል። የክልሉ መንግስት ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል። በዚሁ አግባብ መንግስት ባስቅመጠው አግባብ መሰረት የልዩ ሃሉን ያከስማል። መሰናበት ለሚፈልጉትም መልሶ ማቋቋሚያ መርሃ ግብር ተጀምሯል።

አቶ ተሾማ ቶጋ በበኩላቸው የኮሚሽኑ ዋና አላማ ለሀገርና ለህዝብ ሀገራዊ አገልግሎት የሰጡ እና በጦርነት መስዋዕትነት የከፈሉ የቀድሞ ሰራዊት አባላትን መልሶ ማቋቋም እንደሆነ አስታውሰዋል።

See also  ኢትዮጵያ በራሷ ዜጎች ላይ ጥቃት አልሰነዘረችም!

Leave a Reply